ማሕደረ ዜና፣ የመካከለኛዉ ምሥራቅ እልቂትና የአሜሪካኖች ተቃራኒ መርሕ
10/21/2024 • 15 minutes, 14 seconds አንድ ዓመት የሞላው የሃማስ ጥቃት ቀጣናውን ወደ ቀውስ እየመራው ይሆን ?
10/8/2024 • 14 minutes, 11 seconds ሃማስ እስራኤልን ያጠቃበት ጥር 7 ፤ 2023 ሲታወስ
ጋዛ እንዳልነበረች ሆናለች ፤ ሊባኖስ የጋዛ መንገድ የተከተለች መስሏል ፤ ሞት እና ውድመት እዚህም እዚያም ይሰማል ፤ ከኢራን እና ከምትደግፋቸው ታጣቂዎች ከኋላ እና ከፊት የሚሳኤል እና የሮኬት ዝናብ የሚዘንብባት እስራኤል በቆሰለች ቁጥር ቁጣዋ እያየለ የምትወስደው እርምጃም ሰላማዊን ከጦረኛ ሳይለይ እንዳነፈረ እነሆ አንድ ዓመት ደፈነ ።
10/7/2024 • 14 minutes, 11 seconds ማሕደረ ዜና፣ መካከለኛዉ ምሥራቅ ደም ጠጥቶ ደም የሚጠማዉ ምድር
የአረብ መሪዎች ይርመጠመጣሉ፣ ኢራን ትፎክራለች።ሐማስ ይሽሎኮሎካል፣ ሒዝቡላሕና ሑቲዎች ይፍጨረጨራሉ።ፍልስጤም ያልቃል።እስራኤል፣ ጠቅላይ ሚንስትር ኔታንያሁ እንዳሉት በረጅም ምህረት የለሽ እጇ፣ ሲሻት ጋዛን፣ ሲያሰኛት ምዕራባዊ ዮርዳኖስ ወንዝ ዳርቻን፣ ሲፈልጋት ሊባኖስን፣ ካሰኛት ሁዴይዳሕን፣ ቴሕራንን፣ ደማስቆን ታጋያለች
9/30/2024 • 14 minutes, 10 seconds ማሕደረ ዜና፣ መካከለኛዉ ምሥራቅ ደም ጠጥቶ ደም የሚጠማዉ ምድር
9/30/2024 • 14 minutes, 10 seconds ማሕደረ ዜና፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት መርሕና 79ኛዉ ጉባኤ
9/23/2024 • 13 minutes, 14 seconds አዲሱ የኢትዮጵያዉያን ዓመት በተስፋ እና ስጋት መካከል
9/16/2024 • 12 minutes, 15 seconds አዲሱ ዓመት ለኢትዮጵያዉያን ምን ይዞላቸው መጣ? ተስፋ ወይስ የቀጠለ ስጋት ?
ኢትዮጵያ ከተቀረው ዓለም ሰባት ዓመታት ከመንፈቅ ገደማ ወደ ኋላ የምትቀርበት የዘመን ቀመር 2017 ላይ ደርሶ እነሆ 2016 አሮጌ ሆኖ ለአዲሱ ዓመት ተሸጋገረች ። በእርስ በርስ ግጭት ጦርነት ውስጥ ያለችው ሀገር ከአንዱ የግጭት ጦርነት ምዕራፍ ወደ ሌላው እየተሸጋገረች ዓመታቱም ሂያጁ ለመጪው እየለቀቁ ቀጥለዋል።
9/16/2024 • 12 minutes, 15 seconds ቃለ መጠይቅ፣ የሶማሊያና የግብፅ ወታደራዊ ዝግጅት ያስከተለዉ ሥጋት
ግብፅ ከዚሕ በተጨማሪ በመጪዉ ታሕሳስ ባዲስ መልክ ይዋቀራል ለተባለዉ በሶማሊያ የአፍሪቃ ሕብረት ሠራዊት 5000፣ ለሶማሊያ መንግሥት በቀጥታ ድጋፍ የሚሰጥ ሌላ 5000 ጦር ኃይል ሶማሊያ ዉስጥ ለማስፈር ማቀዷም በሰፊዉ እየተነገረ ነዉ።የሶማሊያና የግብፅ ጦር ኃይላት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ ለማድረግ እየተዘጋጁ መሆናቸዉም ተነግሯል
9/4/2024 • 18 minutes, 5 seconds ማሕደረ ዜና፣ የአፍሪቃ ቀንድ የጦርነት ሥጋት
9/2/2024 • 13 minutes, 21 seconds ማሕደረ ዜና፣ የመካከለኛዉ ምሥራቅ ምሥቅልቅል፣ የአሜሪካ ተቃራኒ አቋም
8/26/2024 • 13 minutes, 27 seconds የህወሓት ጠቅላላ ጉባኤ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንትን ከምክትል ሊቀመንበርነት አሰናብቶ ተጠቀቀ-ከዚያስ?
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ አመራሮቹን ለውዝግብ የዳረገውን ጉባኤ ሲያጠናቀቅ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በሊቀ-መንበርነታቸው ቀጥለዋል። አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊቀ-መንበር ሆነው አቶ ጌታቸው ረዳን ተክተዋል። ለህወሓት አዲስ የሥራ አስፈፃሚ፣ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እና ቁጥጥር ኮሚሽን የተመረጠበት ጉባኤም ይሁን ውጤቱ ግን በምርጫ ቦርድ እውቅና አልተሰጠውም። በህወሓት መሪዎች መካከል የተፈጠረው ልዩነት የፖለቲካ መሪዎች እና ነዋሪዎችን አስግቷቸዋል።
8/19/2024 • 13 minutes, 28 seconds የህወሓት አመራሮች ክፍፍል እና ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር የተፈጠረ ውዝግብ ሥጋት ፈጥሯል
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ አመራሮቹን ለውዝግብ የዳረገውን ጉባኤ ሲያጠናቀቅ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በሊቀ-መንበርነታቸው ቀጥለዋል። አቶ አማኑኤል አሰፋ ምክትል ሊቀ-መንበር ሆነው አቶ ጌታቸው ረዳን ተክተዋል። ጉባኤውም ይሁን ውጤቱ ግን በምርጫ ቦርድ እውቅና አልተሰጠውም። የፖለቲካ መሪዎችና ነዋሪዎች የተፈጠረው ውዝግብ አስግቷቸዋል።
8/19/2024 • 2 minutes, 6 seconds የመካከለኛው ምስራቅ ቀውስ ፤ የኃያላን መንግስታት ተሳትፎ ውጥረት እና የኢትዮጵያዉያን ስጋት
8/13/2024 • 13 minutes, 16 seconds መካከለኛው ምስራቅ አዲሱ የጦር አውድማ ወይስ ?
በኢራን የስለላ እና የደህንነት ተቋማቶቿ ብቃት ላይ ጥያቄ ያስነሳው ሁነቱ የእስራኤል ሰላዮች ኢራን ውስጥ እንደልባቸው እየተዘዋወሩ «የልባቸውን እያደረሱ ነው » ሲያስብላቸው ፤ በአንጻሩ ኢራን ያላት ብቸኛ መልስ ብቀላ ብቻ መሆኑን በይፋ አስታውቃለች።
8/12/2024 • 13 minutes, 16 seconds ማሕደረ ዜና፦ የጎፋ ሕዝብ ለቅሶ የኢትዮጵያ ሐዘን
በጎፋ ዞን በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የኢትዮጵያ መንግሥት 231 የአካባቢው ነዋሪዎች 260 ሰዎች እንደሞቱ ይገልጻሉ። በርካቶች የሟቾች ትክክለኛ ቁጥር ተድበስብሷል የሚል ሥጋት አላቸው። አደጋው “ማምረት የሚችሉትን” ሕይወት ነጥቆ ሕጻናት እና አቅመ ደካሞችን ያለ ረዳት ያስቀረ ነው። አ ስከሬን ፈልጎ ማንነቱን መለየት ለቤተሰብ ማስረከብ በአካባቢው ነዋሪዎች ጫንቃ ወድቋል።
7/29/2024 • 12 minutes, 32 seconds