የጥቅምት 1 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
የመስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የሶማሊያና የግብጽ ፕሬዝደንቶች በኤርትራ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። የሁለት ሃገራት መሪዎች ከኤርትራው ፕሬዝደንት ጋር በሁለትዮሽ፤ በአፍሪቃ ቀንድና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተገልጿል።
የተመድ በመላው ዓለም ወጣቶች ለዘርፈ ብዙ ጥቃቶች መጋለጣቸውን አመለከተ። የተመድ ታይቶ ለማይታወቅ የጥቃት ማዕበል እና ጦርነት ባመጣው ጾታዊ ጥቃት እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ፤ ረሃብና መፈናቀል ተጋልጠዋል።
ግብጽ በሱዳን ጦርነት በአየር ድብደባ ተሳትፋለች በሚል ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል መሪ የቀረበባትን ክስ አስተባበለች።
የጎርጎሪዮሳዊው ዓመት 2024 የስነጽሑፍ የኖቤል ሽልማት ለደቡብ ኮርያዋ ደራሲ ሃን ካን ተሰጠ።
10/10/2024 • 8 minutes, 48 seconds የረቡዕ መስከረም 29 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
10/9/2024 • 10 minutes, 2 seconds የመስከረም 28 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
10/8/2024 • 9 minutes, 52 seconds የመስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
10/7/2024 • 8 minutes, 16 seconds የመስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
10/6/2024 • 11 minutes, 33 seconds የመስከረም 25 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
10/5/2024 • 9 minutes, 27 seconds የመስከረም 24 ቀን 2017 የዓለም ዜና
10/4/2024 • 9 minutes, 58 seconds የመስከረም 23 ቀን 2017 የዓለም ዜና
10/3/2024 • 9 minutes, 43 seconds -የኢትዮጵያ መንግሥት የአማራ ክልል ነዋሪዎችን በጅምላና በዘፈቀደ ማሰሩ የሕግ የበላይነትን ይበልጥ መሸርሸሩን አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።---የእስራኤልና የሊባኖስ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕ ደቡባዊ ሊባኖስ ዉስጥ በቅርብ ርቀት እየተዋ ጉ ነዉ።----በወርሮበሎች ጥቃትና አመፅ በተመሰቃቀለችዉ ሐይቲ ከ7 መቶ ሺሕ በላይ ሕዝብ ከቤት ንብረቱ መፈናቀሉ ተነገረ።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለዉ ካረቢያይቱ ሐገርን ከጥፋት ለማደን ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ አበክሮ መጣር አለበት።የዜናዉ መልዕክት የእስካሁኑ ነበር
10/2/2024 • 10 minutes, 30 seconds የማክሰኞ መስከረም 21 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
10/1/2024 • 8 minutes, 36 seconds የመስከረም 20 ቀን 2017 የዓለም ዜና
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በኻርቱም የሚገኝ የአምባሳደሯ መኖሪያ ቤት በወታደራዊ አውሮፕላን ተደብ ድቧል በሚል ያቀረበችውን ክስ የሱዳን ጦር አስተባበለ። በደቡብ አፍሪካ ምሥራቅ ኬፕ ክፍለ ግዛት በተፈጸመ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 18 አሻቀበ። ርዋንዳ ኃይለኛ ተላላፊ በሆነው ኢቦላ መሰል የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ስምንት ሰዎች መሞታቸውን አስታወቀች። እስራኤል ሊባኖስን በእግረኛ ወታደሮች ከወረረች ሒዝቦላሕ ለውጊያ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ። የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮቭ ጋላንት ሀገራቸው እግረኛ ወታደሮቿን ወደ ሊባኖስ ልታዘምት እንደምትችል ፍንጭ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ኢራንን አስጠንቅቀዋል
9/30/2024 • 10 minutes, 33 seconds የመስከረም 19 ቀን 2017 የዓለም ዜና
9/29/2024 • 10 minutes, 31 seconds የመስከረም 18 ቀን 2017 የዓለም ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዛ አብዲ ባሬ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ የተፈራረመችው የመግባቢያ ሥምምነት የሶማሊያን የግዛት አንድነት ይጥሳል ሲሉ ከሰሱ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሀገራቸው “ዓላማ በቀጠናው የጋራ ዕድገት እና ብልጽግና መፍጠር” እንደሆነ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና የአይኤምኤፍ ባለሙያዎች በተራዘመ የብድር አቅርቦት የመጀመሪያ ግምገማ ተስማሙ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በዳርፉር ግዛት በምትገኘው አል-ፋሽር ለሁለት ቀናት በፈጸመው ጥቃት 48 ሰዎች ተገደሉ። የሊባኖሱ ሒዝቦላሕ መሪው ሐሳን ናስረላሕ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት መገደላቸውን አረጋገጠ።
9/28/2024 • 10 minutes, 21 seconds የዐርብ መስከረም 17 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
9/27/2024 • 10 minutes, 58 seconds የመስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
DW Amharic-የዛሬው የዓለም ዜና በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እስር እና ወከባ እየጨመረ መጥቷል መባሉ፤በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ መከበሩ፤የሱዳን ጦር በዋና ከተማይቱ ካርቱም የመድፍ እና የአየር ድብደባ መጀመሩ ፤ደቡብ አፍሪቃ በፀረ አፓርታይድ ትግሉ ወቅት በስደት ሆነው ህይወታቸውን ያጡ ዜጎቿን አስከሬን ወደ ሀገር መመለሷ፤የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የተኩስ አቁም ስምምነት ሀሳብን ውድቅ ማድረጋቸው እና ሩሲያ የምዕራቡን ዓለም ለመገዳደር አዲስ የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ አጠቃቀም ሰነድ ማውጣቷን ያስቃኛል።
9/26/2024 • 10 minutes, 15 seconds ደቡብ ኢትዮጵያና ጋምቤላ ክልሎች በደረሱ የመኪና አደጋዎች 35 ሰዎች ሞቱ።ናይሮቢ-የኬንያ እናቶች ጥሪ፣ የአምንስቲ ጥያቄ።አቡጃ-በኢትዮጵያ በኩል ያለፈ አደንዛዥ ዕፅ ሌጎስ ላይ ተያዘ።ቫቲካን-የእስራኤል-ሒዝቡላሕ ዉጊያና የርዕሠ ጳጳሱ ተ ማፅዕኖ።ኒዮርክ-የዓለም መሪዎች ጥሪና የእስራኤል ሊባኖስ ዉጊያ
9/25/2024 • 11 minutes, 15 seconds የማክሰኞ መስከረም 14 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
9/24/2024 • 10 minutes, 35 seconds የዓለም ዜና፤ መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ሰኞ
--ሶማሊያ ከግብፅ ከፍተኛ መጠን ያለዉ የጦር መሳሪያን ለሁለተኛ ጊዜ ተረከበች። ግብፅ ዜጎችዋ በቶሎ ከሶማሌላንድ እንዲወጡም ጠይቃለች።--ፓኪስታን ዉስጥ የኢትዮጵያንና የሩስያ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ልዑኮች ከጥቃት መትረፋቸዉ ተመለከተ።--ሱዳን ባለፈው ነሐሴ ወር ብቻ በኮሌራ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 388 ከፍ ማለቱ ተነገረ። በወረርሽኙ ወደ 13,000 ሰዎች ተይዘዋል።--እስራኤል በሊባኖስ እያካሄደች ያለዉ ጥቃት 'አደገኛ መዘዝ' ያስከትላል ስትል ኢራን አስጠነቀቀች። በእስራኤል እና በሂዝቦላ ሚሊሻ መካከል እየጠነከረ የመጣው ዉጥረት ፤ በመካከለኛው ምስራቅ የሚታየዉን ቀዉስ እንዳያሰፋ ስጋት አሳድሯል።
9/23/2024 • 11 minutes, 38 seconds 9/22/2024 • 9 minutes, 15 seconds የመስከረም 11 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
9/21/2024 • 9 minutes, 28 seconds -የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በቅርቡ ያደረገዉ ጉባኤ፣ ዉሳኔዎቹና የባንክ ሒሳቡ በፍርድ ቤት ታገደ።-የእስራኤልና የሊባኖስ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን የሒዝቦላሕ ዉጊያ ዛሬ አይሎ ዉሏል።ሒዝቡላሕ ሰሜን እስራኤልን በሚሳዬል፣ እስራኤል ባንፃሩ የሊባኖስ ርዕሰ ከተማ ቤይሩትን በጦር ጄቶች ደብድበዋል።-የአዉሮጳ ሕብረት ለዩክሬን 35 ቢሊዮን ዩሮ ብድር ሰጠ።
9/20/2024 • 9 minutes, 21 seconds የሐሙስ መስከረም 9 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
የመስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
በደቡብ ምዕራብ ዳርፉር ውስጥ የሱዳን ጦር ባካሄደው የአየር ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። ዩናይትድ ስቴትስ የሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች በአስቸኳይ ለውይይትም እንዲቀመጡ ጠይቃለች።
የዩናይትድ ስቴትስ ሰው አልባ አውሮፕላን የመን አቅራቢያ መከስከሱን ፔንታገን አረጋገጠ። የየመን ሁቲ ሚሊሺያዎች ባለፉት ቀናት በርካታ አውሮፕላኖችን መትተው መጣላቸውን አስታውቀው ነበር።
ሊባኖስ ውስጥ በድምፅና መልእክት መቀበያ መሣሪያ ፍንዳታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ እየተነገረ ነው።
ማዕከላዊ አውሮጳን ከሁለት አስርት ዓመታት ወዲህ ያጥለቀ ለቀው አስከፊ የጎርፍ አደጋ ከሮማንያ እስከ ፖላንድ ከባድ ውድመት አስከትሏል።
9/18/2024 • 9 minutes, 50 seconds የዓለም ዜ ና፤ መስከረም 7 ቀን፤ 2017 ዓ.ም ሰኞ
DW Amharic የካይሮ መንግሥት ህወሓት እና ኤርትራን ማደራደር እንደሚፈልግ ተመለከተ። ግብፅና ኤርትራ ትስስራቸዉን ለማጠናከር ወታደራዊ ትብብር እና የመረጃ ልውውጥ ስምምነት ሊፈፅሙ እንደሚችል የግብፅ የዜና ምንጮች ዘገቡ። በጎንደር ከተማ ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በፋኖና በመንግስት ወታደሮች መካከል ውጊያ ሲካሄድ መዋሉን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል ቱርክ አንካራ ላይ ሊደረግ የታቀደው ሦስተኛ ዙር ዉይይት ለሌላ ጊዜ መተላለፉን የሶማልያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተናገሩ። ደቡብ ሱዳን በጎረቤቷ ሱዳን በኩል ወደ ውጭ ሃገር የነዳጅ ምርትን ለመላክ እና እንደገና ለማስጀመር እየሰራች መሆኑ ተነገረ።
9/17/2024 • 10 minutes, 41 seconds DW Amharic የመስከረም 6 ቀን 2017 የዓለም ዜና
አዲሱ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 16 የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማገዱ አስታወቀ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ብልጽግና ፓርቲ አባላቱን ሲያሰለጥን እንዳለፈው ዓመት “ከመንግሥት ካዝና ገንዘብ አውጥቶ” እየከፈለ ነው ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ወነጀለ።የኬንያ ዋና ኦዲተር ሀገሪቱ ከተለያዩ ወገኖች የተበደረችውን ዕዳ ኦዲት ማድረግ መጀመሩን የፋይናንስ ሚኒስትሩ ተናገሩ ። በምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ በጣለ ከባድ ዝናብ እና ባስከተለው ጎርፍ ምክንያት ከ500 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ የተመ አስታወቀ።
9/16/2024 • 9 minutes, 45 seconds 9/15/2024 • 9 minutes, 25 seconds የመስከረም 4 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
9/14/2024 • 10 minutes, 9 seconds የዓርብ መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
DW Amharic-በኮሬ ዞን በእገታ ላይ የነበሩ አራት አርሶ አደሮች መገደላቸው፤በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን አንድ ድልድይ በመደርመሱ፤ ዞኑን ከአጎራባች አካባቢዎች ጋር የሚያገናኝ መንገድ አገልግሎት እንደማይሰጥ መገለፁ፤የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት የሀገራቸውን ፓርላማ መበተናቸው፤መካከለኛው አውሮፓ በመጭው ቅዳሜና እሁድ በሚጥለው ከባድ ዝናብ ለከፍተኛ የጎርፍ ይጋለጣል መባሉ፤የሰሜን ኮሪያው መሪ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የኒውክሌር ማብላያ እና የዩራኒየም ማበልፀጊያ ቦታዎችን መጎብኘታቸው፤ዶናልድ ትራምፕ ከተፎካካሪያቸው ካማላ ሀርስ ጋር ሌላ የምርጫ ክርክር እንደማያደርጉ ማስታወቃቸው የዛሬው የዓለም ዜና ያካተታቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።
9/13/2024 • 10 minutes, 45 seconds የመስከረም 2 ቀን ፣ 2017 ዓ.ም.የዓለም ዜና