20-10-2024 • 38 minuten, 16 seconden የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአማራ ክልል ይካሄዳል ያሉት «የዘፈቀደ የጅምላ እሥር»
ኢሰመኮና አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያሉት «የዘፈቀደና የጅምላ» ያሏቸው እስሮች እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ክልል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊዎች በክልሉ ጽንፈኛ ባሏቸው ኃይላ ት ላይ የተወሰደው «ሕግ የማስከበር ተግባር ነው» ሲሉ እርምጃው እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
13-10-2024 • 40 minuten, 53 seconden የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአማራ ክልል ይካሄዳል ያሉት «የዘፈቀደ የጅምላ እሥር»
13-10-2024 • 40 minuten, 53 seconden እንወያይ፤ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ዛሬ በኢትዮጵያ እንዴት ይገመገማል?
ኢትዮጵያ ውስጥ ከስድስት ዓመታት በፊት የመናገር ነጻነት ከፍተኛ መሻሻል የታየበት ዓመት ለመሆን በቅቶ ነበር። ይሁንና ሀገራዊ ፖለቲካዊና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ መረጃ የሚያቀርቡ ጋዜጠኞ፤ ት ንታኔ የሚሰጡ የፖለቲካ ተንታኞች፤ ብሎም የኪነጥበብ ባለሞያዎች ጫና ላይ እየደረሰ መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በየጊዜዉ መግለጫ ያወጣሉ።
6-10-2024 • 40 minuten, 55 seconden ለመንግስት ሰራተኞች የታሰበው የደሞዝ ጭማሪ ምን ያህል ይደጉማል ?
29-9-2024 • 41 minuten, 42 seconden የደሞዝ ጭማሪው «ሳይመጣ የሄደ ተስፋ» ወይስ ደጓሚ ?
ገና ለገና የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግ ነው በሚል በተለይ በመሰረታዊ የፍጆታ ቁሳቁሶች ላይ ተከታታይነት ያለው ጭማሪ እየታየ መሆኑን ሸማቾች ይናገራሉ ። ይህ ደግሞ የሰራተኛውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋ ም ይደግፋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የደሞዝ ጭማሪ ተስፋ እንዳያመነምን ያሰጋል ።
29-9-2024 • 41 minuten, 42 seconden ውይይት፤እያሽቆለቆለ ለመጣው የተማሪዎች ውጤት እና የትምህርት ጥራት መፍትሄ ይኖረው ይሆን?
22-9-2024 • 35 minuten, 51 seconden ውይይት፤እያሽቆለቆለ ለመጣው የተማሪዎች ውጤት እና የትምህርት ጥራት መፍትሄ ይኖረው ይሆን?
በኢትዮጵያ ባለፉት ተከታታይ ሶስት ዓመታት በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ብዙዎችን እያሳሰበ ነው። በስርዓተ ትምህርቱ ፣በትምህርት ጥራት እና አሰጣጥ ላይም ጥያቄ እንዲነሳ እያደረገ ነው። ታዲያ የችግሩ መንስኤ ምንድነው? ተማሪዎች መምህራን ወይስ ስርዓተ ትምህርቱ?መፍትሄውስ?
22-9-2024 • 35 minuten, 51 seconden ዉይይት፣ የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያና የግብፅ መዛዛት እንደቀጠለ ነዉ።ከእንግዲሕስ?
15-9-2024 • 41 minuten, 23 seconden የኢትዮጵያን ሴቶች እና ሕጻናት ከአሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃት ማን ይታደጋቸዋል?
በኢትዮጵያ ወሲባዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሕጻናት እና ሴቶች ፍትኅ እንዲያገኙ ሲደረግ የነበረው ውትወታ ምን አሳካ? የሀገሪቱ ተቋማት ተገደው ለተደፈሩ፣ ሕይወታቸውን ለተነጠቁ እና አሰቃቂ ወሲ ባዊ ጥቃቶች ለተፈጸመባቸው ፍትኅ ለማረጋገጥ ለምን ተሳናቸው? ጾታዊ ጥቃትን ለማስቆም ወንዶች፣ ቤተሰብ፣ ማኅበራዊ ተቋማት? በውይይቱ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋርያ፣ በጾታ ዕኩልነት ላይ በአማካሪነት የሚሠሩት ወይዘሮ አሻም አሳዝነው፤ የጾታ ዕኩልነት አዶቮኬት የሆኑት ርብቃ ዳዊት እና ረዳት ፕሮፌሰር ሱራፌል ወንድሙ ተሳትፈዋል።
8-9-2024 • 42 minuten, 13 seconden የኢትዮጵያን ሴቶች እና ሕጻናት ከአሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃት ማን ይታደጋቸዋል?
በኢትዮጵያ ወሲባዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሕጻናት እና ሴቶች ፍትኅ እንዲያገኙ ሲደረግ የነበረው ውትወታ ምን አሳካ? የሀገሪቱ ተቋማት ተገደው ለተደፈሩ፣ ሕይወታቸውን ለተነጠቁ እና አሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃቶች ለተፈጸመባቸው ፍትኅ ለማረጋገጥ ለምን ተሳናቸው? ጾታዊ ጥቃትን ለማስቆም ወንዶች፣ ቤተሰብ፣ ማኅበራዊ ተቋማት እና መንግሥት ምን ሊያደርጉ ይገባል?
8-9-2024 • 42 minuten, 13 seconden የሰሞኑ ተደጋጋሚ የተፈጥሮ አደጋዎች የበርካቶችን ሕይወት ቀጥፏል
ተደጋጋሚ የተፈጥሮ አደጋዎች ያስከተሉት ጉዳት እና የመከላከል ሥራዎች በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ከሰሞኑ የተከሰቱ ተደጋጋሚ የተፈጥሮ አደጋዎች ለበርካቶች ሞት እና መፈናቀል ሰበብ ሆነዋል ። በጎፋ የመሬት መንሸራተት ከሁለት መቶ አምሳ በላይ ሰዎች መቀጠፋቸው ያጫረው የሐዘን ጠባሳ ገና አልጠገገም ። ሦስት ምሑራን እና ባለሞያዎች የተሳተፉበትን ሙሉውን ውይይት በድምፅ ማዕቀፉ መከታተል ይቻላል ።
"ህወሓት ፈረሰ ማለት የፕሪቶሪያ ስምምነት ፈረሰ ማለት ነው የሚል አባባል በውሉ የተካተቱ የትግራይ ባለድርሻ አካላትንና ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉትን የትግራይ የጸጥታ ኃይሎች መስዋዕትነት መናቅ ነው ብዬ አስባለሁ"
25-8-2024 • 41 minuten, 54 seconden ሁለተኛ ዓመቱን የያዘው የአማራ ክልል ጦርነት ማብቂያው የት ነው?
አንድ ዓመት ባለፈው የአማራ ክልል ጦርነት ከሁለቱም ወገን ፣ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የሰዎች ሕይወት እንደጠፋ በርካታ ንብረትም እንደወደመ በሰላማዊ ሰዎች ላይም የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ሴቶችንም የወሲብ ጥቃቶች ሰለባ ማድረጉን የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችባወጧቸው ዘገባዎች አስታውቀዋል።
18-8-2024 • 41 minuten, 38 seconden ሁለተኛ ዓመቱን የያዘው የአማራ ክልል ጦርነት ማብቂያው የት ነው?
17-8-2024 • 41 minuten, 38 seconden «የኤኮኖሚ ማሻሻያው» የብር አቅም መዳከም ለብዙኀኑ ሕዝብ ምን ማለት ይሆን?
11-8-2024 • 40 minuten, 58 seconden እንወያይ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዉይይት ፋይዳዉ ምን ይሆን?
ጠ/ሚኒስትሩና ተቃዋሚዎች ለዉይይት መቀመጣቸዉ በይሁንታ ቢታይም፤ ለሃገሪቱ መፍትሄ ሊያስገኝ ይገባል። በቅድምያ በሃገሪቱ የሚሰማዉን የጥይት ድምፅ ፀጥ ሊያሰኝ፤ ነፍጥ ያነገቡትን ጨምሮ በሃገሪቱ ሁሉን አካታች ዉይይት እንዲጀመር ሊያደርግ ይገባል። የፖለቲካ ምህዳሩ ሊሰፋ እና የታሰሩ ፖለቲከኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊፈቱ ይገባል።
4-8-2024 • 42 minuten, 16 seconden የጠቅላይ ሚኒስትሩና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዉይይት ምን ፋይዳ ይኖረዉ ይሆን?
4-8-2024 • 42 minuten, 16 seconden ውይይት፦ የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ላይ ይበረታል?
የኢትዮጵያ መንግሥት ተግባራዊ የሚያደርገው የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር አካል የሆኑ የተለያዩ አዋጆች ባለፉት ወራት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቀዋል። ለመሆኑ የኤኮኖሚ ማሻሻያው የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ጫንቃ ላይ ይወድቃል? በኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሚና ምንድነው? በዚህ ውይይት የገንዘብ አስተተዳደር ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ፣ በዓለም አቀፍ ተቋም ውስጥ ከፍተኛ ተመራማሪ ሆነው በመሥራት ላይ የሚገኙት ዶክተር ቀልቤሳ መገርሳ እና በዩናይትድ ኪንግደም ብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ ሥር በሚገኘው ፔሪቮሊ አፍሪካ ጥናት ማዕከል ተመራማሪው ዶክተር ኢዮብ ባልቻ ተሳትፈዋል።
28-7-2024 • 41 minuten, 26 seconden የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ላይ ይበረታል?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ “በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት” ተግባራዊ ልታደርግ እንደሆነ ገልጸዋል። የኤኮኖሚ ማሻሻያ አካል የሆነው ውሳኔ የብርን የመግዛት አቅም በከፍተኛ መጠን ያዳክማል። ይኸ ውይይት የኤኮኖሚ ማሻሻያው የሚያስከፍለው ዋጋ ማን ላይ ይበረታል? ሲል ያጠይቃል
28-7-2024 • 41 minuten, 26 seconden «ዕገታ» ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ሆኖ ወይስ በቸልተኝነት እዚህ ደረሰ?
አሁን አሁን ግጭት ጦርነት በሚደረግባቸውም ይሁን አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች ለዜጎች የየዕለት ስጋት ሆኖ የቀጠለው እና ምናልባትም ችግሩ በዚህ ከቀጠለ በሀገር ህልውና ላይ የሚያስከትለው መዘዝ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የሰላማዊ ሰዎች ዕገታ ጉዳይ ነው ።
21-7-2024 • 45 minuten, 8 seconden እንወያይ፤ ሰብዓዊ መብት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቶች ተግዳሮቶች በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን በተለያዩ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። በሌላ በኩል ለሰብዓዊ መብት የሚታገሉ እና ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚወተውቱ በሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም በስራቸው ሳቢያ ከመንግስት ጫና እና እንግልት እየጠነከረባቸው መምጣቱን እየገለፁ ነው።
14-7-2024 • 40 minuten, 52 seconden እንወያይ ፤ የሰብዓዊ መብት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተግዳሮቶች በኢትዮጵያ
14-7-2024 • 40 minuten, 52 seconden 7-7-2024 • 40 minuten, 39 seconden እንወያይ፣ የኢትዮጵያዉን ተፈናቃዮች ፈተና፣ የለጋሾች ዳተኝነት
1-7-2024 • 40 minuten, 51 seconden እንወያይ፤ በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለ ጥቃትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ዉስጥ ግጭትና ጦርነት ሴቶች ይበልጥ ግፍ ደርሶባቸዋል፤ እየደረሰባቸዉም ነዉ። ጾታዊ ጥቃትና ማዋከቦችን ለመግታት ከመንግሥትም ሆነ ከሴቶች ማህበራት በቂ ድጋፍ አልታየም ይባላል። እንደሚታወቀዉ ሴት እናት፤ እህት፤ ሚስት፤ ልጅ ናት። ለኢትዮጵያዉያን ደግሞ አገርም ናት። ግን ሴቶች ላይ እየደረሰ ያለዉ ሰቆቃ ለምን ትኩረት አልተሰጠዉም?
23-6-2024 • 41 minuten, 31 seconden እንወያይ፤ አሳሳቢዉ በሴቶች ላይ የሚሰነዘር ጥቃትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ
23-6-2024 • 41 minuten, 31 seconden የኢትዮጵያ የምርጫ ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ማሻሻያ አዋጅና ፋይዳው
ማሻሻያውን የደገፉ እርምጃው በኢትዮጵያ የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ቡድኖች ወደ ሰላማዊ ትግል እንዲገቡ የሚያበረታታ ሲሉ የማሻሻያው ተቃዋሚዎች ደግሞ ወደ አማራና አፋር ክልሎች ተስፋፍቶ በነበረው በትግራዩ ጦርነት የተፈጸሙ ወንጀሎች ፍትህ ሳያገኙ ተድበስብሰበው እንዲቀሩ የሚያደርግ ሲሉ ይቃወማሉ።
16-6-2024 • 36 minuten, 53 seconden የኢትዮጵያ የምርጫ ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ማሻሻያ አዋጅና ፋይዳው
14-6-2024 • 36 minuten, 53 seconden ግጭት ጦርነት ያጠላበት ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ
9-6-2024 • 39 minuten, 31 seconden ውይይት፦ የመንግሥት 47 ዩኒቨርሲቲዎች ሚና ከኢትዮጵያ ፍላጎት ምን ያህል የተጣጣመ ነው?
የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተዳድራቸው ዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ባለፉት ሦስት አስ ር ዓመታት ገደማ ከሁለት ወደ አርባ ሰባት አድጓል። ባለሙያዎች በተማሪዎች ቁጥር እና በመሠረተ ልማት ግንባታ ረገድ ዕድገት ቢኖርም ውጤቱ ለመንግሥትም ሆነ ለዜጎች አመርቂ አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ። በዚህ ውይይት በኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ፣ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና የኅትመት ዳይሬክተር ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ እና በደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ ተሳትፈዋል።
2-6-2024 • 40 minuten, 59 seconden የመንግሥት 47 ዩኒቨርሲቲዎች ሚና ከኢትዮጵያ ፍላጎት ምን ያህል የተጣጣመ ነው?
አየር መንገድ፣ መከላከያ ሠራዊት እና ፌድራል ፖሊስ ያቋቋሟቸውን ሳይጨምር ኢትዮጵያ 47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አሏት። የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ሲጨምር ሀገሪቱ ምን አተረፈች? የትምህርት ተቋማቱ ከገዢው ፓርቲ ምን ያክል ነጻ ናቸው? በዚህ ውይይት አቶ ኮራ ጡሹኔ፣ ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ እና ዶክተር ሰይፈ ታደለ ተሳትፈዋል።
2-6-2024 • 40 minuten, 59 seconden ከ33 ዓመታት በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ ሚና በኢትዮጵያ ፖለቲካ
26-5-2024 • 39 minuten, 25 seconden የኢትዮጵያ የግጭት አዙሪትና የአሜሪካ የፖሊሲ ንግግር
ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ግጭት በተመለከተ ከሦስት ዐሥርተ ዓመታት ወዲህ ለየት ያለ የፖሊሲ አቋሙዋን ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ከአዲስ አበባ ዐሳውቃለች ። ጉዳዩ 33 ዓመት ወደ ኋላ ወደ ለንደኑ ስብሰባም ይወስደናል ። እንዴት? መልሱን ከሳምንታዊው የውይይት መድረክ ያድምጡ ።
26-5-2024 • 39 minuten, 25 seconden የጠቅላይ ሚንስትሩ «የሰላም ጥሪ » ምን አይነት ምላሽ ያግኝ ?
19-5-2024 • 40 minuten, 58 seconden የጠቅላይ ሚንስትሩ የሰላም ጥሪ ፤ ሰላማዊ ምላሽ እንዴት ያግኝ?
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ሳምንታት መንግስታቸው ከታጣቂዎች ጋር ብርቱ ፍልሚያ እያደረገ ወደ ሚገኝባቸው የኦሮሚያ እና አማራ ክልል አካባቢዎች አቅንተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በሁለቱም አካባቢዎች በጥቅሉ ጦርነት እንዲቆም ብሎም «በወንድማማቾች መካከል የሚደረግ መገዳደልም እንዲያበቃ » ጥሪ አስተላልፈዋል።
19-5-2024 • 40 minuten, 58 seconden የሁለቱ ወገኖች የስልጣን ሽኩቻ ወዴት ያመራ ይሁን?
በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና በህወሐት መካከል ያለው የስላጣን ሽኩቻ ተካሮ አንዱ በአንዱ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻው በግላጭ እየተካሄደ ከመሆኑም አልፎ ጎራ ለይተው እስከመገዳደል እንዳይደረስና የተገኘው አንጻራዊ ሰላም እንዳይደፈርስ ብዙዎቹ የክልሉ ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
12-5-2024 • 40 minuten, 51 seconden እንወያይ፤ ኢትዮጵያ ሌላ ዙር ግጭትን ለመሸከም ጫንቃዉ አላት?
ትግራይና አማራ ክልል በሚወዛገቡባቸዉ አካባቢዎች የተቀሰቀሰዉን ዉጥረት እንዴት አያችሁት? ምንስ ተሰማችሁ? ከየትኛዉም ወገን ይሁን ያ ሁሉ ህዝብ ካለቀ እና ንብረት ከወደመ በኋላ በፕሪቶርያዉ ስምምነት ሰላም ይሰፍናል ተብሎ ሲጠነቅ ዳግም ወደ ሌላ ዉጥረት እየተገባ ነዉ? ይህን ዉጥረት ህዝቡና ሃገሪቱ መሸከም ይችላሉ? ምንድን ነዉ መደረግ ያለበት?
28-4-2024 • 45 minuten, 49 seconden አደገኛው የኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰት
ወደ ሳዑዲ አረብያ ለመሄድ ጉዞ የጀመሩ 38 ኢትዮጵያውያን ጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ የተጫኑበት ጀልባ ሰጥሞ ባለፈው ሳምንት ሞተዋል። በዚሁ ሳምንት ነበር ሳዑዲ አረብያ ውስጥ ችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ጥረት የቀጠለው።በአሁኑ ጊዜ በአደገኛ ጉዞ መላልሰው ወደ መካከለኛው ምሥራቅና ወደ ደቡብ አፍሪቃ የሚሄዱ ጥቂት አይባሉም።
21-4-2024 • 42 minuten, 10 seconden አደገኛው የኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰት
21-4-2024 • 42 minuten, 10 seconden በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕጣ ፈንታ
14-4-2024 • 39 minuten, 29 seconden ኢትዮጵያ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስድስት የሥልጣን ዓመታት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን የያዙበት ስድስተኛ ዓመት ደጋፊዎቻቸው በሰልፍ ተቃዋሚዎቻቸው በትችት አስበውታል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ጆን አሕመድ፣ ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ሙከርም ሚፍታህ፣ ከጁሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ሰይፈ ታደለ የተሳተፉበት ውይይት ለመሆኑ ዐቢይ ምን አሳክተው ምን አጎደሉ? ሲል ያጠይቃል
7-4-2024 • 43 minuten, 21 seconden እንወያይ፦ ኢትዮጵያ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስድስት የሥልጣን ዓመታት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን የያዙበት ስድስተኛ ዓመት ደጋፊዎቻቸው በሰልፍ ተቃዋሚዎቻቸው በትችት አስበውታል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ጆን አሕመድ፣ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር ሙከርም ሚፍታህ በደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር ሰይፈ ታደለ የተሳተፉበት ውይይት በስድስት ዓመታት ዐቢይ ምን አሳክተው ምን አጎደሉ? ሲል ያጠይቃል።
6-4-2024 • 43 minuten, 21 seconden የፊት ለፊቱ ንግግር አንድምታ እና የኢትዮጵያ መሻት
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የትግራዩ ጦርነት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተለያዩ ክልሎች የህዝብ ተወካዮች ጋር በተከታታይ ውይይት እያደረጉ ነው። በየውይይቱ ክልሎቹም ሆኑ የኃይማኖት ተቋማቱ በተናጥል እና የጋራ ወቅታዊ የሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ ፣ አስተያየት እና ጥቆማ ሰጥተዋል፤ አፋጣኝ ምላሽ ይሻሉ ያሏቸውንም ጥያቄዎች አንስተዋል።
24-3-2024 • 41 minuten, 31 seconden ግጭት ጦርነት እንዲቆም ፤ ፖለቲካዊ ንግግር በአፋጣኝ እንዲጀመር ከተወያዮች ጥያቄ ቀርቧል
24-3-2024 • 41 minuten, 31 seconden ከፕሪሪቶሪያ ስምምነት አፈጻጸም ምን እንማር?
አፈራራሚዎቹ በግጭቱ የተጎዱትን መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ ተጎጂዎችን ያማከለ የሽግግር የፍትሕ ሂደት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የስምምነቱ ፈራሚዎች መገናኘታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አድርገዋል።እነዚህ የበለፀጉ እንዲሁም በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተከሰቱት ቀውሶች በተመሳሳይ ቁርጠኝነት ችግሩ እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።
17-3-2024 • 40 minuten, 53 seconden ዉይይት፣ የኦሮሚያና የአማራ ክልል ግጭቶች ለምን አይቆሙም?
የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች፣የመብት ተሟጋቾች፣የርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ከሁሉም በላይ የየአካባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት በየግጭት፣ ዉጊያ ጥቃቶቹ የሚያልቅ፣ የሚቆስል፣የሚፈናቀለዉ ሕዝብና የምትደፈረዉ ሴት ቁጥር እየጨመረ ነዉ።
10-3-2024 • 40 minuten, 24 seconden ዉይይት፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የሚደረጉት ግጭቶች ለምን አይቆሙም?
10-3-2024 • 40 minuten, 24 seconden አሳሳቢው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ በአማራ ክልል
ኢሰመኮ በቅርቡ በመርዓዊ ከተማ በሲቭሎች ላይ በመከላከያ ሠራዊት ከሕግ ውጭ ግድያዎች መፈጸሙን ለማወቅ መቻሉን አስታውቋል። በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር ያረጋገጠው መንግሥት የመከላከያ ኃይሉ የትኛውንም ዓይነት ሲቪል ዒላማ አላደረገም ሲል አስተባብሏል።
25-2-2024 • 39 minuten, 30 seconden አሳሳቢው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ በአማራ ክልል
25-2-2024 • 39 minuten, 30 seconden 50 ዓመታት፦ የኢትዮጵያ አብዮት ውርስ ምንድነው?
የአጼ ኃይለሥላሴን ዘውዳዊ መንግሥት ከፍጻሜ ያደረሰው የኢትዮጵያ አብዮት 50 ዓመታት ሞላው። የካቲት 1966 “ፈነዳ” የሚባለው አብዮት “መሬት ላራሹ” የተፈከረበት፣ የብሔሮች እና የሐይማኖት ዕኩልነት የተጠየቀበት ነው። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር መላኩ ተገኝ እና ዶ/ር ኢዮብ ባልቻ የተሳተፉበት ውይይት የአብዮቱ ውርስ ምንድነው? ሲል ያጠይቃል።
18-2-2024 • 40 minuten, 45 seconden 50 ዓመታት፦ የኢትዮጵያ አብዮት ውርስ ምንድነው?
የአጼ ኃይለሥላሴ ዘውዳዊ መንግሥትን በማስወገድ የፊውዳላዊ ሥርዓትን ከፍጻሜ ያደረሰው የኢትዮጵያ አብዮት የተቀሰቀሰው ከ50 ዓመታት በፊት ነበር። በየካቲት ወር 1966 “ፈነዳ” የሚባለው አብዮት “መሬት ላራሹ” የተፈከረበት፣ የብሔሮች፣ የሐይማኖት ዕኩልነት የተጠየቀበት ነው። የታክሲ አሽከርካሪዎች፣ ሠራተኞች፣ መምህራን እና ወታደሮች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንገብ በየፊናቸው በዘውዳዊው መንግሥት ላይ ጫና ያደርጉ ነበር። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ዶክተር መላኩ ተገኝ እና ዶክተር ኢዮብ ባልቻ የተሳተፉበት ውይይት የኢትዮጵያ አብዮት ውርስ ምንድነው? ሲል ያጠይቃል።
17-2-2024 • 40 minuten, 45 seconden እንወያይ፤ በአንድ ላይ ቆመው ለኢትዮጵያ ይጮሁ የነበሩ ወገኖች ዛሬ የት ናቸዉ?
4-2-2024 • 43 minuten, 36 seconden እንወያይ፤ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሚና ከየት ወዴት?
በዉጭ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊና ትዉልደ ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራ) በኢትዮጵያ ፖለቲካ፤ ኢኮኖሚና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ፤ ከፍተኛ ሚናን እንደሚጫወት ይታወቃል። አሁን አሁን ግን አብዛኛዉ ዲያስፖራ በዘላቂ የአገሪቱ ጥቅሞች ላይ አንድ ላይ መቆሙ ቀርቶ፤ ተጻራሪና ግዚያዊ የሆኑ የቡድን ፍላጎቶችን ይዞ በየፊናው ቆሞ መታየቱ የተለመደ ሁኗል። ችግሩ ምን ይሆን?
4-2-2024 • 43 minuten, 36 seconden ዉይይት፣ የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ ስምምነት፣ ድጋፍ፣ተቃዉሞና ዉግዘቱ
በዓባይ ወንዝ ዉኃ አጠቃቀም ሰበብ ከኢትዮጵያ ጋር የምትወዛገበዉ ግብፅ ደግሞ ለዉጊያም እየተጋበዘች ነዉ።የግብፅ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚሕ ሽኩሪ ኢትዮጵያን «የአካባቢዉ ያለመረጋጋት ምንጭ» በማለት ወንጅለዋታል።የሐገሪቱ ፕሬዝደንት የቀድሞዉ ፊልድ ማርሻል አብዱልፈታሕ አልሲሲ በበኩላቸዉ ሶማሊያና ደሕንነቷ ላደጋ ከተጋለጠ ግብፅ ጣልቃ ለመግባት
28-1-2024 • 41 minuten, 2 seconden ዉይይት፣ የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ ስምምነት፣ ድጋፍ፣ተቃዉሞና ዉግዘቱ
26-1-2024 • 41 minuten, 2 seconden የኢትዮጵያ የጸጥታ እና የደህንነት ተቋማት ወቅታዊ ሁኔታ
21-1-2024 • 43 minuten, 5 seconden ከውጭና ከሃገር ውስጥ በተሰበሰበ የአገሪቱ ሀብት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት እየተገነቡ ያሉ የመናፈሻዎችና የቤተመንግስት ግንባታዎች፤ በቀጥታ ከመንግስት ካዝና በቢልዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ተደርጎ የሚካሄዱ የመንግስት መስሪያቤቶች እድሳት አነጋጋሪነታቸው እንደቀጠለ ነው።
7-1-2024 • 40 minuten, 18 seconden ውይይት፦ ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ማዳከም ወይስ…የኢትዮጵያ አጣብቂኝ
ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ባለፉት አራት ዓመታት በባንኮችም ይሁን በጎንዮሽ ገበያው ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። ብር ሲዳከም ለኢትዮጵያ ምን ፈየደ? ለሀገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ሁለተኛ ምዕራፍ ዳጎስ ያለ ማስፈጸሚያ የሚሻው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሚቀነቀነውን ብርን የማዳከም እርምጃ ሊቀበል ይችላል?
የኢትዮጵያ አጣብቂኝ፦ ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ማዳከም ወይስ…?
ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ባለፉት አራት ዓመታት በባንኮችም ይሁን በጎንዮሽ ገበያው ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። ብር ሲዳከም ለኢትዮጵያ ምን ፈየደ? ለሀገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ሁለተኛ ምዕራፍ ዳጎስ ያለ ማስፈጸሚያ የሚሻው መንግሥት በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሚቀነቀነውን ብርን የማዳከም እርምጃ ሊቀበል ይችላል?
17-12-2023 • 39 minuten, 33 seconden እንወያይ፤ በአማራ ክልል የቀጠለዉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማቆምያዉ የት ነዉ?
ለአማራ ክ ልሉ ሰብዓዊ ቀዉስ ተጠያቂዉ ማን ነዉ? በትግራይ ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተገድለዋል። አሁንም በአማራና በኦሮሚያ ክልል ጦርነቱ ቀጥሏል። መንግሥት ከቀዉስ ማትረፍ ፖሊሲዉን ማቆም አለበት፤ ጠ/ሚኒስትሩ ስልጣን መልቀቅ አለባቸዉ፤ በሃገሪቱ የተኩስ አቁም ታዉጆ ዉይይት መጀመር አለበት» ይላሉ ተወያዮች እርሶስ?። እርሶስ? ይጻፉልን!
10-12-2023 • 43 minuten, 15 seconden 26-11-2023 • 40 minuten, 22 seconden የሰላም ንግግሩ ተስፋ እና የሀገሪቱ መጻኢ ዕጣ ፈንታ
ከወራት ዝምታ በኋላ ተፋላሚ ወገኖች ለ ሌላ የሰላም ንግግር በታንዛንያዋ የንግድ ከተማ ዳሬ ሰላም ተቀምጠዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም ንግግር እየተደረገ መሆኑን ከሳምንት ዝምታ በኋላ ባለፈው ሐሙስ ነበር ይፋ ያደረገው ። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተደራዳሪዎቹ ከመንግስት ተወካዮች ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ቀደም ብሎ ነበር ያስታወቀው።
19-11-2023 • 43 minuten, 41 seconden መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር የሚያደርገው የሰላም ንግግር ዘላቂ ሰላም ያመጣ ይሆን ?
19-11-2023 • 43 minuten, 41 seconden ከምንም በላይ ሕጻናት፤ ሴቶችና አረጋውያን ተጎጂዎች ናቸው
በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ላይ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች
5-11-2023 • 36 minuten, 28 seconden በተፈናቃዮች ላይ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብቶችት ጥሰቶች
ድንገት ተፈናቅለው በወጡበት የቀሩ ፣በማያውቁትና መጠለያ ሊባሉ በማይችሉ ስፍራዎች ለብዙ ጊዜያት የቆዩ በርካቶች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ችግሮቻቸው እየተባባሱ እንጂ እየቀነሱ አልሄዱም። በመጠለያ ጣቢያዎች ለከፋ ችግር ከተጋለጡት አብዛኛዎቹ ምርጫ በማጣታቸው ወደ ቀድሞው ቀያቸው ለመመለስ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። ሆኖም የጸጥታ ስጋት አላቸው።
5-11-2023 • 36 minuten, 28 seconden ዉይይት፣ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብርና አሰራር
27-10-2023 • 39 minuten, 51 seconden እንወያይ፤ የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደቁ የተባሉበት አሳሳቢዉ ዉጤትና አንደምታዉ
ከ 800 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች መዉደቃቸዉ ብቻ ሳይሆን፤ በችግር ያስተማሩ ወላጆች ብሎም በህብረተሰቡ ላይ የሚፈጥረዉ ጫና ቀላል አለመሆኑ ነዉ። የችግሩ መንስኤ ምንድነው? የትምህርት ስርዓት ዉድቀት? ጥቂት ተማሪዎች ብቻ ለከፍተኛ ተቋማት በቁ፤ ብዙኃኑ ግን ወድቋል፤ የተባለለበትን ፈተና የወደቀዉ ማነዉ? እንዴት ትገመግሙታላችሁ? ጻፉልን!
22-10-2023 • 39 minuten, 41 seconden በተስፋ የተሞሉ ተማሪዎች መዉደቃቸዉ የተሰማበት ዜና፤ በኑሮ ዉድነት በቀዉስ ብሎም ከጦርነት ወጥታ ወደ ሌላ ጦርነት ለገባችዉ ሃገር ኢትዮጵያ ሌላ እራስ ምታት ነዉ። ሃላፊነቱን ማን ይዉሰድ?
22-10-2023 • 39 minuten, 41 seconden ውይይት፦ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ለመመርመር የተቋቋመው ኮሚሽን ሥራ መቋረጥ ምን ያጎድላል?
15-10-2023 • 40 minuten, 3 seconden ያለተጠያቂነት እየተባባሰ የመጣው የሰብአዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ
9-10-2023 • 39 minuten, 48 seconden «በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ከሰብአዊ መብት አንጻር እንዴት ይታያል?»
በኢትዮጵያ ሚሊዮኖች የሚኖሩባቸው የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከኢንተርኔቱ ዓለም እንዳይገናኙ ከተዘጋባቸው ሰነባብተዋል ። ሌላው ቀርቶ የቀጥታ ስልክ መስመር አገልግሎት የማያገኙ አካባቢዎች እና ከተሞች ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ። በኢትዮጵያ አንዳች ነገር ኮሽ ሲል የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት በተደጋጋሚ ሲቋረጥ ይስተዋላል ።
24-9-2023 • 40 minuten, 4 seconden አዲሱ ዓመት ለተቀጣሪው ሰራተኛ ተስፋ ወይስ ስጋት ?
በሀገሪቱ በተለይ የመሰረታዊ ፍጆታ ቁሶች እና የቤት ኪራይ በየጊዜው ያለከልካይ እጅግ በተጋነነ ሁኔታ ጭማሪ ሲያሳዩ ሰራተኛው በወር በሚያገኘው ደመወዝ ላይ ጭማሪ ስለመደረጉ ብዙም አይሰማም ወይም ቢኖርም ያለውን የገበያ እና የኑሮ ሁኔታ የሚመጥን ሆኖ አለመገኘቱ ነው የሚነገረው ።
17-9-2023 • 45 minuten, 28 seconden በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው ተቀጣሪ የህብረተሰብ ክፍል ተስፋው ምን ይሆን?
17-9-2023 • 45 minuten, 28 seconden 2015 ግጭቶች የተካሄዱበት፣ የመንግሥት ተባባሪ የነበሩ ውጊያ የገጠሙበት ፣ጎሳ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የደረሰበት ፣ቤቶች የፈረሱበት ሰዎች የተፈናቀሉበት፣ የኑሮ ውድነት እጅግ የናረበት ጋዜጠኞች የታሰሩበት ኢንተርኔትም የተቋረጠበት ዓመት ነበር። እነዚህ ችግሮች ወደ 2016 ዓም እንዳይሻገሩ ለመከላከል ምን መደረግ አለበት?
10-9-2023 • 41 minuten, 41 seconden የአማራ ክልል ግጭት፤ የጅምላ እስር እና የመገናኛ አውታሮች ሽፋን
አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የአማራ ተወላጆች በጅምላ ለእስር መዳረጋቸው ከብዙ አቅጣጫ ይሰማል ። ብሔር ተኮር እስሩ መባባሱ፤ ትምህርት ቤቶች ጭምር በታሰሩ ሰዎች መጨናነቃቸውን በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ለመሆኑ ይህ ምን ያህል የመገናኛ አውታሮች ሽፋን አገኘ?
27-8-2023 • 39 minuten, 54 seconden እንወያይ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ሰላምን ያመጣ ይሆን?
ተወያዮች፤የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተፈጥሮዉ መብት ገዳቢ ነዉ፤ኢትዮጵያም ተሞክሮ ይህንኑ ያሳያል። መንግሥትን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ዝም ያለዉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሁሉ ለሰላም ወደ ድርድር እንዲመጡ፤ጦርነትም ይቁም ሲሉ ጥሪ አሰምተዋል።መንግሥት የጅምላ እስሩን ያቁም፤የአማራ ክልልን ጥያቄዎች ይመልስ ብለዋል። እርሶስ? አስተያየት አሎት?
20-8-2023 • 42 minuten, 47 seconden የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ሰላምን ያሰፍን ይሆን? የክልሉን ጥያቄዎችስ ይፈታ ይሆን?
20-8-2023 • 42 minuten, 47 seconden ውይይት፦ የአማራ ክልል ቀውስ ገፊ ምክንያቶች፣ ዳፋው እና በውይይት የመቋጨት ተስፋ
15-8-2023 • 39 minuten, 58 seconden የአማራ ክልል ቀውስ፦ ገፊ ምክንያቶች፣ ዳፋው እና በውይይት የመቋጨት ተስፋ
በአማራ ክልል ሲብላላ የቆየው ቅራኔ በሣምንቱ መጀመሪያ ወደ ውጊያ ቢያመራም የመረጋጋት ዝንባሌ አሳይቷል። የቀውሱ ገፊ ምክንያቶች ምንድናቸው? በውይይት ካልተቋጨ በአማራ ክልል እና በኢትዮጵያ ላይ የሚያስከትለው ዳፋ ምን ሊሆን ይችላል? ዶክተር ታደሰ ጥሩነህ፣ ዶክተር ብዙነህ ጌታቸው እና ዶክተር ሰማኸኝ ጋሹ በዚህ ውይይት ተሳትፈዋል።
14-8-2023 • 39 minuten, 58 seconden የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት ተስፋ እና ስጋት
30-7-2023 • 40 minuten, 9 seconden 2-7-2023 • 40 minuten, 40 seconden ውይይት፦ የዎላይታ ሕዝበ-ውሳኔ እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ
25-6-2023 • 38 minuten, 32 seconden 4-6-2023 • 39 minuten, 59 seconden 28-5-2023 • 41 minuten, 55 seconden እንወያይ፤ ኢትዮጵያ ከግጭትና ቀዉስ አዙሪት እንዴት ትዉጣ?
በተለያዩ የግጭት ምዕራፍ ውስጥ ገብታ እየተናጠች ያለችው ኢትዮጵያ መውጫዋ ወዴት ይሆን? ምንድን ነዉ ከአንዱ ችግር ወጥተን ወደሌላ ችግር የምንገባበት ምክንያት? መንግሥትን ለመጣል የሚደረግ ትጥቅ ትግል ጊዜዉ ነዉ ወይ? መንግሥትም ሆነ ታጣቂዎች ጦርነት ዉስጥ መግባት ህዝብን ጦርነት ዉስጥ ማስገባት መቼ ነዉ የሚቆመዉ? ከየት ይምጣ ዘላቂው መፍትሄ?
28-5-2023 • 41 minuten, 55 seconden አሳሳቢ እየሆነ የሄደው የፕረስ ነጻነት ይዞታ በኢትዮጵያ
14-5-2023 • 40 minuten, 20 seconden እንወያይ፦ የሸገር ከተማ አስተዳደር ቤት ፈረሳ እና ውዝግቡ
23-4-2023 • 40 minuten, 42 seconden የክልል ልዩ ኃይሎች መፍረስ እና አንድምታው
16-4-2023 • 42 minuten, 47 seconden የጉራጌ የክልልነት ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ እና ምላሹ
በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 47 መሰረት ማንኛውም ብሔር ብሔረሰብ በማንኛውም ጊዜ የክልልነት ጥያቄ ማንሳት ሕገ መንግሥታዊ መብቱ እንደሆነ ይደነግጋል ። ለመሆኑ የጉራጌ ሕዝብ ክልል ልሁን፤ ራሴን በራሴም ላስተዳድር ብሎ ያቀረበው ጥያቄ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ከመንግሥት የተገኘው ምላሽስ ምንድን ነው? ሳምንታዊ እንወያይ መሰናዶ።
9-4-2023 • 40 minuten, 36 seconden ኢትዮጵያ ለሽግግር ፍትህ ዝግጁ ነች? የፍትህ ሚኒስቴር ካቋቋመው ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን አቶ ምስጋናው ሙሉጌታ እና ዶ/ር ማርሸት ታደሰ፤ በሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት የሰብዓዊ መብቶ ች መርሐ-ግብር ተባባሪ ዳይሬክተር ዶክተር አባድር ኢብራሒም እና ዘ-ሔግ በሚገኝ ፍርድ ቤት በአማካሪነት የሚሰሩት አቶ ካሳሁን ሞላ በውይይቱ ተሳትፈዋል
26-3-2023 • 43 minuten, 38 seconden ውይይት፦ ኢትዮጵያ ለሽግግር ፍትህ ዝግጁ ነች?
26-3-2023 • 43 minuten, 38 seconden ዉይይት፤ የፕሪቶርያዉ ስምምነት በርግጥ ተፈጻሚ እየሆነ ነዉ?
ፕሪቶርያ ላይ በሰላም ስምምነት ከተቋጨ አራት ወር የሆነዉና አስከፊ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈፀመበት የሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት ቢያበቃም ብዙዎች በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ላይ ጥርጣሬ አላቸዉ። መንግሥት ስምምነቱን እያስፈጸመ አይደለም፤ የሚሉ እንዳሉ ሁሉ ህወሓት ሁሉን አካታች የሆነ ሽግግር መንግሥት ለመመስረት አልቻለም፤ የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም።
20-3-2023 • 42 minuten, 33 seconden የፕሪቶርያዉ የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት በምን ደረጃ ላይ ነዉ? የፌደራል መንግሥት እና ህወሓትስ ምን ተወያዩ? ምንስ ተስማማ?
19-3-2023 • 42 minuten, 33 seconden 12-3-2023 • 38 minuten, 44 seconden የሩስያና ዩክሬን ጦርነት ወዴት እያመራ ነው?
26-2-2023 • 40 minuten, 1 seconde ሶስት ሕዝበ-ውሳኔዎች፤ አራት ክልሎች፦ የደቡብ ጥያቄ ተመለሰ?
13-2-2023 • 40 minuten, 25 seconden የአዲስ አበባ የተጨማሪ ቋንቋ ስርዓተ ትምሕርት አተገባበርና ትችቱ
22-1-2023 • 39 minuten, 37 seconden የአዲስ አበባ የአንደኛ ደረጃ የተጨማሪ ቋንቋ ስርዓተ ትምሕርት አተገባበርና ትችቱ
ተማሪዎች ተጨማሪ የአገር ውስጥ ቋንቋ እንዲማሩ የሚያደርገውን ውሳኔ ጠቀሚ ሲሉ የደገፉት እንዳሉ ሁሉ በጥድፍያ የተከናወነና ፖለቲካዊ ጫናም ያረፈበት ነው በማለት የተቹትም አሉ። የከተማዋ ነዋሪ በጉዳዩ ላይ በቂ ውይይት አላካሄደም የትምሕርቱም አዋጭነት በሙከራ ደረጃ ሳይፈተሽ ተግባራዊ መሆኑ አግባብ አይደለም የሚሉና የመሳሳሉ ትችቶችም ቀርበውበታል
22-1-2023 • 39 minuten, 37 seconden መንግሥት ካጠፋን ቆንጥጡን ብሏል? በሰላሙ ጥረት ማህበረሰቡ እንዲነጋገር ለምን መድረክ አልተሰጠዉም?
15-1-2023 • 40 minuten, 44 seconden ዉይይት፤ የኢትዮጵያዉያን ማህበራዊ መስተጋብር እንዴት ይመለስ?
የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት እርቅ ሲፈፅሙ በጦርነት ዉስጥ የነበረዉ ማኅበረሰብ እፎይ ይበል እንጂ ማኅበረሰቡ ለዘመናት አብሮት ከኖረዉ ህዝብ ጋር አሁንም እንደተራራቀ ነዉ። የሁለት ዓመቱ የእርስ በርስ ጦርነት በማኅበራዊ መስተጋብሩ ላይ ከፍተኛ ጠባሳን ጥሎ ነዉ ያለፈዉ። በህብረተሰቡ ውስጥ እውነተኛ እርቅና ይቅርታ እንዲመጣ ምን መደረግ አለበት?
15-1-2023 • 40 minuten, 44 seconden ወጣቶቹን የሚያረግፈው ስደት፦ ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አፍሪካ
በጥቅምት እና ሕዳር ወራት ከ50 በላይ የኢትዮጵያውያን አስከሬኖች በማላዊ እና በዛምቢያ ተገኝተዋል። በየአገራቱ የተካሔዱ ምርመራዎች በመንገድ ላይ ሞተው የተገኙት ኢትዮጵያውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ በማምራት ላይ እንደነበሩ የሚጠቁሙ ናቸው። ይኸ ውይይት የጉዞ መስመሩን ጠባይ፣ የስደቱን ገፊ ምክንያቶች እና የኢትዮጵያውያኑን መከራ የሚመረምር ነው።
3-1-2023 • 41 minuten, 44 seconden ውይይት፤ ወጣቶቹን የሚያረግፈው ስደት፦ ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አፍሪካ
1-1-2023 • 41 minuten, 44 seconden የመገናኛ አውታሮች ሁለት ገጽታ በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ አንዳንድ የመገናኛ አውታሮች በጥቃት አድራሾች ሊድበሰበሱና ሊዳፈኑ ይችሉ የነበሩ የግፍ ተግባራትን፣ ግድያዎችን፤ አላግባብ እስሮችንና ሌሎች በደሎችን በማጋለጥ በተለይ የማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች ከፍተኛ አስተዋጽዖ ሲያበረክቱ ይታያል። ግድያ፤ ጭፍጨፋና ማፈናቀሎችን የሚያስፋፉ አደገኛ መረጃዎችን በማሰራጨት በብርቱ የሚተቹም አሉ። ውይይት
ተወያዮች «በመንግሥት በኩል ያለዉ ዝምታ ምን እንደሆነ ለማወቅ ተቸግረናል።»
11-12-2022 • 42 minuten, 10 seconden ዉይይት፤ ስንቱ ሲሞት ነዉ በኢትዮጵያ መግደልና መገዳደል የሚቆመዉ?
ሰሜን ኢትዮጵያ ይካሄድ የነበረዉ ጦርነት በሰላም ስምምነት መቆሙ የፈጠረዉ ስሜት ሳይቀዘቅዝ፤ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብሔርን መሰረት ያደረገዉ ግጭትና ጥቃት አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሷል። በተለያዩ የወለጋ ዘኖች አካባቢ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ባነጣጠረዉ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለው፤ በሺዎች የሚቆጠሩ በየአካባቢዉ እየተሰቃዩ ነዉ።
11-12-2022 • 42 minuten, 10 seconden ውይይት፦ የኢትዮጵያ "ደህንነት ተግዳሮት" የተባለው "የተደራጀ ሌብነት" በኮሚቴ ሥራ ይቆማል?
4-12-2022 • 40 minuten, 28 seconden የኢትዮጵያ "ደህንነት ተግዳሮት" የተባ ለው "የተደራጀ ሌብነት" በኮሚቴ ሥራ ይቆማል?
የኢትዮጵያ መንግሥት የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ እና የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት ባልደረቦችን ጨምሮ በሙስና የተጠረጠሩ ሹማምንት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። በጸረ-ሙስና ዘመቻው የጸጥታ፣ የፍትኅና የመሬት አስተዳደር ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል። የጸረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ የአገር ደህንነት ሥጋት የተባለውን ሙስና ማቆም ይችላል?
4-12-2022 • 40 minuten, 28 seconden የህዳር 11 ቀን 2015 ዓ/ም የእንወያይ ዝግጅት
20-11-2022 • 40 minuten, 50 seconden የትጥቅ መፍ ታት እና የመከላከያ ያልሆኑ ኃይሎች ከክልሉ መውጣት አንድምታ
ግጭት ጦርነቱ ቆሞ ሰላም እንዲወርድ ችግሮች በንግግር ይፈቱ ዘንድ ይወተውቱ የነበሩቱ አሁን ስምምነቱን በደስታ ከመቀበል ባሻገር አሁን ጥያቄው ስምምነቱ በእርግጥ ተግባራዊ ይሆን የሚለው ሆኗል።
20-11-2022 • 40 minuten, 50 seconden ቃለ መጠይቅ ከፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ጋር
15-11-2022 • 24 minuten, 56 seconden ዘላቂ መፍትኄ የሚሻው የፀጥታ ስጋት በኦሮሚያ ክልል
ከሰሞኑ በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል የሰላም ስምምነት መደረጉን በርካቶች በበጎ ጎኑ ቢቀበሉትም በመላ ሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ግን ሌሎች ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎችም ሰላማዊ መፍትኄ እንዲፈለግ ተደጋጋሚ ጥሪ ይሰማል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል ያለው የፀጥታ ችግር እጅግ መባባሱ መነጋገሪያ ኾኗል።
13-11-2022 • 38 minuten, 7 seconden በኦሮሚያ ክልል የፀጥታው ችግር ከሰሞኑ ተባብሶ ቀጥሏል
13-11-2022 • 38 minuten, 7 seconden 6-11-2022 • 36 minuten, 28 seconden ዉይይት፤ በጦርነት ዛቻና ፕሮፖጋንዳ የታጀበዉ የሰላም ድርድር
„የሰላም ንግግሩ ጠረቤዛ ጠባብ ነዉ። ችግሩ በጦርነት ላይፈታ ለምን ሰዉ ያልቃል፤ አገር ይወድማል? ህብረተሰቡ መራብ፤ መገደል፤ ተስፋ መቁረጥ ይብቃን ብሎ መንቃት አለበት ። እነዚህ ቡድኖች የሚወዛገቡበት ችግር የጎበዝ አለቃ አይነት ክርክር ነዉ። ከዉይይቱ በፊት ተኩስ ማቆም ግዳጅ መሆን ነበረበት። የኤርትራ ሰራዊት በቀላሉ ይወጣልስ?“
30-10-2022 • 40 minuten, 43 seconden ዉይይት፤ በጦርነት ዛቻና ፕሮፖጋንዳ የታጀበዉ የሰላም ድርድር
30-10-2022 • 40 minuten, 43 seconden የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሂደት ችግሮችና አስተምህሮቱ
23-10-2022 • 39 minuten, 33 seconden የ2014 ዓ.ም. 12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሂደት ችግሮችና አስተምህሮቱ
ባለፈው ሳምንት ፣በአራት የአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ለመፈተን ከሄዱ ተማሪዎች ፈተናውን ጥለው ወጡ የተባሉ ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች፣ዳግም ፈተና እንዳይወስዱ ትምሕርት ሚኒስቴር መወሰኑ ሲያነጋግር ከርሟል። የፈተናው ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችና አስተምህሮቱ የዚህ ውይይት ትኩረት ነው።
23-10-2022 • 39 minuten, 33 seconden ድርድሩ መክሸፍ፣ ዉጊያዉና የድርድር ባሕል
16-10-2022 • 41 minuten, 59 seconden የዋጋ ንረት፦ ገፊ ምክንያቶች፣ የብሔራዊ ባንክ እርምጃ እና የወደፊት ሥጋቶች
9-10-2022 • 39 minuten, 21 seconden የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እና የጎረቤት ሃገራት ሚና
ሰላማዊ መፍትሔ ያጣው የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ጨምሮ ሀገ ሪቱን ለሚያብጠው አለመረጋጋት በጦርነቱ በቀጥታ በመሳተፍም ሆነ ግጭቶች እንዲባባሱ የጎረቤት ሃገራት ሚና እንዳላቸው በስም እየተጠቀሰ ሲነገር ይሰማል። ድርድን በመደገፍ ለሰላም ንግግሩ ቁርጠኛ አቋም እንዳላቸው የገለጹ የጎረቤት ሃገራት እንዳሉ ስማቸው ይጠቀሳል።
2-10-2022 • 38 minuten, 37 seconden እንወያይ፦ ያለመተማመን፤ የሰላም ውይይት እንቅፋት
25-9-2022 • 39 minuten, 17 seconden «ማጠንጠኛው ተጠያቂነት ነው» የእንወያይ መሰናዶ
11-9-2022 • 39 minuten, 41 seconden ኢትዮጵያ፦ በግጭት ጦርነቱ የሰላማዊ ዜጎች መብት ጥሰት
ኢትዮጵያ ውስጥ በግጭት ጦርነቱ የተነሳ ሰላማዊ ዜጎች በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ አሰቃቂ በሆነ መልኩ ሲገደሉ፤ ጥቃት ሲደርስባቸው እና በገፍ ሲፈናቀሉ ይታያል። በግጭት ጦርነቶች ወቅት የሰላማዊ ዜጎች የሰብአዊ መብት አጠባበቅ» ምን ይመስላል? የሰብአዊ መብት ተሟጋች ባለሞያዎችን ለውይይት ጋብዘናል። ሙሉው ውይይት ከታች በድምፅ ይገኛል።
11-9-2022 • 39 minuten, 41 seconden የኢትዮጵያ ፖለቲካ ክሽፈትና ዳግም ያገረሸዉ ጦርነት
4-9-2022 • 39 minuten, 58 seconden እንወያይ፦ ኢትዮጵያ ሌላ ዙር ጦርነት የሚሸከም ጫንቃ ይኖራታል?
28-8-2022 • 41 minuten, 45 seconden እንወያይ፤ የክልልና የክላስተር አደረጃጀት ተግዳሮት ወይስ መፍትሄ?
«የደቡብ ክልል በፊትም የተዋቀረበት መንገድ ችግር ያለበት ነዉ። ህዝብ ተወያይቶበት እና አምኖበት የተቀበለዉ ሳይሆን የተጫነበት ነዉ። የፖለቲካ ባህላችን መቀየር አለበት። አሁን በደቡብ ክልል ይደረግ የተባለዉ አደረጃጀት እና ህዝቡ የሚፈልገዉ አደረጃጀት ለየቅል ነዉ። ግጭትና ዉዝግብን አስከትሏል።ህዝብ ሕገ መንግሥታዊ መብቱ ሊከበርለት ይገባል።»
21-8-2022 • 41 minuten, 1 seconde ተወያዮች «የችግሮቹ ሁሉ ምንጭ ሕገ መንግሥቱ ነዉ። ልንከልሰዉ ይገባል»
21-8-2022 • 41 minuten, 1 seconde እንወያይ፦ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ውሳኔ እና የሚጠበቁት አዳዲስ ክልሎች ጉዳይ
14-8-2022 • 41 minuten, 3 seconden 31-7-2022 • 40 minuten, 14 seconden «የሙስናዉ ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ነዉ...»
24-7-2022 • 37 minuten, 50 seconden የነዳጅ ድጎማ ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብት ምን ይዞ ይመጣል?
የነዳጅ ድጎማ ብቻውን ኢትዮጵያን ከ146.6 ቢሊዮን ብር በላይ ለሆነ የበጀት ጉድለት እንደዳረጋት መንግሥት አስታውቋል። የነዳጅ ድጎማውን በሒደት የሚያነሳ ማሻሻያ መንግሥት ገቢራዊ እያደረገ ነው። ማሻሻያው ጦርነት፣ ድርቅና የዋጋ ግሽበት ለተጫነው ምጣኔ ሐብት ምን ይዞ ይመጣል? ደሐውን የማኅበረሰብ ክፍል ከዳፋው እንዴት መታደግ ይቻላል?
17-7-2022 • 39 minuten, 48 seconden እንወያይ፦ የነዳጅ ድጎማ ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብት ምን ይዞ ይመጣል?
17-7-2022 • 39 minuten, 48 seconden መንግሥት ጭፍጨፋውን ማስቆም ለምን ተሳነው?
በኢትዮጵያ በተለይ ባለፉት አራት ዓመታት እዚህም እዚያም ኼድ መለስ ይል የነበረው ብሔርን መሰረት ያደረገ ግድያ እና ጭፍጨፋ ከሰሞኑ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱ ብርቱ ቁጣ ቀስቅሷል። ባለፉት ቀናት ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ውስጥ በአብዛኛው የአማራ ብሔር ተወላጆች በተከታታይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋል። ሙሉ ውይይቱ በድምፅ ከታች ይገኛል።
10-7-2022 • 39 minuten, 47 seconden ዳግም ሞት፤ ዳግም ሐዘን እንዳይከሰትስ ምን ይደረግ?
10-7-2022 • 39 minuten, 47 seconden «በብሔር ተኮሩ ግድያ እንድንፈራና እና እንድንባንን እየተደረግን ነዉ»
3-7-2022 • 41 minuten, 20 seconden 19-6-2022 • 39 minuten, 58 seconden እንወያይ፦ የኢትዮጵያ መንግሥትንና ህወሓትን የማሸማገል ጥረት
12-6-2022 • 31 minuten, 15 seconden እንወያይ፦ የጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እስር በኢትዮጵያ
5-6-2022 • 30 minuten, 56 seconden