Winamp Logo
የወጣቶች ዓለም | Deutsche Welle Cover
የወጣቶች ዓለም | Deutsche Welle Profile

የወጣቶች ዓለም | Deutsche Welle

Amharic, Personal/Lifestyle/Family, 1 season, 138 episodes, 22 hours, 56 minutes
About
የወጣቶች ክፍለ ጊዜ ነው።
Episode Artwork

ከባድ አካል ጉዳተኛ ልጅን የምትንከባከበዋ ወጣት

ትዕግሥት ዱባይ ውስጥ አንድ ከባድ የአካል ጉዳተኛ ልጅን የምትንከባከብ ኢትዮጵያዊት ወጣት ናት። ሀገር ውስጥ አማራጭ ማጣቷ ወደ ስደት እንደዳረጋት የምትናገረው ይቺው ወጣት ሥለ ሥራዋ ፈተና እና ሌሎችን ለመርዳት ያላት ፍቅር ገልፃልናለች።
5/17/20249 minutes, 12 seconds

ማላዊ ለምን ወጣቶቿን ለስራ ወደ እስራኤል ትልካለች?

የማላዊ መንግሥት ስምምነቱ ለወጣት ዜጎቹ ጥሩ የሥራ እድል የሚፈጥር ብቻ ሳይሆን ሀገሪቱም ከውጭ ምንዛሬ ትርፋማ የምትሆንበት ነው ይላል። የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ግን እቅዱን ተችተዋል።
5/10/202410 minutes

«328 ዋሻዎች አግኝቼያለሁ» የዋሻ ተመራማሪ ናስር አህመድ

የዋሻ ተመራማሪ የሆነው ወጣት ናስር አህመድ በስሙ ናሲኦል የሚለው ዋሻ ከተሰየመ አራት አመት ሆነው። ዋሻው ኢትዮጵያ ውስጥ ካገኛቸው በውበቱ ልዩ የሆነዉ ብቻ ሳይሆን በቅርብ ወራት ለሀገር ጎብኝዎች ክፍት እንደሚሆን ገልፆልናል።
5/3/202410 minutes
Episode Artwork

ዐይነ ሥውሩ የስፖርት ዘጋቢ በሀዋሳ ኤፍ ኤም 97.7

4/19/20247 minutes, 12 seconds
Episode Artwork

ዐይነ ሥውሩ የስፖርት ዘጋቢ በሀዋሳ ኤፍ ኤም 97.7

oይነሥውር መሆኑ የስፖርት ዘገባ ከመሥራት እንዳላገደው ይናገራል።ጋዜጠኛ መረጃዎችን አሰባስቦ እና ተንትኖ ለአድማጮቹ የሚያደርስ መሆኑን የጠቀሰው ሙሉቀን “ እኔ ይህንኑ የዘገባ ሥራ ለዛውም በስፖርት ዘርፍ እየሠራሁ እገኛለሁ, እይታን ከሚፈልጉ ከኮሜንታተርነት እና ከዳኝነት ሥራዎች በስተቀር አንድ አይነ ሥውር ስፖርትን መዘገብ ይችላል» ብሏል ፡፡
4/19/20247 minutes, 12 seconds
Episode Artwork

ዛሬ ላይ ያለው የሩዋንዳ ወጣት በሀገሩ ስለተፈፀመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ ምን ያውቃል? ምንስ ይላል?

ሩዋንዳ ውስጥ የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ 30ኛ ዓመት ባለፈው ሳምንት እሑድ ታስቧል። ይህ አሳዛኝ ድርጊት በወቅቱ ባልተወለደው ወይም የዛሬው የሩዋንዳ ወጣት ላይ አሁንም ድረስ ተዕፅኖ እንዳለው የዶይቸ ቬለ ባልደረባ አይዛክ ሙጋቤ የጻፈው ዘገባ ይጠቁማል።
4/12/20248 minutes
Episode Artwork

የሩዋንዳ የዘር ማጥፋት 30ኛ ዓመት እና አዲሱ ትውልድ

ሩዋንዳ ውስጥ የተፈፀመው የዘር ማጥፋት ዘመቻ 30ኛ ዓመት ባለፈው ሳምንት እሑድ ታስቧል። ይህ አሳዛኝ ድርጊት በወቅቱ ባልተወለደው ወይም የዛሬው የሩዋንዳ ወጣት ላይ አሁንም ድረስ ተዕፅኖ እንዳለው የዶይቸ ቬለ ባልደረባ አይዛክ ሙጋቤ የጻፈው ዘገባ ይጠቁማል።
4/12/20248 minutes
Episode Artwork

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የሥነ ውበት እይታ

አዳጊ ሴቶች በሥነ ውበት ላይ ያላቸው ግንዛቤ ፣ ከፅንሰ ሀሳቡ ጀምሮ ሥለውበት አጠባበቅ ያላቸው እይታ እንደየአመለካከታቸው ሊለያይ ይቻላል ፡፡ በሀዋሳ ከተማ የ2ኛ ደረጃ ተማሪ የሆኑት የአብሥራ እና ሽታዬ በተመሳሳይ ዕድሜና የትምህርት ደረጃ ላይ የሚገኙ ቢሆንም ሥለውበት ያላቸው አመለካከት የተለያየ ነው፡፡
4/5/202410 minutes
Episode Artwork

የአዳጊ ሴቶች የሥነ ውበት እይታ

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰዱትን ገንዘብ ወደ አቋማሪ ድርጅቶች ያዛወሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 6 ቀን፣ 2016 በገጠመው ቀውስ ገንዘብ ያዘዋወሩ ደንበኞቹ የወሰዱትን እንዲመልሱ የሰጠው ቀነ-ገደብ ነገ ቅዳሜ ይጠናቀቃል። በወቅቱ ገንዘብ ካዘዋወሩ መካከል 57 በመቶው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አስታውቋል። ከባንኩ የወሰዱትን ገንዘብ ወደ አቋማሪ ድርጅቶች ያዘዋወሩ ተማሪዎች በተሰጣቸው ቀነ-ገደብ መሠረት መመለስ ባለመቻላቸው ሥጋት ውስጥ ገብተዋል።
3/29/202410 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የወሰዱትን ገንዘብ ወደ ቁማር ድርጅቶች ያዛወሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች አጣብቂኝ ውስጥ ገብተዋል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዕክል በገጠመው ወቅት ገንዘብ ያዘዋወሩ ደንበኞቹ የወሰዱትን እንዲመልሱ የሰጠው ቀነ-ገደብ ቅዳሜ ይጠናቀቃል። የወሰዱትን ገንዘብ ወደ አቋማሪ ድርጅቶች ያዘዋወሩ ተማሪዎች በተሰጣቸው ቀነ-ገደብ መመለስ ባለመቻላቸው ሥጋት ውስጥ ገብተዋል። በቴሌ-ብር ወደ አቋማሪ ድርጅቶች የተላለፈውን ገንዘብ ንግድ ባንክ እንዲያስመልስ ይሻሉ።
3/29/202410 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

ትምህርት ለመማር እየተማፀኑ ያሉ የባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የመጀመሪያ ዓመት ተማሪዎች

የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንግዶቻችን በ2016 ዓ/ም በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ገብተው እንዲማሩ የተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች ናቸው። ይሁንና እስካሁን ትምህርት አለመጀመራቸው እንዳሳሰባቸው በመግለፅ መፍትሔ እንዲሰጣቸው ይጠይቃሉ። እስካሁን ከሚለከታቸው አካላት ያገኙት ምላሽ ግን በትዕግስት ጠብቁ የሚል ነው።
3/22/20249 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

የዓለም ወጣቶች ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያን ወክለው የተሳተፉ ወጣቶች

ለአንድ ሳምንት ያህል የዘለቀው እና ሩሲያ የተካሄደው የዓለም ወጣቶች ፌስቲቫል ባለፈው ሳምንት ሀሙስ ተጠናቋል። በዚህ ፌስቲቫል ላይ ኢትዮጵያን ወክለው 70 የሚሆኑ ወጣት ኢትዮጵያውያን ተካፍለው ነበር።ስለ ፌስቲቫሉ እና ተሞክሯቸው ጠይቀናል።
3/15/202410 minutes
Episode Artwork

የፍቅር ጓደኛ መተዋወቂያ መተግበሪያዎች ፤ ጥቅምና ጉዳታቸው

ሰዎች ይፋቀራሉ፣ ሲልም ትዳር ይመሰርታሉ። አንዳንዶች የትዳር አጋራቸውን የሚፈልጉት በዘመናዊው መንገድ - ኦንላይን ላይ ነው። «ጥሩና ጊዜ ቆጣቢ ነው» የሚሉ እንዳሉ ሁሉ መጥፎ ጎኑ የሚያመዝንባቸውም አሉ። የሀገር ውስጥም ይሁኑ የውጭ ሀገር የፍቅረኛ ማገናኛ መተግበሪያዎች መሠረታዊ የሆኑ መረጃዎችን ይጠይቃሉ። ይሁንና ሁሉም ሰው ሀቀኛ አይደለም።
3/1/202410 minutes
Episode Artwork

የ3000 ሜትር አሸናፊዎቹ ሂሩት እና ሰለሞን

ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት በፈረንሳይ ሊቫ በተለያዩ ርቀቶች በተካሄዱ የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ሆነዋል። ከእነዚህ አሸናፊ አትሎቶች መካከል ሁለቱ የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንግዶቻችን ናቸው
2/23/202410 minutes, 13 seconds
Episode Artwork

የ3000 ሜትር አሸናፊዎቹ ሂሩት እና ሰለሞን

ከሁለት ሳምንት ገደማ በፊት በፈረንሳይ ሊቫ በተለያዩ ርቀቶች በተካሄዱ የቤት ውስጥ የሩጫ ውድድሮች ኢትዮጵያውያን አሸናፊ ሆነዋል። ከእነዚህ አሸናፊ አትሎቶች መካከል ሁለቱ የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንግዶቻችን ናቸው።
2/23/202410 minutes, 13 seconds
Episode Artwork

«ራዲዮ የብርቅ እቃ ነው»

ለቻይና ወጣቶች ራዲዮ ያለው ትርጓሜ እየቀነሰ ነው። በሀገሪቱ ከ2000 በላይ የራዲዮ ጣቢያዎች ቢኖሩም ወጣቶች መረጃ የሚፈልጉት የኦንላይን መገናኛ ብዙኃን ላይ ነው። ለኢትዮጵያውያን ወጣቶችስ ራዲዮ ምን ያህል ወሳኝ የመረጃ ምንጭ ነው?
2/16/202410 minutes
Episode Artwork

ራዲዮ በወጣቱ ዘንድ ያለው ተሰሚነት ምን ይመስላል?

ለቻይና ወጣቶች ራዲዮ ያለው ትርጓሜ እየቀነሰ ነው። በሀገሪቱ ከ2000 በላይ የራዲዮ ጣቢያዎች ቢኖሩም ወጣቶች መረጃ የሚፈልጉት የኦንላይን መገናኛ ብዙኃን ላይ ነው። ለኢትዮጵያውያን ወጣቶችስ ራዲዮ ምን ያህል ወሳኝ የመረጃ ምንጭ ነው?
2/16/202410 minutes
Episode Artwork

የስልክ ሱስ

በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው ሰዎች በየዕለቱ በአማካይ ሦስት ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከስልካቸው ጋር ጊዜ ያሳልፋሉ። ለመሆኑ በቀን ስልካችሁ ላይ ምን ያህል ጊዜ ታጠፋላችሁ? ስልክ ሱስ ሆኖብኝ ይሆን እንዴ ብላችሁስ ራሳችሁን ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?
2/9/202410 minutes, 10 seconds
Episode Artwork

ለምን ያህል ጊዜ ስልክ በቀን ይመከራል?

በቅርቡ የወጣ አንድ ጥናት እንደሚጠቁመው ሰዎች በየዕለቱ በአማካይ ሦስት ሰዓት ከ15 ደቂቃ ከስልካቸው ጋር ጊዜ ያሳልፋሉ። ለመሆኑ በቀን ስልካችሁ ላይ ምን ያህል ጊዜ ታጠፋላችሁ? ስልክ ሱስ ሆኖብኝ ይሆን እንዴ ብላችሁስ ራሳችሁን ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?
2/9/202410 minutes, 10 seconds
Episode Artwork

በሳምንት የአራት ቀን ስራ የሙከራ ፕሮጀክት በጀርመን

ከትናንት ጀምሮ ጀርመን ውስጥ የሚገኙ 45 ድርጅቶች በአንድ የሙከራ ፕሮጀክት መሳተፍ ጀምረዋል። ይኼውም ሰራተኞቻቸው እንደተለመደው በሳምንት አምስት ቀናት ሳይሆን አራት ቀናት ብቻ እየሰሩ ተመሳሳይ ደሞዝ ይከፈላቸዋል። የዚህ የሙከራ ፕሮጀክት ዓላማ ለሰራተኛው ተጨማሪ የዕረፍት ቀን መጨመር ብቻ ሳይሆን የድርጅቱንም ምርታማነት ማሳደግ ነው።
2/2/202410 minutes
Episode Artwork

የትምህርት ጥቅም እና ሚና

የተመድ ዕሮብ ታስቦ የዋለውን ዓለም አቀፍ የትምህርት ቀን በማስታወስ ባወጣው መግለጫ አፍጋኒስታን ውስጥ ሴቶችን ከትምህርት ገበታ ማግለል ሁሉንም የሀገሪቱን ዜጋ እንደሚጎዳ አስታውቋል። ኢትዮጵያ የአፍጋኒስታን አይነት ችግር ባይኖራትም በሀገሪቱ በነበረና ባለ ጦርነት የተነሳ አሁንም በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን መከታተል አልቻሉም።
1/30/202410 minutes
Episode Artwork

ዓለም አቀፍ የትምህርት ቀን

የተመድ ዕሮብ ታስቦ የዋለውን ዓለም አቀፍ የትምህርት ቀን በማስታወስ ባወጣው መግለጫ አፍጋኒስታን ውስጥ ሴቶችን ከትምህርት ገበታ ማግለል ሁሉንም የሀገሪቱን ዜጋ እንደሚጎዳ አስታውቋል። ኢትዮጵያ የአፍጋኒስታን አይነት ችግር ባይኖራትም በሀገሪቱ በነበረና ባለ ጦርነት የተነሳ አሁንም በብዙ ሺ የሚቆጠሩ ተማሪዎች ትምህርታቸውን መከታተል አልቻሉም።
1/26/202410 minutes
Episode Artwork

1000 ጥንዶች ጋብቻ የሚፈፅሙበት ሰርግ

እንደሚታወቀው ኢትዮጵያ ውስጥ የጥር ወር በርካታ ወጣት ጥንዶች ጋብቻ የሚመሰርቱበት ወር ነው። የዘንድሮውን ወር ለየት የሚያደርገው ደግሞ የፊታችን እሁድ 1000 ጥንዶች በአዲስ አበባ አብረው ጋብቻቸውን የሚፈፅሙበት መሆኑ ነው። የዝግጅቱ ዓላማ ወጪን መቀነስ ብቻ ሳይሆን ከዛም በላይ ያለመ ነው።
1/12/20249 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

የሺ ጋብቻ

የአርቲስት አደም መሐመድ የሙዚቃ ህይወት

1/5/20249 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

አርአያ እና ሁለገብ የሙዚቃ ሰው ፤ አደም መሐመድ

የየማህበረሰባቸውን ባህል ወግ እና ስረዓት በሙዚቃቸው ለማሳየት፣ ብሎም ለማሳደግ ለሚውተረተሩቱ ደግሞ ፈተናው በዚያው ልክ ነው። አደም እንደሚለው እርሱ ተወልዶ ያደገበት ማህበረሰብ ያለው ቱባ ባህል መገለጥ በሚገባው ልክ አለመገለጡ እርሱ እና መሰሎቹ የበለጠ እንዲተጉ ገፋፍቷቸዋል።
1/5/20249 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች : የሴት ልጅ አለባበስ ከፆታዊ ጥቃት ያድናል?

የሴት ልጅ የአለባበስ ሁኔታ ለተለያዩ አይነት ጾታዊ ትንኮሳዎች ብሎም ለጾታዊ ጥቃት ለመዳረግ ገፊው ምክኒያት የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው የሚሉ እንዳሉ ሁሉ የሴት ልጅ አለባበስ ለጾታዊ ጥቃት ሊዳርጋት አይገባም፤ መንስኤውም ሆኖ ሊቀርብ አይችልም የሚሉ አሉ።
12/29/202312 minutes, 2 seconds
Episode Artwork

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች : የሴት ልጅ አለባበስ ከፆታዊ ጥቃት ያድናል?

የሴት ልጅ የአለባበስ ሁኔታ ለተለያዩ አይነት ጾታዊ ትንኮሳዎች ብሎም ለጾታዊ ጥቃት ለመዳረግ ገፊው ምክኒያት የመሆን እድሉ ከፍተኛ ነው የሚሉ እንዳሉ ሁሉ የሴት ልጅ አለባበስ ለጾታዊ ጥቃት ሊዳርጋት አይገባም፤ መንስኤውም ሆኖ ሊቀርብ አይችልም የሚሉ አሉ።
12/28/202312 minutes, 2 seconds
Episode Artwork

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የአቻ ጓደኝነት ተፅዕኖ የትኛው ጎኑ ያመዝናል?

አዳጊ ሴቶች በትምህርት ቤት ወይም በመኖሪያ አካባቢያቸው የአቻ ጓደኝነት ሊመሠረቱ ይችላሉ ፡፡የሚመሠረተው የአቻ ጓደኝነት ግን በአዳጊዎቹ ህይወት ላይ አዎንታዊ ወይንም አሉታዊ ተፅዕኖ ማሳደሩ አይቀርም ፡፡ የትኛው ጎኑስ ያመዝናል?
12/22/202310 minutes, 27 seconds

«ስኬታማ መሆን ማለት ከሀገር መውጣት ይመስለኝ ነበር።» መሠረት ንጉሤ

«ስኬታማ መሆን ማለት ከሀገር መውጣት ይመስለኝ ነበር።» ትላለች የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንግዳችን። ይህን አመለካከቷን እንዴት መቀየር እንደቻለች እና የሕይወት ተሞክሮዋን ታጫውተናለች።
12/15/20239 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

የሥዕብና ስልጠናዎችን እንዴት ማግኘት ይቻላል?

«ስኬታማ መሆን ማለት ከሀገር መውጣት ይመስለኝ ነበር።» ትላለች የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንግዳችን። ይህን አመለካከቷን እንዴት መቀየር እንደቻለች እና የሕይወት ተሞክሮዋን ታጫውተናለች።
12/15/20239 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የ12ኛ ክፍል ፈተና ክርክር

በታዳጊነት እድሜ የሚገኙ አራት ተማሪዎችን በዚሁ ጉዳይ ላይ ልናከራክራቸው ወደናል፡፡ ተማሪዎቹ ጠንከር ያለውን የ12ኛ ክፍል የፈተና አሰጣጥና በርካቶችን ከዩኒቨርሲቲ መግቢያ ያራቀውን ውጤት በሁለት መልኩ አይተው ትችትና ሙገሳቸውን ችረውታል፡፡
12/8/202310 minutes, 53 seconds

ሳዑዲ አረቢያ ውሰጥ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ

በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች አሁን ድረስ እንደሚገኙ እዛው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ይናገራሉ። «ፍትሕ ለእስረኞች» ወይም «ድምፅ ሁኗቸው» የሚሉትም ብዙ ናቸው። የታሳሪ ቤተሰቦች እንደሚሉት አብዛኞቹ ታሳሪዎች ወጣቶች እና ወንዶች ናቸው።
12/1/20239 minutes
Episode Artwork

የ12ኛ ክፍል ውጤት እና የትምህርት ምዘና እና ፈተና አገልግሎት ምላሽ

ኢትዮጵያ ውስጥ በ2015 የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተናን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 50 በመቶ እና ከዛ በላይ ያመጡት ተማሪዎች 3,2 በመቶ ያህሉ ብቻ እንደሆኑ ትምህርት ሚኒስቴር ማስታወቁ ይታወሳል። በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት በዚሁ ጉዳይ ላይ ተማሪዎችን፣ መምህራንን እና የትምህርት ምዘና እና ፈተና አገልግሎትን ጠይቀናል።
12/1/202311 minutes, 27 seconds
Episode Artwork

ሳዑዲ አረቢያ ውሰጥ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ጉዳይ

በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የሳዑዲ አረቢያ እስር ቤቶች አሁን ድረስ እንደሚገኙ እዛው የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ይናገራሉ። «ፍትሕ ለእስረኞች» ወይም «ድምፅ ሁኗቸው» የሚሉትም ብዙ ናቸው። የታሳሪ ቤተሰቦች እንደሚሉት አብዛኞቹ ታሳሪዎች ወጣቶች እና ወንዶች ናቸው።
12/1/20239 minutes
Episode Artwork

በዓለም ላይ የሴቶችና ልጃገረዶች ግድያ እየጨመረ ነው

ሰሞኑን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ይፋ እንዳደረገው ባለፈው የጎርጎሮሲያዊያኑ 2022 ዓ ም በዓለም ላይ የተገደሉት ሴቶች እና ልጃገረዶች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። ወደ 89,000 የሚጠጉ ሴቶች እና ልጃገረዶች ሲገደሉ 20, 000 የሚሆኑት ደግሞ የተገደሉት አፍሪቃ ውስጥ ነው።
11/24/202310 minutes, 11 seconds

የአማራ ክልል የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብሶት እና ጥያቄ

በተለያዩ የአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ተመድበው ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች እስካሁን ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ አለመቻላቸውን ለዶይቸ ቬለ ድምፅ ሁኑን ሲሉ ሰሞኑን ቅሬታቸውን ገልፀዋል። ተማሪዎቹ ዩኒቨርስቲዎቹ ሳይጠሯቸው እቤት ከተቀመጡ በርካታ ወራት እየተቆጠረ መሆኑ ስጋት ላይ ጥሏቸዋል። ከሚመለከተው አካልም እስካሁን ምላሽ ማግኘት አልቻሉም።
11/17/202310 minutes
Episode Artwork

እቤት መቀመጥ የሰለቻቸው የአማራ ክልል የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ብሶት እና ጥያቄ

በተለያዩ የአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ተመድበው ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች እስካሁን ወደ ትምህርት ገበታቸው መመለስ አለመቻላቸውን ለዶይቸ ቬለ ድምፅ ሁኑን ሲሉ ሰሞኑን ቅሬታቸውን ገልፀዋል። ተማሪዎቹ ዩኒቨርስቲዎቹ ሳይጠሯቸው እቤት ከተቀመጡ በርካታ ወራት እየተቆጠረ መሆኑ ስጋት ላይ ጥሏቸዋል። ከሚመለከተው አካልም እስካሁን ምላሽ ማግኘት አልቻሉም።
11/17/202310 minutes
Episode Artwork

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ገንዘብ ወይስ ጥረት?

ለመሆኑ በታዳጊዎች አስተዳደግ ውስጥ የቤተሰብ የገቢ ሁኔታ እንዴት ያለ ሚና ይኖረው ይሆን የሚለው ዛሬ ታዳጊዎች ሁለት ጎራ ይዘው የሚሞግቱበት ነው፡፡ አወያይዋ የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዝግጅት ዘጋቢ ሱመያ ሳሙኤል ናት።
11/12/202310 minutes, 38 seconds
Episode Artwork

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ገንዘብ ወይስ ጥረት?

ወጣቶች በታዳጊነት ዘመናቸው የተለያዩ የህይወት ምዕራፎች ውስጥ ያልፋሉ። እያንዳንዱ ወጣት ግን የህይወት ምዕራፉን ፈተና በእኩል ጥረት፤ በእኩልም ብርታት ያልፋል ማለትም አይደለም፡፡ለመሆኑ በታዳጊዎች አስተዳደግ ውስጥ የቤተሰብ የገቢ ሁኔታ እንዴት ያለ ሚና ይኖረው ይሆን የሚለው ዛሬ ታዳጊዎች ሁለት ጎራ ይዘው የሚሞግቱበት ነው፡፡
11/10/202310 minutes, 38 seconds
Episode Artwork

ከጦርነት ጠባሳዎች በማገገም ላይ ያሉ ወጣቶች

ከሁለት ዓመት በላይ የዘለቀው እና በትግራይ ክልል የተጀመረው የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት በሰላም ስምምነት ከተቋጨ አንድ ዓመት ሆኖታል። ይሁንና ጦርነቱ በተካሄደበት አካባቢ የነበሩ ወጣቶች ፣ጦርነቱ ካስከተለባቸው የስነ ልቦና ችግሮች ለማገገም ገና ብዙ ጊዜ እንደሚሹ ገልጸውልናል።
11/3/202310 minutes, 2 seconds

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ፆታዊ ተፅኖዎች መቼ ይጀምራሉ?

ፆታዊ ተፅኖዎች መቼ ይጀምራሉ? በሴቶች እና ወንዶች መካከል ፆታን መሠረት ያደረጉ ልዩነቶችና ፆታዊ ተፅኖዎች ከቤተሰብ ይጀምራሉ “ ይላሉ የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አመርቲ ጎበና እና በጸሎት ውብሽት ፡፡
10/27/202310 minutes, 39 seconds
Episode Artwork

«ጨው እና ወርቅ ላይ ተኝተን በርሃብ እየሞትን ነው» በአፋር ክልል ለተቃውሞ የወጡ ወጣቶች

አሁን ያለው የአፋር መንግሥትን የሚቃወሙ ወጣቶች ከፍተኛ በደል እየደረሰባቸው እንደሆነ ለዶይቸ ቬለ ገልፀዋል። በወጣቶች ዓለም ዝግጅት ያነጋገርናቸው ወጣቶች እንደሚሉት ከሆነ፤ ከሰሜኑ ጦርነት በደንብ ባላገገመው አፋር ክልል ከፍተኛ የመልካም አስተዳደር እጦት አለ፣ ወጣቶች ላይም እስራት እና አፈና ይካሄዳል። የክልሉ መንግሥት ይህን ያጣጥላል።
10/13/202310 minutes, 54 seconds
Episode Artwork

የሀዋሳ ወጣቶች የኪነ ጥበብ መድረክ

10/6/20238 minutes, 41 seconds
Episode Artwork

መውሊድን እና መስቀልን ከቤተሰብ ጋር

ይህ ሳምንት ሁለት ትላልቅ ኃይማኖታዊ በዓላትን ያስተናገደ ነበር። በተለይ ዕሮብ ዕለት ኢትዮጵያዉያን ሙስሊሞች የነቢዩ መሐመድ ልደትን ሲያከብሩ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ክርስቲያኖች ደግሞ ደመራ እና መስቀልን አክብረዋል።
9/29/202310 minutes

የትናንት ወጣቶች ለዛሬ ወጣቶች የአርአያነት መንገድ ለተቀዛቀዘው ሰብአዊነት

9/22/20239 minutes, 5 seconds
Episode Artwork

የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ መቀዛቀዝ እና ዘመን ተሻጋሪ ህልመኞች

ሰዎች ለሰዎች በጎደላቸው፣ አቅም ባነሳቸው እና በህመም ተይዘው በደከሙ ጊዜ ያለው በገንዘቡ ፣ የሌለው በጉልበቱ አልያም በሃሳቡ በቻሉት መንገድ ይረዳዳሉ ፤ ይደጋገፋሉ ። ይህ ሰዋዊ ባህሪ ነውና ድንበር ሳያግደው፣ ጎሳ እና ኃይማኖትም ሳያቆመው በመላው ዓለም በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ይከወናል ። መልካምነት የጤናማ ስብዕና መገለጫ ነውና።
9/22/20239 minutes, 5 seconds
Episode Artwork

የወጣቶች የአዲሱ ዓመት ተስፋ እና ስጋት

«በ2016 ሰላማዊ የሆነች ምድርን ማየት እናፍቃለሁ።ሰላማዊት ኢትዮጵያን እናፍቃለሁ።አንድነቷ አብሮነቷ ተጠብቆ የሚቆይባትን ሀገር እናፍቃለሁ።»ጋዜጠኛ መክሊት ወንድወሰን።ሌላዋ ወጣት ቤተልሄም ሀይሉ በበኩሏ«በ2016 ዓ/ም ሰዎች ከቀያቸው ተፈናቀሉ፣ረብሻ ተፈጠረ ጦርነት አለ የሚሉ ዜናዎችን ባንሰማ»በማለት ምኞቷን ገልፃለች።
9/15/20238 minutes, 14 seconds
Episode Artwork

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ባህሎቻችን በአዳጊ ሴቶች አይን

በዓላትን በጋራ ማክበር ፣ እቁብ በመሰብሰብ በኢኮኖሚ መደጋገፍ ፤ እንዲሁም ለቅሶ የመሳሰሉ ችግሮች ሲያጋጥሙ በዕድር አማካኝነት ሐዘንን መጋራት አብሮነትን የሚያጠናክሩ እሴቶች እንደሆኑ ታዳጊ ረድኤት እና ናዝራዊት ይገልጻሉ፡፡
9/1/202310 minutes

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ያላጠናቀቁት የጎንደር ተማሪዎች ጉዳይ ከምን ደረሰ?

ዘንድሮ የ12ኛ ክፍልን መልቀቂያ ፈተና በጎንደር ከተማ ይወስዱ የነበሩ 16ሺ የሚሆኑ ተማሪዎች ፈተናውን ሙሉ በሙሉ እንዳልወሰዱ ይታወቃል። ታድያ የፈተናው ጉዳይ ከምን ደረሰ?
8/25/20238 minutes, 5 seconds
Episode Artwork

አሳሳቢዉ የሰዎች እገታ በኢትዮጵያ

በቡድን የተደራጁ ሰዎች ኢትዮጵያ ውስጥ በጠራራ ፀሐይ ሳይቀር በርካታ ዘረፋዎች እየፈፀሙ እንደሆነ ዶይቸ ቬለ በተደጋጋሚ ጥቆማዎች እየደረሱት ይገኛል። አብዛኛው ጊዜም በድርጊቱ ተሳትፈው የሚገኙት ወጣቶች እንደሆኑ ይታመናል።
8/18/202310 minutes
Episode Artwork

«ፈተና የተፈተነው መስኮት በጥይት እየተመታ ነው» የጎንደር ከተማ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ

በቅርቡ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ተቋማት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተሰጥቷል። ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው በጎንደር ዩንቨርስቲ 3 ካምፓሶች ግን ይፈተኑ የነበሩ 16 ሺህ ተማሪዎች በከተማዋ በነበረ ውጊያ ፈተናውን ሳይወስዱ ቀርተዋል። በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ይህንን ፈተና በአራት ተቋማት የወሰዱ ተማሪዎችን አነጋግረናል።
8/12/202310 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

«ፈተና የተፈተነው መስኮት በጥይት እየተመታ ነው» የጎንደር ከተማ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ

በቅርቡ በተለያዩ የኢትዮጵያ ከፍተኛ ተቋማት የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ተሰጥቷል። ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ እንዳደረገው በጎንደር ዩንቨርስቲ 3 ካምፓሶች ግን ይፈተኑ የነበሩ 16 ሺህ ተማሪዎች በከተማዋ በነበረ ውጊያ ፈተናውን ሳይወስዱ ቀርተዋል። በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ይህንን ፈተና በአራት ተቋማት የወሰዱ ተማሪዎችን አነጋግረናል።
8/11/202310 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

ኢትዮጵያዉያን በሀገራቸዉ ዜጎች የሚደርስባቸዉ በደል በሳዑዲ አረቢያ

ኢትዮጵያውያን በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሲሰደዱ ስለሚደርስባቸው የተለያዩ ፈተናዎች ዶይቸ ቬለ ከዚህ ቀደም ደጋግሞ ዘግቧል። ዛሬ ደግሞ እነዚህ ሰዎች እዛ ከገቡ በኋላ እንዴት በወገኖቻቸው እየተበደሉ እንዳለ እና መሻሻል ስለሚገባቸው ነገሮች እንመለከታለን።
8/4/202310 minutes
Episode Artwork

ኢትዮጵያዉን በወገኖቻቸዉ የሚደርስባቸዉ በደል በሳዑዲ አረቢያ

ኢትዮጵያውያን በሕገ ወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሲሰደዱ ስለሚደርስባቸው የተለያዩ ፈተናዎች ዶይቸ ቬለ ከዚህ ቀደም ደጋግሞ ዘግቧል። ዛሬ ደግሞ እነዚህ ሰዎች እዛ ከገቡ በኋላ እንዴት በወገኖቻቸው እየተበደሉ እንዳለ እና መሻሻል ስለሚገባቸው ነገሮች እንመለከታለን።
8/4/202310 minutes
Episode Artwork

የተንጨላጨለ ስራ የማግኘት ተስፋ

ከተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዘንድሮም በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ተማሪዎች እየተመረቁ ይገኛሉ። ይሁንና ስራ የማግኘት እድላቸው አጠያያቂ ነው። «ተማሪውን የሚያስጨንቀው ሥራ አገኛለሁ ወይ የሚለው ሳይሆን ቤተሰቤን ተመርቄ እንዴት አስደስታለሁ የሚለው ነው። » ይላል ከተመራቂዎቹ አንዱ ለዶይቸ ቬለ።
7/28/202310 minutes
Episode Artwork

የመነመነዉ ስራ የማግኘት ተስፋ

ሁኔታዎች ያልገደቧት «ሰቃይዋ» ተማሪ እና ህልሟ

የዩኒቨርሲቲ ትምህርቷን የታላቅ ወንድሟን እና እህቷን ፈለግ በመከተል የነርስ ሙያ ለመከታተል ነበር ነቀምቴ ወደ ሚገኘው የሪፍት ቫሊ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ቅርንጫፍ ያመራችው ። በውጣ ውረድ ውስጥ ያሳለፈቻቸው የትምህርት ዓመታት ኦብሲኔትን አልከዷትም።
7/21/20238 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

የቀርከሃ ብስክሌቶች

7/14/20239 minutes, 54 seconds
Episode Artwork

የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች በተለያየ ሁኔታ ውስጥ ለፈተና እየተዘጋጁ ነው

7/7/20238 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

የወጣቶቹ ጥናት እና ምርምር በተስፋ እና ስጋት መካከል

6/30/20239 minutes, 52 seconds
Episode Artwork

ኒው ሚሊኒየም ውመን ኢምፓወርመንት

ከከተማ ወደ ገጠራማው የኢትዮጵያ ክፍል በተሔደ ቁጥር ሴቶት የሚገጥማቸው ፈተና መጨመሩ አይቀሬ ነው። ስለሆነም ኒው ሚሊኒየም ውመን ኢምፓወርመንት የተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሴቶች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን በማስቆም ፣በጤና፣ በኢኮኖሚ እና ትምህርት ዘርፎች ላይ ይሳተፋል።
6/23/20239 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

ለሴቶችን መብት የሚሟገተዉ ድርጅት

የኪነ ህንፃ ባለሙያው ኃይሌ ታደሰ እና ትላልቅ ስራዎቹ

የኪነ ህንፃ ባለሙያ የሆነው ኃይሌ ታደሰ በኢትዮጵያ ትላልቅ የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ባለፉት ሶስት ዓመታት ለመስራት ችሏል። ከእነዚህም አንዱ በደቡብ ምዕራብ ክልል በኮንታ ዞን የሚገኘው የኮይሻ ፕሮጀክት ነው። ስለተሳተፈባቸው ትልልቅ ፕሮጀክቶች፣ ስለስኬቶቹና ሌሎች ወጣቶች እንዴት ለዚህ ሙያ ራሳቸውን ማነቃቃት እንደሚችሉ አጫውቶናል።
6/16/20239 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

«ሰው እንደሁ መረጃ ፈልፍሎ ማግኘቱ አይቀርም»

ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ ፌስቡክ፣ ቴሌግራም፣ ቲክ ቶክ እና ዩቲዩብ የመሳሰሉ የተመረጡ የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ከታገዱ እንሆ አራት ወር ሆናቸው። ረዥም ጊዜ ያስቆጠረውን እገዳ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሉ ወጣቶች እንዴት እየተወጡት ነው? በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት አጠያይቀናል።
6/9/202310 minutes

«አፍሪቃን ማስተዋወቅ ነው ዓላማችን»: አቤኔዘር ታደሰ

አቤኔዘር ታደሰ የቆዳ ውጤቶችን የሚያመርት ኢትዮጵያዊ ወጣት ነው። በስሩ አምስት ወጣት ሰራተኞችን ቀጥሮ እየሰራ የሚገኘው የ25 ዓመቱ ወጣት እንደ ጀማሪ ስራ ፈጣሪ ያለፈበትን መንገድ እና ምርቶቹን ከሀገር ውስጥ አልፎ ለውጭ ገበያ ለማቅረብ እንዴት እንደበቃ አጫውቶናል።
6/2/20239 minutes, 59 seconds

አፍሪቃዊ አንድነት በሥዕል ሲገለፅ

የቀድሞው የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ትናንት ሀሙስ 60ኛ ዓመቱን አክብሯል። ይህ ቀን በአፍሪቃ ህብረት አዳራሽ ብቻ ሳይሆን ሰሞኑን «አፍሪቃዊ ማንነት የሥዕል ትርዒት » በሚል መሪ ቃል አዲስ አበባ ውስጥ ለአራት ቀናት በቆየ የሥዕክ አውደ ርዕይ ተከብሯል።
5/26/202310 minutes, 24 seconds
Episode Artwork

በቲክቶክ የሚሰራጩ ምክሮች ምን ያህል ጠቃሚ ናቸው?

ሌሎችም እንዲሞክሯቸው በሚል ብዙ ጠቃሚ የሚባሉ የቲክቶክ ምክሮች በመተገብሪያው ላይ በየዕለቱ ይሰራጫሉ። የውበት አያያዝ ፣ የምግብ አበሳሰል ወይም የቤት ማስዋቢያዎች ከነዚህ ጥቂቶቹ ናቸው። ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ከዚህ ምን ያህል ተጠቃሚ እየሆኑ ነው? ጠቃሚ እና ጎጂን መልዕክት እንዴት ይለያሉ?
5/19/202310 minutes

ከሊቢያ የሚመለሱት አፍሪቃውያን ስደተኞች

ወደ ኢጣሊያ በጀልባ የሚገቡት የስደተኞች ቁጥር በአራት እጥፍ ጨምሯል። አብዛኞቹ ከሰሀራ በስተ ደቡብ የሚገኙ ሃገራት ስደተኞች ተሳክቶላቸው አውሮጳ ቢደርሱ፤ ሌሎች ሜዲትራንያን ላይ ሞተው የሚቀሩ ወይም በሊቢያ በቃኝ ብለው መመለስ የሚፈልጉት ስደተኞች ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ ነው የዶይቸ ቬለዋ ማርቲና ሺቪኮቭስኪ ዘገባ የሚጠቁመው።
5/12/20239 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

ከሊቢያ የሚመለሱት አፍሪቃውያን ስደተኞች

ወደ ጣሊባን በጀልባ የሚገቡት የስደተኞች ቁጥር በአራት እጥፍ ጨምሯል። አብዛኞቹ ከሰሀራ በስተ ደቡብ የሚገኙ ሃገራት ስደተኞች ተሳክቶላቸው አውሮጳ ቢደርሱ፤ ሌሎች ሜዲትራንያን ላይ ሞተው የሚቀሩ ወይም በሊቢያ በቃኝ ብለው መመለስ የሚፈልጉት ስደተኞች ቁጥር ቀላል እንዳልሆነ ነው የዶይቸ ቬለዋ ማርቲና ሺቪኮቭስኪ ዘገባ የሚጠቁመው።
5/12/20239 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

ዜጎችን ከህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ማዳን ላይ የሚሰራው የምህረት አምባ አገልግሎት

የምህረት አምባ በህገወጥ መንገድ ወይም በሃሰተኛ ደላሎች ለሚጠቁ ኢትዮጵያውያን የቆመ ሃገር በቀል ማህበር ነው። ማህበሩ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 200 የሚሆኑ ህፃናት እና ወጣቶችን ከህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ለማዳን መቻሉን ይናገራል።
5/5/202310 minutes
Episode Artwork

የምህረት አምባ አገልግሎት

የምህረት አምባ በህገወጥ መንገድ ወይም በሃሰተኛ ደላሎች ለሚጠቁ ኢትዮጵያውያን የቆመ ሃገር በቀል ማህበር ነው። ማህበሩ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ 200 የሚሆኑ ህፃናት እና ወጣቶችን ከህገ ወጥ አዘዋዋሪዎች ለማዳን መቻሉን ይናገራል።
5/5/202310 minutes
Episode Artwork

«90ሺ ብር እየተጠየቀ ነው» ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን

በርካታ ምዕራባዊያን ሀገራት በተጠናከረ ሁኔታ ዜጎቻቸውን ከሱዳን ባስወጡበት በዚህ ሳምንት ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ «ህይወታችንን አትርፉልን » ብለው የሚጣሩት አፍሪቃውያን ቁጥር ጨምሯል። በዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ብርቱ ጦርነት በሚካሄድባት ሱዳን ውስጥ መሄጃ አጥተው የተቀመጡ ኢትዮጵያውያን በምን ሁኔታ ላይ እንዳሉ እንቃኛለን።
4/28/202310 minutes
Episode Artwork

ሱዳን የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ጥሪ

ኢድ አልፈጥርን በተለያየ ሁኔታና ሀገር

በአራት የተለያዩ ሀገራት የሚገኙ ሙስሊም ወጣቶች ስለ የዘንድሮው የረመዳን ፆም፤ ኢድ አልፈጥር አከባበር እና ረመዳንን ልዩ የሚያደርገው ነገር ገልፀውልናል። የአዲስ አበባ ነዋሪ የሆነው ሞሀመድ ወርቁ «ይህንን የረመዳን ወር ጾም በመጾም፤ ስግደት በማብዛት ፣ ያለው ለሌለው በማካፈል እና በመተዛዘን አሳልፈናል» ይላል።
4/21/20239 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

ለመጀመሪያ ጊዜ ፋሲካን ያለቤተሰብ

ቤተሰብ ከሚሰባሰብባቸው ታላላቅ በዓላት አንዱ - ፋሲካ ነው። ይሁንና ሁሉም ሰው ለበዓል ወደ ቤት መሄድ አይችልም። ልክ እንደዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ተሳታፊዎች። ለመጀመሪያ ጊዜ ፋሲካን ያለቤተሰብ ለምን እና እንዴት እንደሚያከብሩ ጠይቀናቸዋል።
4/14/20239 minutes, 57 seconds
Episode Artwork

የ«እኔ ነኝ መፍትሔው» ንቅናቄ ጠንሳሽ እና አስተባባሪዎቹ

«የማያሳብብ ፣ ትኩረቱን ራሱ ላይ ያደረገ ዜጋ መፍጠር ነው አላማችን» ይላሉ የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት ተሳታፊዎች። «እኔ ነኝ መፍትሔው » በሚል መሪ ቃል በኢትዮጵያ ስድስት ከተሞች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ እየሠሩ ይገኛሉ።
4/7/202310 minutes

«አንድ ባጃጅ ላይ 13 ሆነን ነው የመጣነው»የሳዑዲ ስደተኛ

ኢትዮጵያ ውስጥ ከመቶ ሺህ በላይ ወጣቶች ለውጭ አገር የሥራ ሥምሪት ሰልጥነው በህጋዊ መንገድ የሚሄዱበት ሁኔታ እየተመቻቸ መሆኑን መንግሥት ሰሞኑን አስታውቋል። በሌላ በኩል በሳዑዲ አረቢያ የተለያዩ እስር ቤቶች የሚገኙ ኢትዮጵያውያን አሁን ድረስ ወደ ሀገራቸው እየተመለሱ ነው። ሌሎች ደግሞ በህገ ወጥ መንገድ ወደዛው እየተሰደዱ ይገኛሉ።
3/31/202310 minutes, 2 seconds

የሮም ማራቶንን በባዶ እግሩ የሮጠው ሁለተኛው ኢትዮጵያዊ

የረዥም አመታት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ የነበረው ኤርሚያስ አየለ ባለፈው እሁድ በጣሊያን ዋና ከተማ ሮም በተካሄደው የማራቶን ውድድር በባዶ እግሩ ሮጦ አጠናቋል። ይህንን ያደረገው ለዝነኛው አበበ ቢቂላ ክብር እና ለሀገር ገጽታ ግንባታ ነው ይላል።
3/24/202310 minutes
Episode Artwork

የሮም ማራቶንን በባዶ እግሩ የሮጠው ኤርሚያስ አየለ

የረዥም አመታት የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ ስራ አስኪያጅ የነበረው ኤርሚያስ አየለ ባለፈው እሁድ በጣሊያን ዋና ከተማ ሮም በተካሄደው የማራቶን ውድድር በባዶ እግሩ ሮጦ አጠናቋል። ይህንን ያደረገው ለዝነኛው አበበ ቢቂላ ክብር እና ለሀገር ገጽታ ግንባታ ነው ይላል።
3/24/202310 minutes
Episode Artwork

ሚስ ካልቸር ኢትዮጵያ፦ ብሩክታዊት ሐብታሙ

ብሩክታዊት ሐብታሙ በአሁኑ ሰዓት ሚስ ካልቸር ኢንተርናሽናል በሚል ዓለም አቀፍ ባህላዊ የቁንጅና ውድድር ላይ ተሳታፊ ናት። ኢትዮጵያን ወክላ ለመወዳደር የበቃችውም «ሚስ ካልቸር ኢትዮጵያ» ተብላ ኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄደውን ውድድር በማሸነፏ ነው። ብሩክታዊት ለዚህ ምን ያህል ዝግጁ ናት? ሰዎችስ ለምን ለእሷ ድምጫቸውን ይስጡ?
3/17/202310 minutes
Episode Artwork

የዓለም አቀፍ ቁንጅና ተወዳዳሪዋ ብሩክታዊት ሐብታሙ

ብሩክታዊት ሐብታሙ በአሁኑ ሰዓት ሚስ ካልቸር ኢንተርናሽናል በሚል ዓለም አቀፍ ባህላዊ የቁንጅና ውድድር ላይ ተሳታፊ ናት። ኢትዮጵያን ወክላ ለመወዳደር የበቃችውም «ሚስ ካልቸር ኢትዮጵያ» ተብላ ኢትዮጵያ ውስጥ የተካሄደውን ውድድር በማሸነፏ ነው። ብሩክታዊት ለዚህ ምን ያህል ዝግጁ ናት? ሰዎችስ ለምን ለእሷ ድምጫቸውን ይስጡ?
3/17/202310 minutes
Episode Artwork

«ኃላፊነቱ የሁላችንም ነው» ማስተር አብነት ከበደ

ማስተር አብነት ከበደ ሰሞኑን በተለይ ቦረና ውስጥ ከተከሰተው ድርቅ እና ርሀብ ጋር በተያያዘ በማኅበራዊ መገናኛ ዘዴ በተደጋጋሚ ስሙ እየተነሳ ይገኛል። ወጣቱ ቦታው ድረስ በመሄድ ርዳታ ሲለግስ እና ሲያሰባስብ ተስተውሏል።
3/10/20239 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

አዳጊው የፕሮግራሚንግ ባለሙያ ኒቆዲሞስ ኤሊያስ

ኒቆዲሞስ ኤሊያስ ገና ሚኒስትሪ ፈተና እንኳን አልተፈተነም። ነገር ግን በአጭር ጊዜ ውስጥ የፕሮግራሚንግ ባለሙያ ሊሆን ችሏል። የ 14 ዓመቱ አዳጊ ወጣት እንደ ኔትፊሊክስ እና አማዞን የመሳሰሉ የተለያዩ ድረ ገጾችን አስመስሎ ሊሰራ ችሏል።
3/3/202310 minutes, 21 seconds
Episode Artwork

የቲሊሊ 12ኛ ክፍል ተፈታኞች አቤቱታ

እስካሁን ድረስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ውጤታችን አልተገለፀልንም የሚሉ የቲሊሊ ከተማ ተማሪዎች በፈተና ወቅት በተነሳ ረብሻ ምክንያትም ውጤታቸው ተሰርዟል ወይም እስካሁን ይፋ ሳይሆን ቀርቷል። ለውጤቶቹ መዘግየት(መሰረዝ) ምክንያቱ ምንድን ነው? ከትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር ምላሽ ጠይቀናል።
2/24/202310 minutes, 26 seconds

የወጣቶች ዓለም

ኢትዮጵያ ውስጥ ሰላም እንዲሰፍን መሻት ብቻ ሳይሆን የሰላም አምባሳደር ሆነው የሚሰሩ ወጣቶች የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት እንግዶቻችን ናቸው። ከጥቂት ዓመታት በፊት በበርካታ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች ዘንድ የተጫረው የሰላም እና የለውጥ ተስፋ ጊዜ የተዋወቁት እና ሰላም ላይ የሚሠሩት እነዚህ ወጣቶች አሁንም የበለጠ መሠራት እንዳለበት ያሳስባሉ።
2/17/202310 minutes, 24 seconds
Episode Artwork

ሰላምን ፍለጋ

«ሰው ቅሬታውን በፆም በፀሎት መግለፁ ነገሩን ያስተነፍሰዋል እንጂ አይጎዳም»

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ባደረገዉ ጥቁር የመልበስ ጥሪ መሠረት ሰሞኑን በርካታ የዕምነቱ ተከታዮች ወይም አጋርነታቸውን መግለፅ የፈለጉ ሰዎች ጥቁር መልበስ መከልከላቸውን በተለያየ መንገድ ይፋ ሲያደርጉ ተስተውሏል። ለመሆኑ አንድ መሥሪያ ቤት ጥቁር መልበስን መቼ ሊከለክል ይችላል? አጋርነትስ እንዴት ይገለፃል?
2/10/20239 minutes, 55 seconds

ከመላ ሀገሪቱ ከፍተኛ ነጥብ አስመዝግቧል

2/3/20239 minutes, 53 seconds
Episode Artwork

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ወጣት

የትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ውጤቱን ይፋ ባደረጉበት ወቅት ከአጠቃላይ ተፈታኞች መካከል 3.3% ብቻ ፈተናውን ያለፉ ሲሆን ከፍተኛው ውጤት 666 መሆኑ ተገልጧል። በዛሬው የወጣቶች ዓለም ፕሮግራም የወጣቱን የቀደመ ታሪክ፣ የገጠመውን ውጣውረድና የወደፊት ራዕይ በተመለከተ ወላጆቹንና ተማሪውን ለዶይቸ ቬለ ተናግሯል።
2/3/20239 minutes, 53 seconds
Episode Artwork

«ከንፋስ የፈጠነ ከውኃ የቀጠነ ፍቅር ይዞኛል»

አሆላሎ በልጃገረዶች እና እነሱን ለማጨት በሚፈልጉ ወጣት ወንዶች መካከል ከጥንት ጀምሮ የሚካሄድ ባሕላዊ ጭፍራ ነው። ጭፈራው በተለያዩ አጋጣሚዎች የሚከናወን ሲሆን በዚህ በጥምቀት በዓል ሰሞን በወሎ ደሴ እና አካባቢዋ ይከናወናል። የአሆላሎ ጭፈራና አከባበሩ ባህሉን ጠብቆ ለትውልድ እንዲተላለፍ ምን እየተሰራ ነው?
1/20/202310 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

የዘንድሮ ወጣት ፈተናዎች

በውጭውም ይሁን ኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ በእድሜ ከፍ ያሉ ሰዎች ወይም ወላጆች የዘመኑን ወጣቶች ሲገልፁ አብዛኛውን ጊዜ ከስልካቸው እንደማይለዩ ፣ ስርዓት እንደሚጎድላቸው ወይም የተለያዩ ሱሶችን እንደሚያዘወትሩ አድርገው ነው። ይህ ምን ያህል እውነት ነው? የዘንድሮ ወጣት ፈተናዎችስ ምንድን ናቸው?
1/13/202310 minutes, 32 seconds
Episode Artwork

የዘመኑ ወጣት ፈተናዎች

በዱባይ ለጉልበት ብዝበዛ የተዳረጉ እንስት ኢትዮጵያውያን ድረሱልን ይላሉ

1/6/20239 minutes, 9 seconds
Episode Artwork

ወጣት ሰአልያንና ፈተናዎቻቸው

የኔ ሥራ በዓለም አቀፍ ደረጃም ሊታይ የሚችል ሥራ ነው ይዤ የቀረብኩት። የኔ ሥራ ባሕል ላይ ወይም አንድ ጉዳይ ላይ ብቻ የሚያተኩር ሳይሆን ማሕበረሰቡ ላይ ያሉ ችግሮችን፣ በቀን በቀን ሕይወታችን ላይ የምናያቸውን እነሱን እያጎላሁ፣ አሁን አንድ አንድ ጊዜ አንዳንዶች የበለጠ ውበት ላይ ትኩረት አድርገው የሚሰሩ አሉ።
12/30/202210 minutes
Episode Artwork

ሴቶች በዩኒቨርሲቲ እንዳይማሩ የከለከለው ታሊባንና የገጠመው ተቃውሞ

አፍጋኒስታን ውስጥ ሴቶች ዩኒቨርስቲ ገብተው እንዳይማሩ ታሊባን በዚህ ሳምንት ከከለከለ ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ተቃዉሞና ቁጣ ገጥሞታል። የአፍጋኒስታን ሴት ተማሪዎች እጃቸውን ላለመስጠት እየታገሉ እንደሆነ ነው የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ፔተር ሆርኑግ የዘገበው።
12/23/20229 minutes, 32 seconds
Episode Artwork

ሴቶች በዩንቨርስቲ እንዳይማሩ የከለከለው ታሊባን እና የገጠመው ተቃውሞ

አፍጋኒስታን ውስጥ ሴቶች ዩኒቨርስቲ ገብተው እንዳይማሩ ታሊባን በዚህ ሳምንት ከከለከለ ጊዜ አንስቶ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ ተቃዉሞና ቁጣ ገጥሞታል። የአፍጋኒስታን ሴት ተማሪዎች እጃቸውን ላለመስጠት እየታገሉ እንደሆነ ነው የዶይቸ ቬለ ባልደረባ ፔተር ሆርኑግ የዘገበው።
12/23/20229 minutes, 32 seconds
Episode Artwork

የሻራገነት በጎ ፍቃደኞች

የዛሬው የወጣቶች ዓለም ዝግጅት በሰሜን ወሎ ዞን ወደምትገኝ ትንሽዬ የገጠር ወረዳ ይወስደናል። በዚህች የጋዞ ወረዳ ቤት ከቤት እየሄዱ ከሚያሰባስቡት የርዳታ እቃ ተነስተው አሁን ላይ በማህበራዊ ሚዲያ በአካባቢያቸው ለሚገኙ የተጎዱ ወገኖች፤ የምግብ፣ የማሳከሚያ እና ሌሎችም ድጋፎች የሚለግሱ ሶስት ወጣቶችን እንግዳው አድርጓል።
12/16/202210 minutes
Episode Artwork

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የወጣቶችና የወላጆች ግንኙነት

አዳጊ ሴቶች ከወላጆቻቸው ጋር ያላቸው የግንኙነት ደረጃ በእርግጥ እንደማህበረሰቡ ልማድና እውቀት ሊለያይ ይችላል፡፡ በሀዋሣ ከተማ ነዋሪ የሆነችው ቤቴሌሄም ሞገስ የአስራ ዘጠኝ ዓመት አዳጊና የ12ኛ ክፍል ተማሪ ናት፡፡ ቤቴሌሄም በአዳጊ የእድሜ ክልል የምንገኝ ሴቶች ያልተቋረጠ የወላጆች ክትትልና ድጋፍ ያስፈልገናል ትላለች፡፡
12/9/202210 minutes, 11 seconds

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ወጣት ሴቶች በስንት ዓመታቸው የፍቅር ግንኙነት ቢጀምሩ አግባብ ነው?

የተወደዳችሁ የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዝግጅት የሬድዮ አድማጮች በዛሬው ፕሮግራም አንዲት ሴት ልጅ የወንድ ጓደኛ ልትይዝበት የሚገባው ፤ በብዙ መልኩም ትክክለኛ ሊባል የሚችለው ዕድሜ የቱ ነው ?
12/2/202210 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: ወጣት ሴቶች በስንት ዓመታቸው የፍቅር ግንኙነት ቢጀምሩ አግባብ ነው?

የተወደዳችሁ የዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዝግጅት የሬድዮ አድማጮች በዛሬው ፕሮግራም አንዲት ሴት ልጅ የወንድ ጓደኛ ልትይዝበት የሚገባው ፤ በብዙ መልኩም ትክክለኛ ሊባል የሚችለው እድሜ የቱ ነው ? ወይም የፍቅር አጋር ለመወዳጀት በእድሜ እና ስነ ልቦና ዝግጁ የሚኮንበት ጊዜ የትኛው ነው?
12/2/202210 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

በቀጠር የኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ተሞክሮ

የዓለም ዋንጫ አስተናጋጇ ቀጠር በውጭ ሀገራት ሰራተኞች ጉልበት ሰባት ስታድየሞች፣ አዲስ አውሮፕላን ማረፊያ፣ የባቡርና የአስፋልት መንገዶችን ገንብታለች። በዚህም ኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ተካፍለዋል። በግንባታው ወቅት ቀጠር የበርካታ ሰራተኞችን መብት አላከበረችም በሚል ጠንካራ ትችት ተሰንዝሮባታል። በግንባታዉ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያን ምን ይላሉ?
11/25/202210 minutes, 28 seconds

ዲዛይነት ምህረት ታሪኩ

በቤተሰቧ ሳሎን ውስጥ በአንድ የልብስ ስፌት ማሽን የስፌት ሥራ እንደጀመረች ታሪኳን ያጫወተችን ምህረት ታሪኩ ትባላለች። ምህረት የሰፋችውን አንድ ከረባትም ዩናይትድ ስቴትስ ለሚገኙ የአንድ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ልካም ነበር። ለምን?
11/18/202210 minutes
Episode Artwork

"ሳሎን ውስጥ ነው ልብስ መስፋት የጀመርኩት”

በቤተሰቧ ሳሎን ውስጥ በአንድ የልብስ ስፌት ማሽን የስፌት ሥራ እንደጀመረች ታሪኳን ያጫወተችን ምህረት ታሪኩ ትባላለች። ምህረት የሰፋችውን አንድ ከረባትም ዩናይትድ ስቴትስ ለሚገኙ የአንድ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ልካም ነበር። ለምን?
11/18/202210 minutes
Episode Artwork

የወጣቶች ዓለም

11/4/202210 minutes, 32 seconds
Episode Artwork

የጀማል እና ሀሰን ክስ ከምን ደረሰ?

ሳውዲ ዓረቢያ ውስጥ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተከሰው የሞት ፍርድ ስለሚያሰጋቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን ባለፈው ግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ መዘገባችን ይታወሳል። በወቅቱ የተከሳሽ ቤተሰቦች በአንድ ወር ውስጥ ይግባኝ ካልተባለ የሞት ፍርዱ ተግባራዊ ይሆናል የሚል ስጋታቸውን ገልፀውልን ነበር። ከዛን ጊዜ በኋላ የጀማል እና ሀሰን ክስ ከምን ደረሰ?
10/28/20229 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

ሳውዲ ዓረቢያ: የጀማል እና ሀሰን ክስ ከምን ደረሰ?

ሳውዲ ዓረቢያ ውስጥ በነፍስ ማጥፋት ወንጀል ተከሰው የሞት ፍርድ ስለሚያሰጋቸው ሁለት ኢትዮጵያውያን ባለፈው ግንቦት ወር መጀመሪያ ላይ መዘገባችን ይታወሳል። በወቅቱ የተከሳሽ ቤተሰቦች በአንድ ወር ውስጥ ይግባኝ ካልተባለ የሞት ፍርዱ ተግባራዊ ይሆናል የሚል ስጋታቸውን ገልፀውልን ነበር። ከዛን ጊዜ በኋላ የጀማል እና ሀሰን ክስ ከምን ደረሰ?
10/28/20229 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

የኤሚ አዋርድስ አሸናፊዎቹ ሀድራ እና ንጉሱ

የዛሬው የወጣቶች ዓለም ፣ ለፊልም ባለሙያዎች የሚሰጠውን ፣በአጭሩ «ኤሜ » በመባል የሚታወቀውን ሽልማት ያገኙ ሁለት ወጣት ኢትዮጵያውያንን እንግዳው አድርጓል። የፊልም ፕሮዲውሰር እና ጋዜጠኛ ሀድራ አህመድ እና የካሜራ ባለሙያ ንጉሱ ሰለሞን ፣የኤሚ 2021 ተሸላሚ ናቸው።
10/21/202210 minutes
Episode Artwork

የቅኔ ተማሪዎች ተበትነዋልን?

ቅሬታ አቅራቢዎች የወረታ ደብረ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤል ግቢ ውስጥ የነበረ የቅኔ ጉባኤ ቤት በመፍረሱ በርካታ የቅኔ ተማሪዎች ተባረዋል ሲሉ ይወቅሳሉ። ወቀሳ የቀረበበት ወገን ደግሞ ፈረሰ ሳይሆን የሚባለው የተሻሻለ ቦታ ላይ መማሪያ ቦታ ሰጥተናቸዋል ፣ይሁንና የተማሪው ቁጥር እንዲቀንስ አድርገናል ይላል።
10/14/202210 minutes, 44 seconds

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች: የሱስ ተጋላጭ የነበረችው ወጣት

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆነችው የአሥራ ስምንት ዓመቷ ሐና ታደለ ላለፉት ሦስት ዓመታት በጎዳና ላይ መኖሯን ትናገራለች ፡፡ ሐና በጎዳና ሕይወት ውስጥ ያለ ሰው ለፆታዊ ጥቃት የመጋለጥና በሱስ የመያዝ እድሉ ሠፊ ነው ትላለች ፡፡
10/7/20229 minutes
Episode Artwork

የሱስ ተጋላጭ የነበረችው ሃና

የሀዋሳ ከተማ ነዋሪ የሆነችው የአሥራ ስምንት ዓመቷ ሐና ታደለ ላለፉት ሦስት ዓመታት በጎዳና ላይ መኖሯን ትናገራለች ፡፡ ሐና በጎዳና ሕይወት ውስጥ ያለ ሰው ለፆታዊ ጥቃት የመጋለጥና በሱስ የመያዝ እድሉ ሠፊ ነው ትላለች ፡፡
10/7/20229 minutes
Episode Artwork

የኢራናውያኗ ወጣት ሞት የቀሰቀሰው ተቃውሞ

ሰሞኑን በፋርስ ቋንቋ በቀዳሚነት የተሰራጨ የትዊተር መልዕክት ቢኖር #MahsaAmini ነው። ፀጉሯን በአግባቡ አልሸፈንሽም በሚል በ«ሥነ ምግባር ፖሊስ» ቁጥጥር ስር ውላ የነበረቸው የ22 ዓመት ወጣት ራሷን ስታ ሆስፒታል ከገባች በኋላ መስከረም 6 ቀን 2015 ዓ.ም ህይወቷ አልፏል። የወጣቷ ሞት ከፍተኛ ተቃውሞ እና ቁጣ አስነስቶ ሰንብቷል።
9/30/202210 minutes, 1 second
Episode Artwork

አነጋጋሪ የሆነው አዲሱ የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት

ኢትዮጵያ ውስጥ መስከረም 9 ቀን 2015 ዓ. ም. አዲስ የትምህርት ዘመን መጀመር ብቻ ሳይሆን፤ በመላው ሀገሪቱ አዲስ ሥርዓተ ትምህርትም ተግባራዊ ሆኗል። በወጣቶች ዓለም ክፍለ ጊዜ ያነጋገርናቸው በተለይም መምህራን እና ወላጆች አዲስ ሥርዓተ ትምህርት መዘጋጀቱን ቢደግፉም አያይዘው የሚያነሷቸው በርካታ ትችቶችም አሉ።
9/23/202210 minutes, 11 seconds
Episode Artwork

«ስሟ ጊታር ነው» ድምፃዊ ዮሃንስ ጌታቸው

ድምፃዊ ዮሃንስ ጌታቸውን በተለይ በቅርቡ ያወጣው «ስምሽ ማነው» የተሰኘው ዜማ ከህዝብ ጋር አስተዋውቆታል። ወጣቱ የሂሳብ አያያዝ ምሩቅ ሲሆን በዚህ ሙያ ከመስራት ይልቅ ሙዚቃ መጫወትን መርጧል።
9/16/202210 minutes
Episode Artwork

«ስሟ ጊታር ነው» ድምፃዊ ዮሃንስ ጌታቸው

ድምፃዊ ዮሃንስ ጌታቸውን በተለይ በቅርቡ ያወጣው «ስምሽ ማነው» የተሰኘው ዜማ ከህዝብ ጋር አስተዋውቆታል። ወጣቱ የሂሳብ አያያዝ ምሩቅ ሲሆን በዚህ ሙያ ከመስራት ይልቅ ሙዚቃ መጫወትን መርጧል።
9/16/202210 minutes
Episode Artwork

የአዲስ ዓመት እቅዶች እና ማሳኪያ መንገዶች

ኢትዮጵያ ውስጥ አዲስ ዓመት በድምቀት የሚከበር በዓል ብቻ ሳይሆን ሰዎች በመጪው ዓመት ለማሳካት የሚፈልጉትን ነገሮች እቅድ የሚያወጡበትም ነው። ነገር ግን ምን ያህላችን ያቀድነውን እናሳካለን? እቅዶች ሳይሳኩ የሚቀሩትስ ለምንድን ነው?
9/9/202210 minutes

ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች፤ ሴት የስኬት ቦርድ ነጂዎች

በአዲስ አበባ መካኒሳ አካባቢ በቡድን ተሰባስበው ስኬት ቦርድን የሚለማመዱ ሴት ታዳጊዎች ለዶይቼ ቬለ ዝምታ ሰባሪ አዳጊ ሴቶች ዘጋቢ ሱመያ ሳሙኤል እንደገለፁላት ስፖርቱ ደፋር አድርጓቸዋል፣ በራስ መተማመናቸውም ጨምሯል።
9/2/20229 minutes, 41 seconds
Episode Artwork

የኢትዮጵያውያን ወጣቶች ወቅታዊ ስጋት

ጀርመን ውስጥ በቅርብ ጊዜ የተካሄደ የዳሰሳ ጥናት እንደሚያሳየው የአየር ንብረት ለውጥ፣ የዩክሬን ጦርነት እና የጀርመን የወደፊት እጣ ፈንታ ጀርመን ያሉ ወጣቶችን የሚያስጨንቋቸው ጉዳዮች ናቸው። ኢትዮጵያውያን ወጣቶችንስ? የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ፣ ሥራ አጥነት እና የኑሮ ውድነት በርካታ ኢትዮጵያውያን ወጣቶች የሚያስጨንቁ ጉዳዮች ናቸው።
8/26/202210 minutes, 15 seconds