Winamp Logo
መዝናኛ | Deutsche Welle Cover
መዝናኛ | Deutsche Welle Profile

መዝናኛ | Deutsche Welle

Amhaars, Music, 1 seizoen, 50 afleveringen, 9 uur, 5 minuten
Over
አዝናኚ ዝግጅት ነው።
Episode Artwork

መዝናኛ፦ የካፋ ቱባ ባህላዊ ሙዚቃዎች ወዴት ናቸው?

5-6-202210 minuten, 26 seconden
Episode Artwork

የካፋ ባህላዊ ሙዚቃዎች ተጠበቅዋልን?

ካፋዎች አራት አይነት ባህላዊ የሙዚቃ ስልቶች አሏቸው ። በደስታ እና በበዓላት ቀናት የሚዜሙ፣ በጋራ ስራ ወይም ደቦ ወቅት የሚዜሙ ፣ በለቅሶ ወይም የሀዘን ወቅት የሚዜሙ ፣ እንዲሁም በአካባቢው ከተፈጥሯዊ ስረዓት ውጪ አዲስ ክስተት ሲፈጠር ሴቶች ከመንደር መንደር እየተቀባበሉ የሚያዜሟቸው ናቸው ።
5-6-202210 minuten, 26 seconden
Episode Artwork

የጉማ ሽልማት

ኢትዮ ፊልም የሚዘጋጀው ጉማ አዋርድ ባለፈው አመት ተሰርተው በተለያዩ የኢትዮጵያ ሲኒማ ቤቶች ለህዝብ እይታ የበቁ ፊልሞችን የሚያወዳድር ነው። በዘንድሮው የሽልማት መርሐ ግብር ቤተልሔም አካለወርቅ በእጇ እና በጀርባዋ ጽፋ የታየችው የሴት ልጅ ጥቃት ይቁም የሚል መልዕክት የብዙሃንን ቀልብ የሳበ ነበር።
22-5-202210 minuten, 28 seconden
Episode Artwork

መዝናኛ፦ የጉማ ሽልማት

22-5-202210 minuten, 28 seconden
Episode Artwork

የስእልና ቅርጻቅርጽ ባለሞያ ምሕረት ዳዊት

ከ1983 ጀምሮ የተለያዩ ስእሎችን በመሳል በቡድንና በተናጥል ወደ 40 የሚጠጉ የሥእል ትርኢቶችን ማቅረቧን የገለጸችልን ምሕረት ከተመልካቾችም የእደጊ ተመንደጊ አድናቆት ማግኘቷንና ይህም ለስራዋ ብርታት እንደሰጣት አጫውታናለች።
15-5-20229 minuten, 50 seconden
Episode Artwork

የስእልና ቅርጻቅርጽ ባለሞያ ምሕረት ዳዊት

ከ1983 ጀምሮ የተለያዩ ስእሎችን በመሳል በቡድንና በተናጥል ወደ 40 የሚጠጉ የሥእል ትርኢቶችን ማቅረቧን የገለጸችልን ምሕረት ከተመልካቾችም የእደጊ ተመንደጊ አድናቆት ማግኘቷንና ይህም ለስራዋ ብርታት እንደሰጣት አጫውታናለች።
15-5-20229 minuten, 50 seconden
Episode Artwork

ታዋቂዉ የጥበብ ሰው ሃብታሙ ማሞ

1-5-20229 minuten, 3 seconden
Episode Artwork

ታዋቂዉ የጥበብ ሰው ሃብታሙ ማሞ

ሜድ ኢን ቻይና፣ ታሰጨርሺኛለሽ፣ እሾሃማ ፍቅር፣ ላገባ ነው የሚሉ ፊልሞቸ በአብዛኛው የጥበብ ታዳሚ የሚታወቁ ናቸው። በእነዚህና ሌሎች ሰራዎቸ በደራሲነት ዳይሬክተርነተና በፊልም ሰሪነት እንዲሁም በመጽሐፍና ግጥም ደራሲነት እያገለገለ ነው አርቲስት ሃብታሙ ማሞ
1-5-20229 minuten, 3 seconden
Episode Artwork

ሁለገቡ የስነ ጥበብ ሰው ምንይችል እንግዳ የህይወት ተሞክሮ

17-4-202211 minuten, 10 seconden
Episode Artwork

ድምጻዊ ፣ ጸሐፊና ጋዜጠኛው ምንይችል እንግዳ

ምንይችል እንግዳ ይባላል፣ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በቲያትሪካል አርትስ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ከጎንደር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በሶሻል ሳይንስ 2ኛ ዲግሪውን ይዟል፡፡ አሁን በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋዜጠኛ ነው፡፡ ምንይችል ዘፋኝና ፀሐፊም ነው፣ በአገውኛ ቋንቋ የዘፈን ግጥሞችን ለዘፋኞች ይሰጣል፣ እሱም ይዘፍናል፡፡
17-4-202211 minuten, 10 seconden
Episode Artwork

እንደገና የሚቀናበሩ ሙዚቃዎች በኢንደስትሪው ውስጥ ያላቸው አንድምታ

ሙዚቃ በኢትዮጵያ በትውልድ ቅብብሎሽ ሂደት እያለፈ ዛሬን ደርሷል። በየትውልዱ ዘመን ተሻጋሪ የሙዚቃ ስራዎች ተሰርተው ለአድማጭ ተመልካቹ ደርሰዋል። የዚያኑ ያህል ከግለሰቦች ድካም ሳይዘል በአንድ ወቅት ተደምጠው በሆነ አጋጣሚ ካልሆነ በቀር ከአድማጭ ተመልካቹ ጆሮና አይን ርቀው የቀሩ የሙዚቃ ስራዎች  ተጠቃሾች ናቸው ።
10-4-202211 minuten, 43 seconden
Episode Artwork

እንደገና የሚቀናበሩ ሙዚቃዎች በኢንደስትሪው ውስጥ ያላቸው አንድምታ

አሁን አሁን በኢትዮጵያ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ እንደገና በሚሰሩ ወይም በእንግሊዘኛው ሪሚክስ በሚደረጉ እንዲሁም በከቨር የተሰሩ አዳዲስ የነጠላ ዜማዎች በስፋት እየተለቀቁ ይገኛሉ። የማህበራዊ መገናኛ ዘዴዎች በተለያዩ አማራጮች መምጣታቸው ደግሞ የሙዚቃ ስራዎች በቀላሉ አድማጭ ተመልካች ጋር እንዲደርሱ ከማስቻሉም ባለፈ የገቢ ምንጭ እየሆነ ነው።
3-4-202210 minuten, 34 seconden
Episode Artwork

ማጀቴ፤ የኒና ግርማ አዲሱ የሙዚቃ አልበም

27-3-202211 minuten, 37 seconden
Episode Artwork

አምስተኛው የኦዳ አዋርድ የዕድሜ ልክ ተሸላሚዎችን አካቶ ተከናውኗል

13-3-202210 minuten, 23 seconden
Episode Artwork

አምስተኛው የኦዳ አዋርድ እነማንን ሸለመ?

በዘንድሮው የኦዳ ሽልማት ስነ ስረዓት በሙዚቃ ፣ ፊልም እና የስነ ጽሁፍ ዘውጎች ከ60 በላይ አርቲስቶች በዕጩነት መቅረባቸው በአዘጋጆቹ ተገልጿል። በ20 የተለያዩ ዘርፎች ሽልማቱ የተዘጋጀ ሲሆን ለሙዚቃ ስምንት የሽልማት ዘርፎች ፣ ለፊልም ሰባት የሽልማት ዘርፎች እንዲሁም ለስነ ጽሁፍ ሁለት የሽልማት ዘርፎች አሸናፊዎች ተለይተዋል።
13-3-202210 minuten, 23 seconden
Episode Artwork

መዝናኛ፦ ተሸላሚዎቹ ጋዜጠኞች

20-2-202220 minuten, 30 seconden
Episode Artwork

ድምጻዊ እና የመብት ተሟጋቹ ኑሆ ጎበና ሲዘከር

ለዛ ባላቸው እና ወኔ ቀስቃሽ ሙዚቃዎቹ ተወዳጅነትን ያተረፈው ገና በለጋ የወጣትነት ዕድሜው ነበር ። ለዚያውም አማራጭ የመገናኛ ብዙኃን ባልነበረበት እና የሙዚቃ ኢንዱስትሪው ገና ባልተስፋፋበት የንጉሱ ዘመን። ለኦሮሞ ህዝብ መብት መከበር «ከንጉሱ ዘመን ጀምሮ የሙዚቃ ተሰጥዖውን ተጠቅሞ መታገሉን » የሙያ አጋሮቹ ይመሰክሩለታል።
23-1-202210 minuten, 58 seconden
Episode Artwork

ከደራሲ ምህረት አዳል ጊቢ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

26-12-20219 minuten, 36 seconden
Episode Artwork

ከደራሲ ምህረት አዳልጊቢ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

ትውልድ እና እድገቷ አዲስ አበባ የሆነችው ወጣት ደራሲ ምህረት አዳልጊቢ ከህጻንነቷ ጊዜ ጀምሮ የመጻፍ ልምድ አካብታለች። አሁን ላለችበት የደራሲነት ሙያ የእናትዋ አሻራ ትልቅ እንደሆነ ጭምር ትናገራለች። በእንግሊዘኛ ቋንቋ አራት መጻሕፍት ለኅትመት ያበቃችው ምህረት አዳልጊቢ የዛሬው የመዝናኛ መሰናዶ እንግዳ ነች።
26-12-20219 minuten, 36 seconden
Episode Artwork

የድሬዳዋው ሲሳይ ዘለገሀሬ የግጥም ስራዎች

"ለፍቅራችሁ" ገጣሚ ሲሳይ ከስምንት አመት በፊት ያሳተመው የግጥም መፅሀፍ ርዕስ ነበር። የዚያን ጊዜው መፅሀፍ  ከብዙዎች አስተዋውቆኛል የሚለው ሲሳይ ከዚያ በኃላ ግን መፅሀፍ ማሳተም ሀሳቡ ቢኖረውም በተለያየ ምክንያት ማሳተም አለመቻሉን አጫውቶናል።
19-12-20218 minuten, 9 seconden
Episode Artwork

ዘርፈ ብዙ የጥበብ ባለሙያ ዋሲሁን አራጌ

በጋዜጠኝንት፣ የሙዚቃ ግጥም ደራሲነት በተንቀሳቃሽ ምስል የታግዙ የሙዚቃ አልበሞችን ዳይረክተርነትና አምራችነት እንዲሁም በግጥም፣ አጭር ወጎችና ረዥም ልቦለድ ድርሰት ይታወቃል። ዋሲሁን አራጌ።
12-12-202110 minuten, 8 seconden
Episode Artwork

የድምጻዊ ወንድዬ አበበ የሙዚቃ ሕይወት እና ስራዎች

ትውልድ እና እድገቱ በቀድሞው የደቡብ ክልል ኮንታ ልዩ ወረዳ ፤ በአሁኑ የደቡብ ምዕራብ ህዝቦች ክልል ኮንታ ዞን እንደሆነ ይናገራል። የሙዚቃ ስራን ገና በለጋ እድሜው በተቀላቀለበት የወታደር ቤት መጀመሩን ይናገራል፤ ድምጻዊ ወንድዬ አበበ ወይም በቅጽል ስሙ ወንድዬ ኮንታ ። የዛሬው የመዝናኛ ዝግጅት እንግዳችን ነው።
28-11-202111 minuten, 12 seconden
Episode Artwork

የአርቲስት መርጊቱ ወርቅነህ የሙዚቃ ህይወት እና ስራዎቿ

14-11-202111 minuten, 43 seconden
Episode Artwork

ሰርከስ ደብረብርሃን በጀርመን ብሩል ከተማ

ከተመሠረተ ከ20 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የሰርከስ ደብረብርሃን ቡድን በአሁን ሰዓት አውሮፓ ውስጥ እየተዟዟረ ትርዒት በማቅረብ ላይ ይገኛል። በኮሮና ምክንያት ሰባት የቡድኑ አባላትን ብቻ ይዞ የተጓዘው ሰርከስ ደብረብርሃን ሰሞኑን በዚህ በጀርመን የተለያዩ ከተሞች ተዟዙሮ ብቃቱን ያሳየበት ብቻ ሳይሆን የባህል ልውውጥም ያደረገበት ነበር።
7-11-202110 minuten, 30 seconden
Episode Artwork

ሰርከስ ደብረብርሃን በጀርመን ብሩል ከተማ

ከተመሠረተ ከ20 ዓመታት በላይ ያስቆጠረው የሰርከስ ደብረብርሃን ቡድን በአሁን ሰዓት አውሮፓ ውስጥ እየተዟዟረ ትርዒት በማቅረብ ላይ ይገኛል። በኮሮና ምክንያት ሰባት የቡድኑ አባላትን ብቻ ይዞ የተጓዘው ሰርከስ ደብረብርሃን ሰሞኑን በዚህ በጀርመን የተለያዩ ከተሞች ተዟዙሮ ብቃቱን ያሳየበት ብቻ ሳይሆን የባህል ልውውጥም ያደረገበት ነበር።
7-11-202110 minuten, 30 seconden
Episode Artwork

ማኅበራዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ተነስተውበታል

17-10-202111 minuten, 51 seconden
Episode Artwork

«ከሁሉ ነገር ሀገሬ ትቀድምብኛለች»ድምፃዊት ራሄል ጌቱ

10-10-202111 minuten, 13 seconden
Episode Artwork

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ቴያትር መቶ ዓመት በሰሜን አሜሪካ ተከበረ

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ቴያትር መቶ ዓመት ሞላው::የሃገር ቤቱን ክብረ በዓል ተከትሎ ካናዳን ጨምሮ በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የቴያትር ባለሙያዎች የኢትዮጵያ ዘመናዊ ቴያትር የተጀመረበትን መቶኛ ዓመት በዋሽንግተን ዲሲ አክብረዋል:: ይኸው ልዩ ክብረ በኃል የተካሄደው ሲልቨርስፕሪንግ ሜሪላንድ በሚገኘው ሞንቶጎመሪ ኮሌጅ የቴያትር ማዕከል ውስጥ ነበር::
3-10-20219 minuten, 6 seconden
Episode Artwork

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ቴያትር መቶ ዓመት በሰሜን አሜሪካ ተከበረ

3-10-20219 minuten, 6 seconden
Episode Artwork

ኢትዮጵያዊው ኤልቪስ ፕሪስሊ፤ አለማየሁ እሸቴ  ሲታወስ

ኢትዮጵያዊው ኤልቪስ ፕሪስሊ፤ አለማየሁ እሸቴ  ሲታወስ
5-9-202110 minuten, 22 seconden
Episode Artwork

መዝናኛ፦ የኢትዮጵያውያን የኪነ-ጥበብ ማኅበር በሰሜን አሜሪካ

8-8-20219 minuten, 59 seconden
Episode Artwork

ከጋዜጠኛ ሰለሞን ታምሩ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

ሰለሞን ታምሩ በአካል ጉዳተኞች ላይ ያተኮሩ መሰናዶዎች የሚሰራ ጋዜጠኛ ነው። አዲስ አበባ ተወልዶ ያደገው ሰለሞን እስከ ዘጠነኛ ክፍል ድረስ ማየት ይችል ነበር። የአይን ብርሀኑን ካጣ በኋላ በቤት ውስጥ ለመቀመጥ ሲገደድ ራዲዮ ማዳመጥ ያዘወትር የነበረው ሰለሞን በአካል ጉዳት ላይ በቂ ትኩረት ባለመሰጠቱ በእልህ ጋዜጠኝነትን እንደጀመረ ተናግሯል
1-8-202110 minuten, 31 seconden
Episode Artwork

ከጋዜጠኛ ሰለሞን ታምሩ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ

1-8-202110 minuten, 31 seconden
Episode Artwork

የአንጋፋዋ ጋዜጠኛ ኢሌኒ መኩርያ ሕይወት እና ስራዎቻቸው

25-7-202111 minuten, 33 seconden
Episode Artwork

የባጃጅ ሾፌሯ ወ/ሮ የሕይወት ተሞክሮ ምን ይናገራል?

ወ/ሮ መድኃኒት ተሾመ በአዲስ አበባ ከተማ የባለሶስት እግር ታክሲ ሾፌር ናቸው። ከኮሌጅ መመረቃቸውን የሚናገሩት ወ/ሮ መድኃኒት ስራ ከመጠበቅ ስራ ፈጥሮ ህይወትን ማሸነፍ ይቻላል ባይ ናቸው።  ከታክሲዋ በሚያገኙት ገቢ ቤተሰባቸውን ያስተዳድራሉ።
18-7-20219 minuten, 56 seconden
Episode Artwork

የባለሶስት እግር ታክሲ ሾፌር ወ/ሮ የሕይወት ልምድ

ወ/ሮ መድኃኒት ተሾመ በአዲስ አበባ ከተማ የባለሶስት እግር ታክሲ ሾፌር ናቸው። ከኮሌጅ መመረቃቸውን የሚናገሩት ወ/ሮ መድኃኒት ስራ ከመጠበቅ ስራ ፈጥሮ ህይወትን ማሸነፍ ይቻላል ባይ ናቸው።  ከታክሲዋ በሚያገኙት ገቢ ቤተሰባቸውን ያስተዳድራሉ።
18-7-20219 minuten, 56 seconden
Episode Artwork

የአርቲስት ሓጫሉ ሁንዴሳ ሶስተኛ አልበምና ሙት ዓመት

4-7-202111 minuten, 50 seconden
Episode Artwork

የአርቲስት ሓጫሉ ሁንዴሳ በሙት ዓመቱ ሶስተኛ አልበሙ

እውቁ የኦሮምኛ ሙዚቃ አቀንቃኝ አርቲስት ሓጫሉ ሁንዴሳ ከተገደለ ድፍን አንድ ዓመት አለፈው።  አርቲስቱ እየሰራበት የነበረው ሶስተኛ አልበሙ ተጠናቆ ባለፈው ሰኞ ሰኔ 21 ቀን 2013 ዓ.ም. ከሙት ዓመቱ አንድ ቀን ቀድሞ ተለቋል፡
4-7-202111 minuten, 50 seconden
Episode Artwork

ዲጄዎች በኢትዮጵያ

13-6-202110 minuten, 17 seconden
Episode Artwork

ድምፃዊት ዘቢባ ግርማና የሙዚቃ ስራዎቿ

ድምፃዊት ዘቢባ ግርማ በ2011 ዓ/ም «ገራገር»፣ በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ደግሞ «ያማል ቅኔው» የተሰኙ ሁለት ተወዳጅ ነጠላ ዜማዎቿን ለአድማጭ ጀሮ አድርሳ አድናቆት ተችሯታል። በቅርቡ በተካሄደው 11ኛው አዲስ ሚዩዚክ የኪነ ጥበብ ሽልማትም ገራገር በተሰኘው ዜማዋ በምርጥ ነጠላ ዜማ የ2013 ዓ/ም ተሸላሚ ሆናለች። 
6-6-202110 minuten, 32 seconden
Episode Artwork

ድምፃዊት ዘቢባ ግርማና የሙዚቃ ስራዎቿ

ድምፃዊት ዘቢባ ግርማ በ2011 ዓ/ም «ገራገር»፣ በ2012 ዓ/ም መጨረሻ ደግሞ «ያማል ቅኔው» የተሰኙ ሁለት ተወዳጅ ነጠላ ዜማዎቿን ለአድማጭ ጀሮ አድርሳ አድናቆት ተችሯታል። በቅርቡ በተካሄደው 11ኛው አዲስ ሚዩዚክ የኪነ ጥበብ ሽልማትም ገራገር በተሰኘው ዜማዋ በምርጥ ነጠላ ዜማ የ2013 ዓ/ም ተሸላሚ ሆናለች። 
6-6-202110 minuten, 32 seconden
Episode Artwork

«የወጎቼ ዓላማ ሁሉም ራሱን እንዲመለከት ነው»

የእፀገነት ሽሙጥ ቀመስ የመድረክ ወጎች
30-5-202115 minuten, 48 seconden
Episode Artwork

የእፀገነት ሽሙጥ ቀመስ የመድረክ ወጎች

መምህርትና የጥበብ ሰው እፀገነት ከበደ በተለያዩ መድረኮች በምታቀርባቸው ሽሙጥ ቀመስ ወጎቿ ትታወቃለች። በሰራዎቿ ከታዳሚው ዘንድ የምታገኘው አድናቆት ከፍተኛ ቢሆንም የሚተቿት እንዳሉም ትናገራለች። እንደ እፀገነት የፅሁፎቿ ዓላማ ሁሉም ወደራሱ እንዲመለከት ቢሆንም፤ የራሱን ትርጉም ሰጥቶ መልዕክቱን ለአንድ ለተወሰነ አካል የሚገፋ ታዳሚ ብዙ ነው።
30-5-202115 minuten, 48 seconden
Episode Artwork

መዝናኛ፦ የሸዋል ኢድ በዓል በሀረር

23-5-202110 minuten, 23 seconden
Episode Artwork

የሸዋል ኢድ በዓል በሀረር

በመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በታላቅ ድምቀት የሚከበረውን የኢድ አልፈጥር በዓል አንድ ሳምንት አልፎ በሀረሪ ብሄረሰብ ዘንድ የሚከበረው የሸዋል ኢድ በዓል ለሀረር በተለይም በዓሉ ምሽት ለሚከበረበት የጀጎል አካባቢ ድምቀት ነው፡፡ በዓሉ በተለይ ወጣቶች ውሀ አጣጭ የሚመረርጡበት፣ የተፈላለጉ የሚተጫጩበት መሆኑ ትዕይንቱን ያማረ ያደርገዋል
23-5-202110 minuten, 23 seconden
Episode Artwork

´´የከተማው መናኝ´´ ኤልያስ መልካ ሕይወት

ሰሞኑን በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለየው አንጋፋው የሙዚቃ ደራሲ እና አቀናባሪ ኤልያስ መልካ ህይወት ላይ ያተኮረ መጽሐፍ ታትሞ ለንባብ በቅቷል። በመጽሐፉ የሙዛቃ አቀናባሪ እና ደራሲ ኤልያስ መልካ በሙዚቃ ህይወቱ ያለፈባቸውን ውጣ ውረዶች መተረካቸውን የመጽሐፉ ደራሲ ይነገር ጌታቸው ገልጿል።
17-5-202110 minuten, 13 seconden
Episode Artwork

"ፍትሕ"  ወይም "A Fire within" ዘጋቢ ፊልም

9-5-20216 minuten, 51 seconden
Episode Artwork

«የደቡብ የሙዚቃ እና የስነጽሁፍ ሰው» ወንድሙ ከበደ

የደቡብ ክልል ካፈራቸው እና ስማቸው ጎልቶ ከሚነሳ የሙዚቃ እና ስነጽሁፍ ሰዎች አንዱ ነው ። ከሙዚቃ እና የስነጽሁፍ ስራዎቹ በተጨማሪ ጥሩ የባህል አምባሳደር ነው ይሉታል። «ዳውሮ ባና » የሚታወቅበት ነጠላ ዜማው ነው። ከተወለደበት ማሕበረሰብ አልፎ ስም እና ዝናን አትርፏል።
2-5-202112 minuten, 24 seconden
Episode Artwork

መዝናኛ፦ ወንድሙ ከበደ «ዳውሮ ባና» እና የሙዚቃ ስራዎቹ

2-5-202112 minuten, 24 seconden
Episode Artwork

የአርቲስት ቤዛ ታደሰ የሙዚቃ ሕይወት እና ስራዎች

ቤዛ ታደሰ ተወልዳ ያደገችው በአዲስ አበባ ከተማ ሳር ቤት አካባቢ ነው ።ሙዚቃን አንድ ብላ የጀመረችው ደግሞ በከተማዋ ከፍተኛ 3 ተብሎ ይታወቅ በነበረ የኪነት ቡድን ውስጥ ነበር። በብሔራዊ ቴያትር እና ራስ ቴያትር ቤቶች ባሉ ዘመናዊ የሙዚቃ ባንዶች ውስጥ በድምጻዊነት አገልግላለች። በርካታ የሙዚቃ ባንዶችንም በቡድን ኃላፊነት መርታለች ።
25-4-202112 minuten, 17 seconden