የጥቅምት 14 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
24/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos ዶይቼ ቬለ የዕለቱን ዋና ዋና የዜና ትንታኔዎች ከኢትዮጵያ እና ከመላው ዓለም በየቀኑ ያቀርባል። የኢትዮጵያ እና የአፍሪካ ፖለቲካዊ እና ኤኮኖሚያዊ ጉዳዮችን ጨምሮ የመላው ዓለምን ውሎ የተመለከቱ ጠቃሚ መረጃዎች በሰባቱም የሣምንቱ ቀናት ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከዶይቼ ቬለ ያድምጡ።
የዶይቼ ቬለን ዜናዎች በዩቲዩብ፣ በአፕል ፖድካስት፣ በስፖቲፋይ እና በየትኛውም የፖድካስት ምርጫዎን በምታገኙባቸው መንገዶች ማድመጥ ትችላላችሁ። የዶይቼ ቬለ ዜና በራዲዮ፣ በሳተላ ይት እና በፌስቡክ በየዕለቱ በቀጥታ ይደመጣል።
አስገድዶ መሰወር፣ እገታ እና እየደረሰ ያለው ቀውስ
የእስራኤል ድሮኖች በታሪካዊት ከተማ ያካሄዱት ድብደባ
ሩስያና ኒኩለር ጦር መሳሪያ የመጠቀም ስጋት
የብሪክስ መድረክ የአዳጊ አገራት ድምጽና ፍላጎት ማንጸባረቂያ እንዲሆን ተጠየቀ
23/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የነአቶ ዮሃንስ ቧያሌው የፍርድቤት ውሎ
እስራኤል የሒዝቦላህ የፋይናንስ ተቋማትን በአየር ማውደሟን
የእስራኤል የመከላከያ ሰራዊት ሊባኖስን ይቅርታ ጠየቀ።
አሜሪካ ለዩክሬይን የ400 ሚልዮን ዶላር ወታደራዊ ድጋፍ እንደምትሰጥ ይፋ አደረገች።
23/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የጥቅምት 12 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
ትናንት ማምሻውን በአዲስ አበባ መርካቶ የተነሳውና ለረዥም ሰዓት የቆየው የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ሳያደርስ እንዳልቀረ እየተነገረ ነው። እሳቱ እስከ ዛሬ ማለዳ ድረስ ሙሉ ለሙሉ በቁጥጥር ሥር አልዋለም ነበር። መስኤውም እልታወቀም።
ከአንድ ወር በላይ ተዘግቶ የቆየው የኢትዮ ሱዳን ደንበር ከትናንት አንስቶ ጀምሮ እንደገና ተከፍቶ አገልግሎት መጀመሩን የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር አስታወቀ።
የሱዳን ጦር ባካሄደው የአየር ጥቃት ቢያንስ 31 ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው የመብት ተሟጋቾች አስታወቁ።
የአውሮጳ ዓርላማ ከታገደው የሩሲያ ንብረት ላይ ለዩክሬን 35 ቢሊየን ዩሮ ብድር አጸደቀ።
22/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos በጫሞ ሐይቅ ላይ በደረሰው የጀልባ መስጠም አደጋ እስከአሁን 12 አስከሬን መገኘቱን
እስራኤል 3 የሒዝቦላህ ከፍተኛ አመራሮች ገደልኩ አለች
በጋዛ እስራኤል በፈጸመችው ጥቃት 87 ፍልስጤማውያን ተገደሉ
ሾልኮ የወጣው ሚስጢራዊ ሰነድ
20/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የጥቅምት 9 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
19/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos -የቀድሞዉ የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ የሠላም ሚንስትር ደኤታና የኦሮሚያ ምክር ቤት እንደራሴ ታዬ ደንደዓ ሕገ ወጥ የጦር መሳሪያ ታጥቃዋል በሚል መከሰሳቸዉን ዉድቅ አደረ ጉት።ከአምና ታሕሳስ ጀምሮ ከሥልጣን ተነስተዉ የታሰሩት አቶ ታዬ ጦር መሳሪ መታጠቃቸዉን አልካዱም።መከሰሳቸዉን ግን አልተቀበሉትም።-----የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝደንት ጆ ባይደን የጀርመን ፌደራል ሪፐብሊክን ከፍተኛ ኒሻን ዛሬ ተሸለሙ።-የእስራኤል ጦር የሐማስን መሪ ያሕያ ሲንዋርን መግደሉን የፍልስጤሙ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን አመነ።
18/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የሐሙስ፤ ጥቅምት 7 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
17/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos በአማራ ክልል የሚዋጉት የኢትዮጵያ መንግሥት ጦርና የፋ ኖ ታጣቂዎች ለሰላማዊ ሰዎችና ተቋማት ጥበቃና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ የክልሉ ዩኒቨርስቲዎች መድረክ ወይም ፎረም ጠየቀ።----የኬንያ ሕግ መወሰኛ ምክር ቤት (ሴኔት) የሐገሪቱ ምክትል ፕሬዝደንት ሪጋዚ ጋሻጉዋ ሥልጣን መልቀቅ አለባቸዉ-የለባቸዉም በሚለዉ ሐሳብ ላይ መከራከር ጀመረ።ምክትል ፕሬዝደንቱ የተያዘባቸዉን የወንጀል ጭብጥ በሙሉ ፖለቲካዊ በማለት ክደዋል።-የኢራንና የእስራኤል ባለሥልጣናት አሁንም እየተዛዛቱ ነዉ።ሊባኖስና ጋዛ ዛሬም ይወድማሉ።ዩናይትድ ስቴትስና ጀርመን ለእስራኤል ጦር መሳሪያ ማስታጠቃቸዉን ቀጥለዋል።
16/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos 15/10/2024 • 0 minutos, 1 segundo የጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
14/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos 13/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የጥቅምት 2 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
12/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የጥ ቅምት 1 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
የመስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የሶማሊያና የግብጽ ፕሬዝደንቶች በኤርትራ ይፋዊ ጉብኝት በማድረግ ላይ ናቸው። የሁለት ሃገራት መሪዎች ከኤርትራው ፕሬዝደንት ጋር በሁለትዮሽ፤ በአፍሪቃ ቀንድና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተገልጿል።
የተመድ በመላው ዓለም ወጣቶች ለዘርፈ ብዙ ጥቃቶች መጋለጣቸውን አመለከተ። የተመድ ታይቶ ለማ ይታወቅ የጥቃት ማዕበል እና ጦርነት ባመጣው ጾታዊ ጥቃት እንዲሁም የአየር ንብረት ለውጥ፤ ረሃብና መፈናቀል ተጋልጠዋል።
ግብጽ በሱዳን ጦርነት በአየር ድብደባ ተሳትፋለች በሚል ከፈጥኖ ደራሹ ኃይል መሪ የቀረበባትን ክስ አስተባበለች።
የጎርጎሪዮሳዊው ዓመት 2024 የስነጽሑፍ የኖቤል ሽልማት ለደቡብ ኮርያዋ ደራሲ ሃን ካን ተሰጠ።
10/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የረቡዕ መስከረም 29 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
9/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የመስከረም 28 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
8/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የመስከረም 27 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
7/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የመስከረም 26 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
6/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የመስከረም 25 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
5/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የመስከረም 24 ቀን 2017 የዓለም ዜና
4/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የመስከረም 23 ቀን 2017 የዓለም ዜና
3/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos -የኢትዮጵያ መንግሥት የአማራ ክልል ነዋሪዎችን በጅምላና በዘፈቀደ ማሰሩ የ ሕግ የበላይነትን ይበልጥ መሸርሸሩን አምንስቲ ኢንተርናሽናል አስታወቀ።---የእስራኤልና የሊባኖስ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን ሒዝቡላሕ ደቡባዊ ሊባኖስ ዉስጥ በቅርብ ርቀት እየተዋጉ ነዉ።----በወርሮበሎች ጥቃትና አመፅ በተመሰቃቀለችዉ ሐይቲ ከ7 መቶ ሺሕ በላይ ሕዝብ ከቤት ንብረቱ መፈናቀሉ ተነገረ።የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እንደሚለዉ ካረቢያይቱ ሐገርን ከጥፋት ለማደን ዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ አበክሮ መጣር አለበት።የዜናዉ መልዕክት የእስካሁኑ ነበር
2/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የማክሰኞ መስከረም 21 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
1/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የመስከረም 20 ቀን 2017 የዓለም ዜና
የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች በኻርቱም የሚገኝ የአምባሳደሯ መኖሪያ ቤት በወታደራዊ አውሮፕላን ተደብድቧል በሚል ያቀረበችውን ክስ የሱዳን ጦር አስተባበለ። በደቡብ አፍሪካ ምሥራቅ ኬፕ ክፍለ ግዛት በተፈጸመ ጥቃት የተገደሉ ሰዎች ቁጥር ወደ 18 አሻቀበ። ርዋንዳ ኃይለኛ ተላላፊ በሆነው ኢቦላ መሰል የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝ ስምንት ሰዎች መሞታቸውን አስታወቀች። እስራኤል ሊባኖስን በእግረኛ ወታደሮች ከወረረች ሒዝቦላሕ ለውጊያ ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ። የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር ዮቭ ጋላንት ሀገራቸው እግረኛ ወታደሮቿን ወደ ሊባኖስ ልታዘምት እንደምትችል ፍንጭ ሰጥተዋል። ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ ኢራንን አስጠንቅቀዋል
30/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የመስከረም 19 ቀን 2017 የዓለም ዜና
29/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የመስከረም 18 ቀን 2017 የዓለም ዜና
ጠቅላይ ሚኒስትር ሐምዛ አብዲ ባሬ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ የተፈራረመችው የመግባቢያ ሥምምነት የሶማሊያን የግዛት አንድነት ይጥሳል ሲሉ ከሰሱ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ታዬ አጽቀ ሥላሴ የሀገራቸው “ዓላማ በቀጠናው የጋራ ዕድገት እና ብልጽግና መፍጠር” እንደሆነ ተናግረዋል። ኢትዮጵያ እና የአይኤምኤፍ ባለሙያዎች በተራዘመ የብድር አቅርቦት የመጀመሪያ ግምገማ ተስማሙ። የሱዳን ፈጥኖ ደራሽ ኃይል በዳርፉር ግዛት በምትገኘው አል-ፋሽር ለሁለት ቀናት በፈጸመው ጥቃት 48 ሰዎች ተገደሉ። የሊባኖሱ ሒዝቦላሕ መሪው ሐሳን ናስረላሕ እስራኤል በፈጸመችው የአየር ጥቃት መገደላቸውን አረጋገጠ።
28/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የዐርብ መስከረም 17 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
27/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የመስከረም 16 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
DW Amharic-የዛሬው የዓለም ዜና በኢትዮጵያ የጋዜጠኞች እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች እስር እና ወከባ እየጨመረ መጥቷል መባሉ፤በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን የመስቀል ደመራ በዓል በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ መከበሩ፤የሱዳን ጦር በዋና ከተማይቱ ካርቱም የመድፍ እና የአየር ድብደባ መጀመሩ ፤ደቡብ አፍሪቃ በፀረ አፓርታይድ ትግሉ ወቅት በስደት ሆነው ህይወታቸውን ያጡ ዜጎቿን አስከሬን ወደ ሀገር መመለሷ፤የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የተኩስ አቁም ስምምነት ሀሳብን ውድቅ ማድረጋቸው እና ሩሲያ የምዕራቡን ዓለም ለመገዳደር አዲስ የኒዩክሌር ጦር መሳሪያ አጠቃቀም ሰነድ ማውጣቷን ያስቃኛል።
26/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos ደቡብ ኢትዮጵያና ጋምቤላ ክልሎች በደረሱ የመኪና አደጋዎች 35 ሰዎች ሞቱ።ናይሮቢ-የኬንያ እናቶች ጥሪ፣ የአምንስቲ ጥያቄ።አቡጃ-በኢትዮጵያ በኩል ያለፈ አደንዛዥ ዕፅ ሌጎስ ላይ ተያዘ።ቫቲካን-የእስራኤል-ሒዝቡላሕ ዉጊያና የርዕሠ ጳጳሱ ተማፅዕኖ።ኒዮርክ-የዓለም መሪዎች ጥሪና የእስራኤል ሊባኖስ ዉጊያ
25/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የማክሰኞ መስከረም 14 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
24/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የዓለም ዜና፤ መስከረም 13 ቀን 2017 ዓ.ም ሰኞ
--ሶማሊያ ከግብፅ ከፍተኛ መጠን ያለዉ የጦር መሳሪያን ለሁለተኛ ጊዜ ተረከበች። ግብፅ ዜጎችዋ በቶሎ ከሶማሌላንድ እንዲወጡም ጠይቃለች።--ፓኪስ ታን ዉስጥ የኢትዮጵያንና የሩስያ ዲፕሎማቶችን ጨምሮ የተለያዩ ሃገራት ልዑኮች ከጥቃት መትረፋቸዉ ተመለከተ።--ሱዳን ባለፈው ነሐሴ ወር ብቻ በኮሌራ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ወደ 388 ከፍ ማለቱ ተነገረ። በወረርሽኙ ወደ 13,000 ሰዎች ተይዘዋል።--እስራኤል በሊባኖስ እያካሄደች ያለዉ ጥቃት 'አደገኛ መዘዝ' ያስከትላል ስትል ኢራን አስጠነቀቀች። በእስራኤል እና በሂዝቦላ ሚሊሻ መካከል እየጠነከረ የመጣው ዉጥረት ፤ በመካከለኛው ምስራቅ የሚታየዉን ቀዉስ እንዳያሰፋ ስጋት አሳድሯል።
23/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos 22/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የመስከረም 11 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
21/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos -የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በቅርቡ ያደረገዉ ጉባኤ፣ ዉሳኔዎቹና የባንክ ሒሳቡ በፍርድ ቤት ታገደ።-የእስራኤልና የሊባኖስ ደፈጣ ተዋጊ ቡድን የሒዝቦላሕ ዉጊያ ዛሬ አይሎ ዉሏል።ሒዝቡላሕ ሰሜን እስራኤልን በሚሳዬል፣ እስራኤል ባንፃሩ የሊባኖስ ርዕሰ ከተማ ቤይሩትን በጦር ጄቶች ደብድበዋል።-የአዉሮጳ ሕብረት ለዩክሬን 35 ቢሊዮን ዩሮ ብድር ሰጠ።
20/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የሐሙስ መስከረም 9 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
የመስከረም 8 ቀን 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
በደቡብ ምዕራብ ዳርፉር ውስጥ የሱዳን ጦር ባካሄደው የአየር ጥቃት ከ40 በላይ ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። ዩናይትድ ስቴትስ የሱዳን ተቀናቃኝ ኃይሎች በአስቸኳይ ለውይይትም እንዲቀመጡ ጠይቃለች።
የዩናይትድ ስቴትስ ሰው አልባ አውሮፕላን የመን አቅራቢያ መከስከሱን ፔንታገን አረጋገጠ። የየመን ሁቲ ሚሊሺያዎች ባለፉት ቀናት በርካታ አውሮፕላኖችን መትተው መጣላቸውን አስታውቀው ነበር።
ሊባኖስ ውስጥ በድምፅና መልእክት መቀበያ መሣሪያ ፍንዳታ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ማሻቀቡ እየተነገረ ነው።
ማዕከላዊ አውሮጳን ከሁለት አስርት ዓመታት ወዲህ ያጥለቀለቀው አስከፊ የጎርፍ አደጋ ከሮማንያ እስከ ፖላንድ ከባድ ውድመት አስከትሏል።
18/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የዓለም ዜና፤ መስከረም 7 ቀን፤ 2017 ዓ.ም ሰኞ
DW Amharic የካይሮ መንግሥት ህወሓት እና ኤርትራን ማደራደር እንደሚፈልግ ተመለከተ። ግብፅና ኤርትራ ትስስራቸዉን ለማጠናከር ወታደራዊ ትብብር እና የመረጃ ልውውጥ ስምምነት ሊፈፅሙ እንደሚችል የግብፅ የዜና ምንጮች ዘገቡ። በጎንደር ከተማ ዛሬ ከማለዳ ጀምሮ በፋኖና በመንግስት ወታደሮች መካከል ውጊያ ሲካሄድ መዋሉን ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል ቱርክ አንካራ ላይ ሊደረግ የታቀደው ሦስተኛ ዙር ዉይይት ለሌላ ጊዜ መተላለፉን የሶማልያ ከፍተኛ ባለስልጣናት ተናገሩ። ደቡብ ሱዳን በጎረቤቷ ሱዳን በኩል ወደ ውጭ ሃገር የነዳጅ ምርትን ለመላክ እና እንደገና ለማስጀመር እየሰራች መሆኑ ተነገረ።
17/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos DW Amharic የመስከረም 6 ቀን 2017 የዓለም ዜና
አዲሱ የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 16 የቀድሞ ከፍተኛ አመራሮች ከፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ማገዱ አስታወቀ። የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ብልጽግና ፓርቲ አባላቱን ሲያሰለጥን እንዳለፈው ዓመት “ከመንግሥት ካዝና ገንዘብ አውጥቶ” እየከፈለ ነው ሲል የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትሕ (ኢዜማ) ወነጀለ።የኬንያ ዋና ኦዲተር ሀገሪቱ ከተለያዩ ወገኖች የተበደረችውን ዕዳ ኦዲት ማድረግ መጀመሩን የፋይናንስ ሚኒስትሩ ተናገሩ። በምዕራብ እና ማዕከላዊ አፍሪካ በጣለ ከባድ ዝናብ እና ባስከተለው ጎርፍ ምክንያት ከ500 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ የተመ አስታወቀ።
16/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos 15/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የመስከረም 4 ቀን 2017 ዓ/ም የዓለም ዜና
14/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የዓርብ መስከረም 3 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
DW Amharic-በኮሬ ዞን በእገታ ላይ የነበሩ አራት አርሶ አደሮች መገደላቸው፤በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን አንድ ድልድይ በመደርመሱ፤ ዞኑን ከአጎራባች አካባቢዎች ጋር የሚያገናኝ መንገድ አገልግሎት እንደማይሰጥ መገለፁ፤የሴኔጋሉ ፕሬዝዳንት የሀገራቸውን ፓርላማ መበተናቸው፤መካከለኛው አውሮፓ በመጭው ቅዳሜና እሁድ በሚጥለው ከባድ ዝናብ ለከፍተኛ የጎርፍ ይጋለጣል መባሉ፤የሰሜን ኮሪያው መሪ ለመጀመሪያ ጊዜ በይፋ የኒውክሌር ማብላያ እና የዩራኒየም ማበልፀጊያ ቦታዎችን መጎብኘታቸው፤ዶናልድ ትራምፕ ከተፎካካሪያቸው ካማላ ሀርስ ጋር ሌላ የምርጫ ክርክር እንደማያደርጉ ማስታወቃቸው የዛሬው የዓለም ዜና ያካተታቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።
13/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የመስከረም 2 ቀን ፣ 2017 ዓ.ም.የዓለም ዜና
የሐሙስ መስከረም 2 ቀን 2017 ዓም አርዕስተ ዜና
የተባበሩት መንግሥታት የትምሕርት የሳይንስና የባህል ድርጅት በምህጻሩ ዩኔስኮ ዩኔስኮ የሱዳን ብሔራዊ ቤተ መዘክርን ጨምሮ በሌሎች የሱዳን ቤተ መዘክሮች እና የቅርስ ተቋማት ላይ ተፈጽመዋል የሚባሉ ዝርፊያዎችና ጉዳቶች በእጅጉ አሳስቦኛል አለ።
ስዊድን ወደ ሀገራቸው በፈቃደኝነት ለሚመለሱ ስደተኞች እስከ 34 ሺህ ዶላር እንደምትከፍል አስታወቀች።
በደቡብ ምዕራብ እስያን የመታው ያጊ የተባለው ወጀብ ያስከተለው ጎርፍ የገደለው ሰው ቁጥር ከ250 በለጠ።
12/9/2024 • 0 minutos, 1 segundo የረቡዕ መስከረም 1 ቀን፣ 2017 ዓ.ም የዓለም ዜና
11/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የጳጉሜ 5 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
10/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
በኦሮሚያ ክልል ቄለም ወለጋ ዞን ጅማ ሆሮ ወረዳ ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መናድ የሦስት ሰዎች ሕይወት አለፈ። በንብረት ላይም ከፍተኛ ውድመት ደ ረሰ።
በዘንድሮው የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ያለፉት ተማሪዎች ብዛት ከአምናው እንደሚሻል ተገለጸ። እንዲያም ሆኖ ከ1,363 ት/ቤቶች ምንም ተማሪዎች እንዳላለፉ የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ አስታውቋል።
ሰሜን ናይጀሪያ ውስጥ የነዳጅ ቦቴ ሰዎች ካሳፈረ ትልቅ መኪና ጋር ተጋጭቶ በተፈጠረ ፍንዳታ ቢያንስ 52 ሰዎች ሞቱ።
ምዕራባዊ ሶርያ ውስጥ እስራኤል ባደረሰችው የአየር ጥቃት 16 ሰዎች ሲገደሉ፤ በርካቶች መጎዳታቸው ተነገረ። ኢራን ጥቃቱን አውግዛለች።
9/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos 8/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የጳጉሜ 2 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
Dw Amharic-በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረቆ ልዩ ወረዳ ዛሬ እኩለ ቀን አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ህይወት ማለፉ፣በአማራ ክልል ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል በተባሉ 7ሺህ የሚጠጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መውሰዱ፣ አርብ ዕለት በዌስት ባንክ የተገደለችው ቱርካዊ-አሜሪካዊት ወጣት ግድያ በገለልተኛ ወገን እንዲጣራ መጠየቁ፣ሩሲያ በአሜሪካ መገናኛ ብዙሃን ላይ ገደብ እንደምትጥል መግለጿ እንዲሁም የዶናልድ ትራምፕ ክስ የሀገሪቱ ምርጫ እስኪጠናቀቅ ድረስ ብይኑ እንዲዘገይ መወሰኑን የዛሬው የዓለም ዜና የያዛቸው ርዕሰ ጉዳዮች ናቸው።
7/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የዓርብ ጳጉሜ 1 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
DW Amharic - በእስር ላይ የነበሩ ሰባት የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ ባለስልጣናት ከእስር መለቀቃቸው- በኢትዮጵያ በመጭው አዲስ ዓመት ሰላም እንዲሰፍን፣ ፍትሕና ተጠያቂነት እንዲረጋገጥ መጠየቁ -የሱዳን ጦር ከፋኖ ታጣቂዎች ሸሽተው ወደ ሱዳን የገቡ 77 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ትጥቅ ማስፈታቱን--በኬንያ በአንድ አዳሪ ትምህርት ቤት ውስጥ በደረሰ የእሳት አደጋ 17 ተማሪዎች መሞታቸውን- በሱዳን እርስ በእርስ የሚዋጉት ሁለቱም ኃይሎች የጦር ወንጀል ሊባል የሚችል ጥቃት ፈጽመዋል መባላቸው -በደቡብ ሱዳን ከ700 ሺህ በላይ ሕዝብ በጎርፍ መጎዳቱን የተሰኙ ርዕሰ ጉዳዮችን የዛሬው የዓለም ዜና አካቷል።
6/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የነሐሴ 30 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
በ ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ ጋብ ብሎ የነበረው ውጊያ ማገርሸቱን ነዋሪዎች ለዶቼ ቬለ ተናገሩ። ለቀናት ተኩስ እንዳልነበረ የገለጹት እማኞች ዛሬ ከቀትር በኋላ ከ11 ሰዓት ጀምሮ በከተማዋ የተለያየ አካባቢ ተኩስ መከፈቱን አመልክተዋል።
ቻይና በቀጣይ ሦስት ዓመታት ለአፍሪቃ ሃገራት ከ50 ቢሊየን ዶላር በላይ የገንዘብ ድጋፍ ለማድረግ መዘጋጀቷን አስታወቀች።
ከሱዳን ተፈናቅለው በኢትዮጵያ ተጠግተው ከነበሩ ስደተኞች 700 የሚሆኑት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸው ተነገረ።
በጀመርኗ ሙኒክ ከተማ በዛሬው ዕለት ፖሊስ አንድ ተጠርጣሪን ተኩሶ መግደሉ ተነገረ።
5/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን፤ 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
4/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos -የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደና ከ-ኤርትራ የሚያደርገዉን በረራ አቋረጠ።የአየር መንገዱ የበላይ ኃላፊ እንዳሉት አየር መንገዳቸዉ በረራዉን ያቋረጠዉ ኤርትራ ባንክ የሚገኝ ገንዘቡ በመታገዱ ነዉ።የዉጪ ዲፕሎማቶች እንደሚሉት ግን አየር መንገዱ በረራዉን ያቋረጠዉ የአዲስ አበባና የአስመራ ግንኙነት ሲበዛ በመሻከሩ ነዉ።----የኢትዮጵያ መንግስት የሰዎችን መታገትና የሚደርስባቸዉን የመብት ጥሰት ለማስቆም ሁነኛ እርምጃ እንዲወስድ የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በድጋሚ ጠየቀ።-60 ከመቶ የሚሆኑ የአፍሪቃ ወጣቶች ከየሐገራቸዉ መሰደድ እንደሚፈልጉ አንድ ጥናት አረጋገጠ።
3/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
የፋኖ ታጣቂዎች ዛሬ የጠረፍ ከተማ የሆነችው መተማ ከተማን ተቆጣጥረው መዋላቸውን የከተማዋ ናዋሪዎች ለዶይቼ ቬሌ ገለጹ።
የጀርመን ቀኝ ጽንፈኛ ፓርቲ በሁለት ፌደራል ግዛቶች በተካሄደው ምርጫ ያገኘው ስኬት በመራሄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ አስተዳደር ላይ ጫና ማስከተሉ እየተነገረ ነው።
ሩሲያ በዛሬው ዕለት የተጠናከረ የሚሳኤል ጥቃት በዩክሬን ዋና ከተማ ኪየቭና በሌሎች የሀገሪቱ ከተሞች ላይ ከፈተች።
በፓሪስ 2024 ፓራለምፒክ የሚሳተፉ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል እያስመዘገቡ ነው።
2/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የነሐሴ 26 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
1/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የነሐሴ 25 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
*ኢትዮጵያ ፦ በአማራ ክልል ከፍተኛ ዝናብ ያስከተለው ጥፋት
*ኬንያ፣ ከፍተኛ የኃይል መቆራረጥ ገጠማት
*ቱኒዝያ፣ አደጋ ላይ የነበሩ 28 ስደተኞች ተረፉ
*ጀርመን፤ ስድስት ሰዎች በስለት ተወግተው ቆሰሉ
*እስራኤል፤ በጄኒን የሚካሄደው ከባድ ውጊያ ቀጥሏል
*ኢትዮጵያ ፤ በዓለም ከ20 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና 2ኛ ደረጃ ላይ
31/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የነሐሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረቆ ልዩ ወረዳ ማንነትን መሠረት ያደረገ ነው በተባለ ጥቃት አራት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ሰባት ሰዎች መገደላቸው ተሰማ።
ኢትዮጵያ ሶማሊላንድ ውስጥ ለሚገኘው ቆንስላ ጽሕፈት ቤቷ አዲስ አምባሳደር ሾመች።
የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት የኢትዮጵያን የዘመን መለወጫ በዓል ምክንያት በማድረግ ከ3,600 በላይ የሕግ ታራሚዎችን በይቅርታ መልቀቁን አስታወቀ። ከታሰሩ የኦነግ አባላት የተለቀቀ የለም።
የቀድሞው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝደንት ፕሮፌሰር እንድርያስ እሸቴ ባደረባቸው ህመም በህክምና ሲረዱ ቆይተው ትናንት ሐሙስ ነሐሴ 23 ቀን፣ 2016 ዓ.ም ማረፋቸውን ዩኒቨርስቲው አስታወቀ።
30/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 23 ቀን፤ 2016 ዓ.ም ሐሙስ
አርስተ ዜና፤
--የአውሮጻ ህብረት የውጭ ጉዳይ ሃላፊ ጆሴፍ ቦሬል በእስራኤል ሚኒስትሮች ላይ ማዕቀብ እንዲጣል ሃሳብ ለማቅረብ እየሰሩ እንደሆነ ተመለከተ።
--በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ስልጢ ዞን ጎርፍ ከ6ሺህ በላይ ነዋሪዎችን አፈናቀለ። የጎርፍ አደጋው መንሥኤ በአካባቢው ከተገነባ የመስኖ ግድብ ነዉ ተብሏል። በሌላ በኩል በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በናዳ ለተጎዱ እርዳታ እየተጠበቀ ነዉ። --ዓለም አቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅት «ሂውማን ራይትስ ዋች» በሱዳን ከ16 ወራት በላይ በዘለቀዉ የእርስ በእርስ ግጭት፤ ሁለቱንም ተፋላሚ ወገኖች ፤ የጦርነት ወንጀል ፈፅመዋል ሲል ከሰሰ።
29/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos -የኢትዮጵያ መንግሥትን በነፍጥ የሚወ ጉ ኃይላት በሐገሪቱ ብሔራዊ የምክክር ሒደት እንዲካፈሉ ለተደረገላቸዉ ጥሪ መልስ አለመስጠታቸዉን የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።ለታጣቂዎቹ ኃይላት ጥሪዉ የተደረገበትን መንገድና ጥሪዉ ሥለመድረስ አለመድረሱ ግን የኮሚሽኑ ባለሥልጣናት አልጠቀሱም።-----ግብፅ ለሶማሊያ የጦር መሳሪያ ማስታጠቅ ጀመረች።መሳሪያ የጫኑ ሁለት የግብፅ የጦር አዉሮፕላኖች ትናንት ሞቃዲሾ ማረፋቸዉን ዲፕላቶች አስታዉቀዋል።ኢትዮጵያ ከሶማሊላንድ ጋር ወደብ ለመኮናተር ከተስማማች ወዲሕ የሞቃዲሾና የካይሮ ፍቅር ፀጥንቷል
28/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የነሐሴ 21 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
ዓርስተ ዜና
--የእስራኤል ልዩ ኃይል እጅግ በጣም ውስብስብ ባለው ልዩ ዘመቻ ደቡባዊ ጋዛ ውስጥ ከሚገኝ የሃማስ ዋሻ ውስጥ አንድ ታጋች ማስለቀቁን ዛሬ አስታወቀ። የ52 ዓመቱ ታጋች ከ10 ወራት በፊት ነበር በሃማስ ከደቡባዊ እስራኤል በሃማስ ታጣቂዎች ታግቶ የተወሰደው ።
--በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን ሰሞኑን በተከታታይ በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ 23 ሰዎች ሞቱ። በአደጋዉ ከሞቱት ሰዎች በተጨማሪ 2700 ያክል ነዋሪዎች ከቤት ንብረታቸዉ ተፈናቅለዋል።
--የሱዳን ፈኖ ደራሽ ኃይል በዳርፉር ግዛት በስደተኞች መጠለያ ጣቢያ ላይ በፈጸሙት የከባድ መሳሪያ ጥቃት በትንሹ 20 ሰዎች ተገደሉ።
27/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos DW Amharic ነሐሴ 20 ቀን 2016 የዓለም ዜና
DW Amharic--በስለት ሦስት ሰዎች የተገደሉባትን ዞሊንገን የጀርመን ምዕራባዊ ከተማን ቻንስለር ኦላፍ ሾልዝ እና ታዋቂ የሃ ገሪቱ ፖለቲከኞች ለህዝብ አጋርነታቸዉን በማሳየት ከተማዋን ጎበኙ። IS የተባለዉ ጽንፈኛ ቡድን ሃላፊነት በወሰደበት በዚህ ጥቃት ሦስት ጀርመናዉያን ተገድለዋል፤ ስምንት ሰዎች ደግሞ ቆስለዋል።
--በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ በደረሰ ናዳ ህይወታቸው ካለፈ 10 ሰዎች መካከል እስካሁን የስድስቱን አስከሬን ማግኘት እንዳልተቻለ ተገለፀ። በሌላ በኩል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፤ ደቡብ አሞ ዞን ዳሰነች ወረዳ፤ በኦሞ ወንዝና በቱርካና ሀይቅ ሙላት በሺህዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተፈናቀሉ።
26/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos 25/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos DW Amharic የነሐሴ 18 ቀን 2016 የዓለም ዜና
በእስራኤል የፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂን መንግሥት በሚደግፉ እና በሚቃወሙ ሁለት ቡድኖች መካከል በተፈጠረው ግጭት ሁለት ኤርትራውያን መገደላቸውን ፖሊስ አስታወቀ። በምዕራብ ጀርመን በምትገኘው ዞሊንገን ከተማ ሦስት ሰዎች ከተገደሉበት እና ሌሎች ስምንት ከቆሰሉበት ጥቃት ጋር ግንኙነት ሳይኖረው አይቀርም የተባለ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የሀገሪቱ ባለሥልጣናት አስታወቁ። የኤርትራ የቀድሞ የፋይናንስ ሚኒስትር ብርሃነ ኣብርሀ በእስር ላይ ሳሉ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። በጋዛ በትንሹ 50 ፍልስጤማውያን በእስራኤል ጥቃት መገደላቸውን የጋዛ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።
24/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የነሐሴ 17 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
23/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የሐሙስ ነሀሴ 16 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
DW Amharic- ህወሃት የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደርን በአዳዲስ ተሿሚዎች ለመቀየር ውይይት እንደሚጀምር ማስታወቁ- ሶማሊያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ሀገሪቱ የሚያደርገውን በረራ እንደምታግድ መግለጿ- በአማራ ክልል ሁለት ዞኖች የመሬት መንሸራተት በሰብልና በመኖሪያ ቤቶች ላይ ጉዳት ማድረሱ- የኬንያ ፖሊስ ከ40 በላይ ሴቶችን በመግደል ከዕስር ያመለጠ አንድ ተጠርጣሪን ለጠቆመ የገንዘብ ወሮታ እንደሚከፍል ማስታወቁ-ታሊባን የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ መብቶች ልዩ ዘጋቢን ወደ አፍጋኒስታን እንዳይገቡ ማገዱ
22/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የረቡዕ ነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የነሐሴ 15 ቀን 2016 ዓ.ም. አርዕስተ ዜና
በኮንሶ ዞን ዋና ከተማ ሰገን የገቡት ታጣቂዎች ከተማዋን ተቆጣጠሩ፤የፖሊስ አባላትና ሰላማዊ ሰዎችንም ገደሉ።
የ7 ዓመትዋን ሄቨን አዎትን አስገድዶ በመድፈርና አንቆም በመግደል ጥፋተኛ የተባለው ጌትነት ባዬ ላይ ፍርድ ቤት ያስተላለፈውን የ25 ዓመት የእሥር ፍርድ በመቃወም በበይነ መረብ ፊርማቸውን ያኖሩ ሰዎች ቁጥር ዛሬ ከ240 ሺህ በላይ መድረሱ ተገልጿል።
ኬንያ ውስጥ በርካታ ሰዎችን በተከታታይ በመግደል ተጠርጥሮ የታሰረው ኬንያዊና 12ኤርትራውያን እስረኞች ናይሮቢ ከሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ እንዲያመልጡ በመርዳት የተከሰሱ አምስት የኬንያ ፖሊሶች ዛሬ ፍርድ ቤት ቀረቡ።
21/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የነሐሴ 14 ቀን 2014 ዓ/ም የዓለም ዜና
20/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos DW Amharic የነሐሴ 13 ቀን 2016 የዓለም ዜና
በምርጫ ቦርድ እውቅና የተነፈገው የህወሓት 14ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ ደብረፅዮን ገብረሚካኤልን ሊቀ-መንበር አድርጎ መረጠ። አቶ አማኑኤል አሰፋ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝደንት የሆኑት አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት ምክት ል ሊቀ-መንበር ሆነው ተመርጠዋል። የኬንያ መንግሥት ተቃውሞ በቀሰቀሰው የፋይናንስ ደምብ ውስጥ ተካተው ከነበሩ ቀረጦች የተወሰኑትን ሥራ ላይ በማዋል 1.2 ቢሊዮን ዶላር የመሰብሰብ ዕቅድ እንዳለው የሀገሪቱ ከፍተኛ ባለሥልጣን አስታወቁ። የተባበሩት መንግሥታት ተቀባይነት ከሌለው ደረጃ ደርሷል ያለውን የርዳታ ሠራተኞች ግድያ አወገዘ። ብዙ የርዳታ ሠራተኞች ከተገደሉባቸው አስር ሀገራት አንዷ ኢትዮጵያ ናት።
19/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የነሐሴ 12 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
18/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
17/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የነሐሴ 10 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
16/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos DW Amharic የነሐሴ 9 ቀን 2016 የዓለም ዜና
የጋምቤላ ምክር ቤት ዓለሚቱ ኡሞድን በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የክልል ፕሬዝደንት አድርጎ ሾመ። ከኢትዮ- ጅቡቲ ባቡር ትራንስፖርት አክሲዮን ማህበር 32 የጭነት ሎኮሞቲቮች 17ቱ አይሰሩም ተባለ። በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ የግብረ-ሠናይ ሠራተኛ ማንነቱ ባልታወቀ ወንጀለኛ ቡድን ተገደሉ። የ15 ዓመቱ ሔመን በቀለ የታይም መጽሔት የዓመቱ ምርጥ ታዳጊ ተብሎ ተመረጠ። የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት የአድሬ የድንበር መሸጋገሪያን ለሦስት ወራት ሊከፍት ነው። በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የጦጣ ፈንጣጣ 548 ሰዎች መግደሉ ተገለጸ። በጋዛ ተኩስ ለማስቆም የታቀደው የዶሐ ድርድር ያለ ሐማስ ተሳትፎ ተጀመረ።
15/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos DW Amharic የነሐሴ 8 ቀን 2016 የዓለም ዜና
ሶማሌላንድ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያን የምታሸማግለው ቱርክ ገለልተኛ አይደለችም ስትል ከሰሰች። የሶማሌላንድ ክስ የተደመጠው በአንካራ ለሁለተኛ ጊዜ የተካሔደው የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ ው ይይት ያለ ውጤት ከተበተነ በኋላ ነው። የሱዳንን ጦርነት ለማብቃት ያለመ ድርድር የብሔራዊው ጦር አዛዥ ጄነራል አብደል ፋታኅ አል-ቡርኻን በሌሉበት ተጀመረ። ግብጽ እና ሶማሊያ የወታደራዊ ትብብር ፕሮቶኮል ሥምምነት ተፈራረሙ። በጋዛ ውጊያ የገጠሙ ኃይሎች ተኩስ እንዲያቆሙ ለማድረግ ያቀደ ድርድር በቃጣር ሊካሔድ ነው። ጀርመን የኖርድ ስትሪም የጋዝ ማስተላለፊያን በማፈንዳት የጠረጠረችውን ግለሰብ ለመያዝ የእስር ማዘዣ አወጣች።
14/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos 13/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት የህወሓት “የሕግ ሰውነት፤ አግባብ ባለው ሕግ እና በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አሠራር መሠረት ብቻ እልባት ሊያገኝ የሚገባ ጉዳይ” እንደሆነ አስታወቀ። የኢትዮጵያ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በሀገሮቻቸው መካከል የተቀሰቀሰውን ውጥረት ለማብቃት በቱርክ አሸማጋይነት በአንካራ ተገናኙ። በዩጋንዳ በደረሰ የቆሻሻ መደርመስ አደጋ ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 23 ደረሰ። በጋዛ በአስቸኳይ ተኩስ እንዲቆም ጀርመን፣ ፈረንሳይ እና ዩናይትድ ኪንግደም ጥሪ አቀረቡ። ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን ወደ ሩሲያ ግዛት የገቡ የዩክሬን ወታደሮችን የሀገራቸው ጦር እንዲያባርር ትዕዛዝ ሰጡ
12/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos 11/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos 10/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የአርብ ነሐሴ 3 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን ግንደወይን ከተማ በደረሰ የመኪና አደጋ ወንዝ ውስጥ የሰጠሙ ሰዎች አስከሬን የማፈላለግ ስራ መቀጠሉ ተገለፀ።
አቶ ጌታቸው ረዳ፤ ህወሓት አካሂዳ ለሁ ካለው ጠቅላላ ድርጅታዊ ጉባኤ ራሳቸውን ማግለላቸውን አስታወቁ።
ሊባኖስ ውስጥ ያለው ሁኔታ የሚባባስ ከሆነ በተለይ ችግር ያለበት አካባቢ ያሉ ኢትዮጵያውያንን ለማውጣት ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለፀ።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሾፍቱ ከተማ አከባቢ ግዙፍ የአውሮፕላን ማረፊያ ሊያስገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የሱዳን መንግሥት ከአሜሪካ ጋር ለመመካከር የልዑካን ቡድኑን ወደ ጅዳ እንደሚልክ ገለፀ።
9/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos DW Amharic የዓለም ዜና፤ ነሐሴ 2 ቀን 2016 ዓ.ም.ሃሙስ
--የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን “የፕሬዚዳንቱ የሕይወት ዘመን ሽልማት” ተበረከተለት፡፡
--በኢትዮጵያዋ ሶማሌ ክልል በዋቢ ሸቤሌ ወንዝ እስከ ገደፉ ሞልቶ በተከሰተ ጎርፍ ወደ ሦስት ሺህ የሚጠጉ ሰዎች ከመኖርያ ቀዬያቸው መፈናቀላቸውን የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።
--የተለያዩ የኤርትራ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በሥልጣን ላይ ያለውን አምባገነን ያሉትን መንግሥት ለመታገል የጋራ ጥምረት መመስረታቸውን አስታወቁ።
--ኬንያ የወጣቶች ተቃውሞ ዛሬ በመዲናዋ ናይሮቢ በርካታ ወጣቶች በተሳተፉበት ዳግም መቀስቀሱ ተነገረ።
8/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የረቡዕ ነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም.የዓለም ዜና
የነሐሴ 1 ቀን 2016 ዓ.ም.አርዕስተ ዜና
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ከሚኖሩበት መጠለያ ጣቢያዎች ወጥተው በመንገድ ዳር ከሚኖሩ የሱዳን ተፈናቃዮች መካከል አንዳንዶቹ ባለፈው ቅዳሜ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው ተናገሩ።
እስራኤል፣ ዩናይትድ ስቴትስ፣ ብሪታንያ ፣ጀርመን የአውሮጳ ኅብረትና ሌሎች በአሸባሪነት የፈረጁት ታጣቂ ቡድን ሐማስ ያህያ ሲንዋርን የቡድኑ ከፍተኛ መሪ አድርጎ መረጠ።
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሜዳሊያ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ የተገመተበት የወንዶች የሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ውድድር ዛሬ ምሽት 4:40 ይደረጋል። በውድድሩ የክብረ ወሰን ባለቤቱ ለሜቻ ግርማ ሳሙኤል ፍሬው እና ጌትነት ይሳተፋሉ።
7/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos *በመካከለኛው ምስራቅ ያየለው የጦርነት ስጋት
*ኢትዮጵያ፦ የአምነስቲ ኢንተርናሽናል የፍትህ ጥያቄ
*75 የፖሊስ አባላትን ገድለዋል የተባሉ ተፈረደባቸው
*አቶ ታዬ ደንደዓ ከተመሰረተባቸው ሶስት ክሶች በሁለቱ ነጻ ተባሉ
*ሱዳን፤ የስደተኞች መጠለያ ከአየር ጥቃት ደረሰ
*ሩሲያ ወታደሮች ከዮክሬይን ጋር ወደሚያዋስናት ድንበር ላከች
6/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የዓለም ዜና፤ ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም ሰኞ
-የባንግላዴሽ የጠ/ሚ ሼክ ሃሲና በህዝባዊ ትግል ከስልጣን ለቀቁ። የ 76 ዓመትዋ ሃሲና፤ ምናልባትም ወደ ህንድ ሳይሰደዱ አልቀረም። -በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ በመሬት ናዳ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡ በአደጋዉ የሞቱት ሰዎች ቁጥር ሳይጨምር አይቀርም።-የደቡብ አፍሪቃ ፖሊስ ጆሃንስበርግ ዉስጥ ታፍነዉ ተይዘዉ የነበሩ 90 ኢትዮጵያዉያን ስደተኞችን ነፃ አስለቀቀ። ፍልሰተኞቹን ያፈኑት ሁለት የሰዎች አዘዋዋሪ ተጠርጣሪዎች ተይዘ ዋል።-ማሊ ከዩክሬይን ጋር ያላትን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት አቋረጠች። የማሊ ዩክሪን አማፅያኑ ባደረሱት ጥቃት እጇ አለት በሚል ነዉ። ዩክሬይን የማሊ እርምጃን ኮንናዋለች።
5/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
የሐምሌ 28 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም ዜና
በተቃውሞ እየተናጠች ያለችው ናይጄሪያ
የዩክሬይን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአፍሪካ ጉብኝት
4/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የሐምሌ 27 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
3/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የአርብ ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
የአርብ ሐምሌ 26 ቀን 2016 ዓም አርዕስተ ዜና
ጠቅላይ ሚንስትር ዐብይ አሕመድ በአማራ ክልል ከመንግሥት ጋር ከሚዋጉ አንዳንድ ቡድኖች ጋር ውይይት መጀመሩን ለመጀመሪያ ጊዜ መናገራቸው በክልሉ ነዋሪዎች አስተያየት እየተሰጠበት ነው። አንዳንድ የክልሉ ነዋሪዎች ሃሳቡን የተቀደሰ ሲሉ ፣ሌሎች ደግሞ ጥርጣሬ ገብቷቸዋል።
በግጭት በተመሰቃቀለው በዳርፉር በሚገኘው ዘምዘም መጠለያ ኮሌራና ሌሎች መሰል በሽታዎች እንዳይሰፋፉ አስግቷል።
ረቡዕ ቴህራን ውስጥ በአየር ጥቃት የተገደሉት የሃማስ ከፍተኛ መሪ የኢስማኤል ሀኔይ አስከሬን ሽኝትና ስርዓተ-ቀብር በስደት ይኖሩበት በነበረው በዶሀ በከፍተኛ የጸጥታ ጥበቃ ዛሬ ተፈጸመ።
2/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የሐምሌ 25 ቀን 2016 ዓ.ም. የዓለም ዜና
በአዲስ አበባ ከተማና ኦሮሚያ ክልል የብር አቅም መዳከምን ተከትሎ በሸቀጦች ላይ ዋጋ ጭማሪ ያደረጉ በርካታ የንግድ ድርጅቶች መዘጋታቸው ተገለጸ።
በጸጥታ ችግር ምክንያት ለፈተና በሄዱበት ሰላሌ ዩኒቨርሲቲ ለሁለት ሳምንታት ያህል መቆየት የተገደዱት ከ400 በላይ ተማሪዎች ትናንት ማምሻውን ወደ ቤተሰቦቻቸው መመለሳቸው ተሰማ።
የናይጀሪያ ፖሊስ በሀገሪቱ የተባባሰውን የዋጋ ንረትና የአስተዳደር ችግር በመቃወም አደባባይ ከወጡ ሰልፈኞች ጋር ፍጥጫ ገጥሟል።
ትናንት ለተገደሉት የሃማሱ መሪ በኢራን ብሔራዊ የአስክሬን ሽኝት ሥረዓት ተከናወነ። አዲሱ የኢራን ፕሬዝደንት መንግሥታቸው ለሃማስ የሚያደርገው ድጋፍ ይጨምራል ብለዋል።
1/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos የሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ/ም የዓለም ዜና
DW Amharic
-በጎ ፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የሟቾችን አስክሬን የማፈላለጉ ሥራ ማብቃቱን የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት አስታወቀ ፡፡-የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር የህወሃት አመራሮችን ኮነነ። ጊዚያዊ አስተዳደሩ የህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ /ህወሓት/ አመራሮችን የኮነነው፤ በሙስና እና በተደራጀ የማዕድን የመሬት ዘረፋ ፣ በመሳሪያ ንግድ እና በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውር ነው።-የሱዳን ወታደራዊ መሪ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን የግድያ ሙከራ ተፈጸመባቸው።-የሃማስ መሪ እስማኤል ሃኒዬህ ኢራን ውስጥ ከጠባቂያቸው ጋር ተገደሉ።
31/7/2024 • 0 minutos, 0 segundos 30/7/2024 • 0 minutos, 0 segundos * በሲዳማ ክልል በተከሰተ የመሬት መንሸራታት 11 ሰዎች ሞቱ
* የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በውጭ ምንዛሪ ላይ ማሻሻያ አደረገ
*የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ፀጥታ ምክር ቤት ውሳኔዎች አስተላለፈ
*ፆታዊ ጥቃት እና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በሱዳን
*እስራኤል፤ በሂዝቦላህ ላይ ወታደራዊ ርምጃ ለመውሰድ ወሰነች
* ፈረንሳይ፤ በኢንተርኔት አገልግሎት መስመሮች ላይ ጥቃት ተፈፀመ
29/7/2024 • 0 minutos, 0 segundos 28/7/2024 • 0 minutos, 0 segundos