Winamp Logo
እንወያይ | Deutsche Welle Cover
እንወያይ | Deutsche Welle Profile

እንወያይ | Deutsche Welle

Amharic, Debates / Conferences, 1 season, 105 episodes, 2 days, 22 hours, 48 minutes
About
ኢትዮጵያን በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት የዓለም ሀገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋ የምናካሂደውን እና በየሣምንቱ እሁድ ከምሽቱ አንድ ሰዓት ከአሥር ደቂቃ ላይ የሚተላለፈውን የውይይት ዝግጅት ያዳምጡ።
Episode Artwork

የሁለቱ ወገኖች የስልጣን ሽኩቻ ወዴት ያመራ ይሁን?

በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና በህወሐት መካከል ያለው የስላጣን ሽኩቻ ተካሮ አንዱ በአንዱ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻው በግላጭ እየተካሄደ ከመሆኑም አልፎ ጎራ ለይተው እስከመገዳደል እንዳይደረስና የተገኘው አንጻራዊ ሰላም እንዳይደፈርስ ብዙዎቹ የክልሉ ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
5/12/202440 minutes, 51 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፤ ኢትዮጵያ ሌላ ዙር ግጭትን ለመሸከም ጫንቃዉ አላት?

ትግራይና አማራ ክልል በሚወዛገቡባቸዉ አካባቢዎች የተቀሰቀሰዉን ዉጥረት እንዴት አያችሁት? ምንስ ተሰማችሁ? ከየትኛዉም ወገን ይሁን ያ ሁሉ ህዝብ ካለቀ እና ንብረት ከወደመ በኋላ በፕሪቶርያዉ ስምምነት ሰላም ይሰፍናል ተብሎ ሲጠነቅ ዳግም ወደ ሌላ ዉጥረት እየተገባ ነዉ? ይህን ዉጥረት ህዝቡና ሃገሪቱ መሸከም ይችላሉ? ምንድን ነዉ መደረግ ያለበት?
4/28/202445 minutes, 49 seconds
Episode Artwork

አደገኛው የኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰት

ወደ ሳዑዲ አረብያ ለመሄድ ጉዞ የጀመሩ 38 ኢትዮጵያውያን ጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ የተጫኑበት ጀልባ ሰጥሞ ባለፈው ሳምንት ሞተዋል። በዚሁ ሳምንት ነበር ሳዑዲ አረብያ ውስጥ ችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ጥረት የቀጠለው።በአሁኑ ጊዜ በአደገኛ ጉዞ መላልሰው ወደ መካከለኛው ምሥራቅና ወደ ደቡብ አፍሪቃ የሚሄዱ ጥቂት አይባሉም።
4/21/202442 minutes, 10 seconds
Episode Artwork

አደገኛው የኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰት

4/21/202442 minutes, 10 seconds
Episode Artwork

በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕጣ ፈንታ

4/14/202439 minutes, 29 seconds
Episode Artwork

ኢትዮጵያ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስድስት የሥልጣን ዓመታት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን የያዙበት ስድስተኛ ዓመት ደጋፊዎቻቸው በሰልፍ ተቃዋሚዎቻቸው በትችት አስበውታል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ጆን አሕመድ፣ ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ሙከርም ሚፍታህ፣ ከጁሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ሰይፈ ታደለ የተሳተፉበት ውይይት ለመሆኑ ዐቢይ ምን አሳክተው ምን አጎደሉ? ሲል ያጠይቃል
4/7/202443 minutes, 21 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፦ ኢትዮጵያ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስድስት የሥልጣን ዓመታት

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን የያዙበት ስድስተኛ ዓመት ደጋፊዎቻቸው በሰልፍ ተቃዋሚዎቻቸው በትችት አስበውታል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ጆን አሕመድ፣ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር ሙከርም ሚፍታህ በደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር ሰይፈ ታደለ የተሳተፉበት ውይይት በስድስት ዓመታት ዐቢይ ምን አሳክተው ምን አጎደሉ? ሲል ያጠይቃል።
4/6/202443 minutes, 21 seconds
Episode Artwork

የፊት ለፊቱ ንግግር አንድምታ እና የኢትዮጵያ መሻት

ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የትግራዩ ጦርነት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተለያዩ ክልሎች የህዝብ ተወካዮች ጋር በተከታታይ ውይይት እያደረጉ ነው። በየውይይቱ ክልሎቹም ሆኑ የኃይማኖት ተቋማቱ በተናጥል እና የጋራ ወቅታዊ የሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ ፣ አስተያየት እና ጥቆማ ሰጥተዋል፤ አፋጣኝ ምላሽ ይሻሉ ያሏቸውንም ጥያቄዎች አንስተዋል።
3/24/202441 minutes, 31 seconds
Episode Artwork

ግጭት ጦርነት እንዲቆም ፤ ፖለቲካዊ ንግግር በአፋጣኝ እንዲጀመር ከተወያዮች ጥያቄ ቀርቧል

3/24/202441 minutes, 31 seconds
Episode Artwork

ከፕሪሪቶሪያ ስምምነት አፈጻጸም ምን እንማር?

አፈራራሚዎቹ በግጭቱ የተጎዱትን መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ ተጎጂዎችን ያማከለ የሽግግር የፍትሕ ሂደት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የስምምነቱ ፈራሚዎች መገናኘታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አድርገዋል።እነዚህ የበለፀጉ እንዲሁም በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተከሰቱት ቀውሶች በተመሳሳይ ቁርጠኝነት ችግሩ እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።
3/17/202440 minutes, 53 seconds
Episode Artwork

ዉይይት፣ የኦሮሚያና የአማራ ክልል ግጭቶች ለምን አይቆሙም?

የተለያዩ መገናኛ ዘዴዎች፣የመብት ተሟጋቾች፣የርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ከሁሉም በላይ የየአካባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት በየግጭት፣ ዉጊያ ጥቃቶቹ የሚያልቅ፣ የሚቆስል፣የሚፈናቀለዉ ሕዝብና የምትደፈረዉ ሴት ቁጥር እየጨመረ ነዉ።
3/10/202440 minutes, 24 seconds
Episode Artwork

ዉይይት፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የሚደረጉት ግጭቶች ለምን አይቆሙም?

3/10/202440 minutes, 24 seconds
Episode Artwork

አሳሳቢው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ በአማራ ክልል

ኢሰመኮ በቅርቡ በመርዓዊ ከተማ በሲቭሎች ላይ በመከላከያ ሠራዊት ከሕግ ውጭ ግድያዎች መፈጸሙን ለማወቅ መቻሉን አስታውቋል። በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር ያረጋገጠው መንግሥት የመከላከያ ኃይሉ የትኛውንም ዓይነት ሲቪል ዒላማ አላደረገም ሲል አስተባብሏል።
2/25/202439 minutes, 30 seconds
Episode Artwork

አሳሳቢው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ በአማራ ክልል

2/25/202439 minutes, 30 seconds
Episode Artwork

50 ዓመታት፦ የኢትዮጵያ አብዮት ውርስ ምንድነው?

የአጼ ኃይለሥላሴን ዘውዳዊ መንግሥት ከፍጻሜ ያደረሰው የኢትዮጵያ አብዮት 50 ዓመታት ሞላው። የካቲት 1966 “ፈነዳ” የሚባለው አብዮት “መሬት ላራሹ” የተፈከረበት፣ የብሔሮች እና የሐይማኖት ዕኩልነት የተጠየቀበት ነው። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር መላኩ ተገኝ እና ዶ/ር ኢዮብ ባልቻ የተሳተፉበት ውይይት የአብዮቱ ውርስ ምንድነው? ሲል ያጠይቃል።
2/18/202440 minutes, 45 seconds
Episode Artwork

50 ዓመታት፦ የኢትዮጵያ አብዮት ውርስ ምንድነው?

የአጼ ኃይለሥላሴ ዘውዳዊ መንግሥትን በማስወገድ የፊውዳላዊ ሥርዓትን ከፍጻሜ ያደረሰው የኢትዮጵያ አብዮት የተቀሰቀሰው ከ50 ዓመታት በፊት ነበር። በየካቲት ወር 1966 “ፈነዳ” የሚባለው አብዮት “መሬት ላራሹ” የተፈከረበት፣ የብሔሮች፣ የሐይማኖት ዕኩልነት የተጠየቀበት ነው። የታክሲ አሽከርካሪዎች፣ ሠራተኞች፣ መምህራን እና ወታደሮች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንገብ በየፊናቸው በዘውዳዊው መንግሥት ላይ ጫና ያደርጉ ነበር። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ዶክተር መላኩ ተገኝ እና ዶክተር ኢዮብ ባልቻ የተሳተፉበት ውይይት የኢትዮጵያ አብዮት ውርስ ምንድነው? ሲል ያጠይቃል።
2/17/202440 minutes, 45 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፤ በአንድ ላይ ቆመው ለኢትዮጵያ ይጮሁ የነበሩ ወገኖች ዛሬ የት ናቸዉ?

2/4/202443 minutes, 36 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፤ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሚና ከየት ወዴት?

በዉጭ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊና ትዉልደ ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራ) በኢትዮጵያ ፖለቲካ፤ ኢኮኖሚና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ፤ ከፍተኛ ሚናን እንደሚጫወት ይታወቃል። አሁን አሁን ግን አብዛኛዉ ዲያስፖራ በዘላቂ የአገሪቱ ጥቅሞች ላይ አንድ ላይ መቆሙ ቀርቶ፤ ተጻራሪና ግዚያዊ የሆኑ የቡድን ፍላጎቶችን ይዞ በየፊናው ቆሞ መታየቱ የተለመደ ሁኗል። ችግሩ ምን ይሆን?
2/4/202443 minutes, 36 seconds
Episode Artwork

ዉይይት፣ የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ ስምምነት፣ ድጋፍ፣ተቃዉሞና ዉግዘቱ

በዓባይ ወንዝ ዉኃ አጠቃቀም ሰበብ ከኢትዮጵያ ጋር የምትወዛገበዉ ግብፅ ደግሞ ለዉጊያም እየተጋበዘች ነዉ።የግብፅ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚሕ ሽኩሪ ኢትዮጵያን «የአካባቢዉ ያለመረጋጋት ምንጭ» በማለት ወንጅለዋታል።የሐገሪቱ ፕሬዝደንት የቀድሞዉ ፊልድ ማርሻል አብዱልፈታሕ አልሲሲ በበኩላቸዉ ሶማሊያና ደሕንነቷ ላደጋ ከተጋለጠ ግብፅ ጣልቃ ለመግባት
1/28/202441 minutes, 2 seconds
Episode Artwork

ዉይይት፣ የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ ስምምነት፣ ድጋፍ፣ተቃዉሞና ዉግዘቱ

1/26/202441 minutes, 2 seconds
Episode Artwork

የኢትዮጵያ የጸጥታ እና የደህንነት ተቋማት ወቅታዊ ሁኔታ

1/21/202443 minutes, 5 seconds
Episode Artwork

ቅድሚያ ለማን?

ከውጭና ከሃገር ውስጥ በተሰበሰበ የአገሪቱ ሀብት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት እየተገነቡ ያሉ የመናፈሻዎችና የቤተመንግስት ግንባታዎች፤ በቀጥታ ከመንግስት ካዝና በቢልዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ተደርጎ የሚካሄዱ የመንግስት መስሪያቤቶች እድሳት አነጋጋሪነታቸው እንደቀጠለ ነው።
1/7/202440 minutes, 18 seconds
Episode Artwork

ውይይት፦ ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ማዳከም ወይስ…የኢትዮጵያ አጣብቂኝ

ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ባለፉት አራት ዓመታት በባንኮችም ይሁን በጎንዮሽ ገበያው ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። ብር ሲዳከም ለኢትዮጵያ ምን ፈየደ? ለሀገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ሁለተኛ ምዕራፍ ዳጎስ ያለ ማስፈጸሚያ የሚሻው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሚቀነቀነውን ብርን የማዳከም እርምጃ ሊቀበል ይችላል?
12/24/202340 minutes
Episode Artwork

የኢትዮጵያ አጣብቂኝ፦ ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ማዳከም ወይስ…?

ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ባለፉት አራት ዓመታት በባንኮችም ይሁን በጎንዮሽ ገበያው ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። ብር ሲዳከም ለኢትዮጵያ ምን ፈየደ? ለሀገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ሁለተኛ ምዕራፍ ዳጎስ ያለ ማስፈጸሚያ የሚሻው መንግሥት በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሚቀነቀነውን ብርን የማዳከም እርምጃ ሊቀበል ይችላል?
12/24/202340 minutes
Episode Artwork

ግጭት የጋረደው ድርቅና የርሃብ አደጋ

12/17/202339 minutes, 33 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፤ በአማራ ክልል የቀጠለዉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማቆምያዉ የት ነዉ?

ለአማራ ክልሉ ሰብዓዊ ቀዉስ ተጠያቂዉ ማን ነዉ? በትግራይ ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተገድለዋል። አሁንም በአማራና በኦሮሚያ ክልል ጦርነቱ ቀጥሏል። መንግሥት ከቀዉስ ማትረፍ ፖሊሲዉን ማቆም አለበት፤ ጠ/ሚኒስትሩ ስልጣን መልቀቅ አለባቸዉ፤ በሃገሪቱ የተኩስ አቁም ታዉጆ ዉይይት መጀመር አለበት» ይላሉ ተወያዮች እርሶስ?። እርሶስ? ይጻፉልን!
12/10/202343 minutes, 15 seconds
Episode Artwork

የመንግስትና የፓርቲ ሚና መቀላቀል

11/26/202340 minutes, 22 seconds
Episode Artwork

የሰላም ንግግሩ ተስፋ እና የሀገሪቱ መጻኢ ዕጣ ፈንታ

ከወራት ዝምታ በኋላ ተፋላሚ ወገኖች ለሌላ የሰላም ንግግር በታንዛንያዋ የንግድ ከተማ ዳሬ ሰላም ተቀምጠዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም ንግግር እየተደረገ መሆኑን ከሳምንት ዝምታ በኋላ ባለፈው ሐሙስ ነበር ይፋ ያደረገው ። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተደራዳሪዎቹ ከመንግስት ተወካዮች ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ቀደም ብሎ ነበር ያስታወቀው።
11/19/202343 minutes, 41 seconds
Episode Artwork

መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር የሚያደርገው የሰላም ንግግር ዘላቂ ሰላም ያመጣ ይሆን ?

11/19/202343 minutes, 41 seconds
Episode Artwork

ከምንም በላይ ሕጻናት፤ ሴቶችና አረጋውያን ተጎጂዎች ናቸው

11/12/202340 minutes
Episode Artwork

በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ላይ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች

11/5/202336 minutes, 28 seconds
Episode Artwork

በተፈናቃዮች ላይ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብቶችት ጥሰቶች

ድንገት ተፈናቅለው በወጡበት የቀሩ ፣በማያውቁትና መጠለያ ሊባሉ በማይችሉ ስፍራዎች ለብዙ ጊዜያት የቆዩ በርካቶች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ችግሮቻቸው እየተባባሱ እንጂ እየቀነሱ አልሄዱም። በመጠለያ ጣቢያዎች ለከፋ ችግር ከተጋለጡት አብዛኛዎቹ ምርጫ በማጣታቸው ወደ ቀድሞው ቀያቸው ለመመለስ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። ሆኖም የጸጥታ ስጋት አላቸው።
11/5/202336 minutes, 28 seconds
Episode Artwork

ዉይይት፣ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብርና አሰራር

10/27/202339 minutes, 51 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፤ የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደቁ የተባሉበት አሳሳቢዉ ዉጤትና አንደምታዉ

ከ 800 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች መዉደቃቸዉ ብቻ ሳይሆን፤ በችግር ያስተማሩ ወላጆች ብሎም በህብረተሰቡ ላይ የሚፈጥረዉ ጫና ቀላል አለመሆኑ ነዉ። የችግሩ መንስኤ ምንድነው? የትምህርት ስርዓት ዉድቀት? ጥቂት ተማሪዎች ብቻ ለከፍተኛ ተቋማት በቁ፤ ብዙኃኑ ግን ወድቋል፤ የተባለለበትን ፈተና የወደቀዉ ማነዉ? እንዴት ትገመግሙታላችሁ? ጻፉልን!
10/22/202339 minutes, 41 seconds
Episode Artwork

በተስፋ የተሞሉ ተማሪዎች መዉደቃቸዉ የተሰማበት ዜና፤ በኑሮ ዉድነት በቀዉስ ብሎም ከጦርነት ወጥታ ወደ ሌላ ጦርነት ለገባችዉ ሃገር ኢትዮጵያ ሌላ እራስ ምታት ነዉ። ሃላፊነቱን ማን ይዉሰድ?

10/22/202339 minutes, 41 seconds
Episode Artwork

ውይይት፦ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ለመመርመር የተቋቋመው ኮሚሽን ሥራ መቋረጥ ምን ያጎድላል?

10/15/202340 minutes, 3 seconds
Episode Artwork

ያለተጠያቂነት እየተባባሰ የመጣው የሰብአዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ

10/9/202339 minutes, 48 seconds
Episode Artwork

«በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ከሰብአዊ መብት አንጻር እንዴት ይታያል?»

በኢትዮጵያ ሚሊዮኖች የሚኖሩባቸው የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከኢንተርኔቱ ዓለም እንዳይገናኙ ከተዘጋባቸው ሰነባብተዋል ። ሌላው ቀርቶ የቀጥታ ስልክ መስመር አገልግሎት የማያገኙ አካባቢዎች እና ከተሞች ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ። በኢትዮጵያ አንዳች ነገር ኮሽ ሲል የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት በተደጋጋሚ ሲቋረጥ ይስተዋላል ።
9/24/202340 minutes, 4 seconds
Episode Artwork

አዲሱ ዓመት ለተቀጣሪው ሰራተኛ ተስፋ ወይስ ስጋት ?

በሀገሪቱ በተለይ የመሰረታዊ ፍጆታ ቁሶች እና የቤት ኪራይ በየጊዜው ያለከልካይ እጅግ በተጋነነ ሁኔታ ጭማሪ ሲያሳዩ ሰራተኛው በወር በሚያገኘው ደመወዝ ላይ ጭማሪ ስለመደረጉ ብዙም አይሰማም ወይም ቢኖርም ያለውን የገበያ እና የኑሮ ሁኔታ የሚመጥን ሆኖ አለመገኘቱ ነው የሚነገረው ።
9/17/202345 minutes, 28 seconds
Episode Artwork

በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው ተቀጣሪ የህብረተሰብ ክፍል ተስፋው ምን ይሆን?

9/17/202345 minutes, 28 seconds
Episode Artwork

የመጪው የ2016 ዓም ተግዳሮችና ተስፋ

2015 ግጭቶች የተካሄዱበት፣ የመንግሥት ተባባሪ የነበሩ ውጊያ የገጠሙበት ፣ጎሳ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የደረሰበት ፣ቤቶች የፈረሱበት ሰዎች የተፈናቀሉበት፣ የኑሮ ውድነት እጅግ የናረበት ጋዜጠኞች የታሰሩበት ኢንተርኔትም የተቋረጠበት ዓመት ነበር። እነዚህ ችግሮች ወደ 2016 ዓም እንዳይሻገሩ ለመከላከል ምን መደረግ አለበት?
9/10/202341 minutes, 41 seconds
Episode Artwork

የአማራ ክልል ግጭት፤ የጅምላ እስር እና የመገናኛ አውታሮች ሽፋን

አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የአማራ ተወላጆች በጅምላ ለእስር መዳረጋቸው ከብዙ አቅጣጫ ይሰማል ። ብሔር ተኮር እስሩ መባባሱ፤ ትምህርት ቤቶች ጭምር በታሰሩ ሰዎች መጨናነቃቸውን በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ለመሆኑ ይህ ምን ያህል የመገናኛ አውታሮች ሽፋን አገኘ?
8/27/202339 minutes, 54 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ሰላምን ያመጣ ይሆን?

ተወያዮች፤የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተፈጥሮዉ መብት ገዳቢ ነዉ፤ኢትዮጵያም ተሞክሮ ይህንኑ ያሳያል። መንግሥትን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ዝም ያለዉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሁሉ ለሰላም ወደ ድርድር እንዲመጡ፤ጦርነትም ይቁም ሲሉ ጥሪ አሰምተዋል።መንግሥት የጅምላ እስሩን ያቁም፤የአማራ ክልልን ጥያቄዎች ይመልስ ብለዋል። እርሶስ? አስተያየት አሎት?
8/20/202342 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ሰላምን ያሰፍን ይሆን? የክልሉን ጥያቄዎችስ ይፈታ ይሆን?

8/20/202342 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

ውይይት፦ የአማራ ክልል ቀውስ ገፊ ምክንያቶች፣ ዳፋው እና በውይይት የመቋጨት ተስፋ

8/15/202339 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

የአማራ ክልል ቀውስ፦ ገፊ ምክንያቶች፣ ዳፋው እና በውይይት የመቋጨት ተስፋ

በአማራ ክልል ሲብላላ የቆየው ቅራኔ በሣምንቱ መጀመሪያ ወደ ውጊያ ቢያመራም የመረጋጋት ዝንባሌ አሳይቷል። የቀውሱ ገፊ ምክንያቶች ምንድናቸው? በውይይት ካልተቋጨ በአማራ ክልል እና በኢትዮጵያ ላይ የሚያስከትለው ዳፋ ምን ሊሆን ይችላል? ዶክተር ታደሰ ጥሩነህ፣ ዶክተር ብዙነህ ጌታቸው እና ዶክተር ሰማኸኝ ጋሹ በዚህ ውይይት ተሳትፈዋል።
8/14/202339 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት ተስፋ እና ስጋት

7/30/202340 minutes, 9 seconds
Episode Artwork

እንወያይ

7/2/202340 minutes, 40 seconds
Episode Artwork

ውይይት፦ የዎላይታ ሕዝበ-ውሳኔ እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ

6/25/202338 minutes, 32 seconds
Episode Artwork

ሣምንታዊ የእንወያይ መሰናዶ

6/4/202339 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

ዘላቂው መፍትሄ ከየት ይምጣ?

5/28/202341 minutes, 55 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፤ ኢትዮጵያ ከግጭትና ቀዉስ አዙሪት እንዴት ትዉጣ?

በተለያዩ የግጭት ምዕራፍ ውስጥ ገብታ እየተናጠች ያለችው ኢትዮጵያ መውጫዋ ወዴት ይሆን? ምንድን ነዉ ከአንዱ ችግር ወጥተን ወደሌላ ችግር የምንገባበት ምክንያት? መንግሥትን ለመጣል የሚደረግ ትጥቅ ትግል ጊዜዉ ነዉ ወይ? መንግሥትም ሆነ ታጣቂዎች ጦርነት ዉስጥ መግባት ህዝብን ጦርነት ዉስጥ ማስገባት መቼ ነዉ የሚቆመዉ? ከየት ይምጣ ዘላቂው መፍትሄ?
5/28/202341 minutes, 55 seconds
Episode Artwork

አሳሳቢ እየሆነ የሄደው የፕረስ ነጻነት ይዞታ በኢትዮጵያ

5/14/202340 minutes, 20 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፦ የሸገር ከተማ አስተዳደር ቤት ፈረሳ እና ውዝግቡ

4/23/202340 minutes, 42 seconds
Episode Artwork

የክልል ልዩ ኃይሎች መፍረስ እና አንድምታው

4/16/202342 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

የጉራጌ የክልልነት ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ እና ምላሹ

በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 47 መሰረት ማንኛውም ብሔር ብሔረሰብ በማንኛውም ጊዜ የክልልነት ጥያቄ ማንሳት ሕገ መንግሥታዊ መብቱ እንደሆነ ይደነግጋል ። ለመሆኑ የጉራጌ ሕዝብ ክልል ልሁን፤ ራሴን በራሴም ላስተዳድር ብሎ ያቀረበው ጥያቄ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ከመንግሥት የተገኘው ምላሽስ ምንድን ነው? ሳምንታዊ እንወያይ መሰናዶ።
4/9/202340 minutes, 36 seconds
Episode Artwork

ኢትዮጵያ ለሽግግር ፍትህ ዝግጁ ነች?

ኢትዮጵያ ለሽግግር ፍትህ ዝግጁ ነች? የፍትህ ሚኒስቴር ካቋቋመው ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን አቶ ምስጋናው ሙሉጌታ እና ዶ/ር ማርሸት ታደሰ፤ በሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት የሰብዓዊ መብቶች መርሐ-ግብር ተባባሪ ዳይሬክተር ዶክተር አባድር ኢብራሒም እና ዘ-ሔግ በሚገኝ ፍርድ ቤት በአማካሪነት የሚሰሩት አቶ ካሳሁን ሞላ በውይይቱ ተሳትፈዋል
3/26/202343 minutes, 38 seconds
Episode Artwork

ውይይት፦ ኢትዮጵያ ለሽግግር ፍትህ ዝግጁ ነች?

3/26/202343 minutes, 38 seconds
Episode Artwork

ዉይይት፤ የፕሪቶርያዉ ስምምነት በርግጥ ተፈጻሚ እየሆነ ነዉ?

ፕሪቶርያ ላይ በሰላም ስምምነት ከተቋጨ አራት ወር የሆነዉና አስከፊ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የተፈፀመበት የሰሜን ኢትዮጵያዉ ጦርነት ቢያበቃም ብዙዎች በሰላም ስምምነቱ አፈፃፀም ላይ ጥርጣሬ አላቸዉ። መንግሥት ስምምነቱን እያስፈጸመ አይደለም፤ የሚሉ እንዳሉ ሁሉ ህወሓት ሁሉን አካታች የሆነ ሽግግር መንግሥት ለመመስረት አልቻለም፤ የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም።
3/20/202342 minutes, 33 seconds
Episode Artwork

የፕሪቶርያዉ የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት በምን ደረጃ ላይ ነዉ? የፌደራል መንግሥት እና ህወሓትስ ምን ተወያዩ? ምንስ ተስማማ?

3/19/202342 minutes, 33 seconds
Episode Artwork

እንወያይ

3/12/202338 minutes, 44 seconds
Episode Artwork

የሩስያና ዩክሬን ጦርነት ወዴት እያመራ ነው?

2/26/202340 minutes, 1 second
Episode Artwork

ሶስት ሕዝበ-ውሳኔዎች፤ አራት ክልሎች፦ የደቡብ ጥያቄ ተመለሰ?

2/13/202340 minutes, 25 seconds
Episode Artwork

የአዲስ አበባ የተጨማሪ ቋንቋ ስርዓተ ትምሕርት አተገባበርና ትችቱ

1/22/202339 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

የአዲስ አበባ የአንደኛ ደረጃ የተጨማሪ ቋንቋ ስርዓተ ትምሕርት አተገባበርና ትችቱ

ተማሪዎች ተጨማሪ የአገር ውስጥ ቋንቋ እንዲማሩ የሚያደርገውን ውሳኔ ጠቀሚ ሲሉ የደገፉት እንዳሉ ሁሉ በጥድፍያ የተከናወነና ፖለቲካዊ ጫናም ያረፈበት ነው በማለት የተቹትም አሉ። የከተማዋ ነዋሪ በጉዳዩ ላይ በቂ ውይይት አላካሄደም የትምሕርቱም አዋጭነት በሙከራ ደረጃ ሳይፈተሽ ተግባራዊ መሆኑ አግባብ አይደለም የሚሉና የመሳሳሉ ትችቶችም ቀርበውበታል
1/22/202339 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

መንግሥት ካጠፋን ቆንጥጡን ብሏል? በሰላሙ ጥረት ማህበረሰቡ እንዲነጋገር ለምን መድረክ አልተሰጠዉም?

1/15/202340 minutes, 44 seconds
Episode Artwork

ዉይይት፤ የኢትዮጵያዉያን ማህበራዊ መስተጋብር እንዴት ይመለስ?

የኢትዮጵያ መንግስትና ህወሓት እርቅ ሲፈፅሙ በጦርነት ዉስጥ የነበረዉ ማኅበረሰብ እፎይ ይበል እንጂ ማኅበረሰቡ ለዘመናት አብሮት ከኖረዉ ህዝብ ጋር አሁንም እንደተራራቀ ነዉ። የሁለት ዓመቱ የእርስ በርስ ጦርነት በማኅበራዊ መስተጋብሩ ላይ ከፍተኛ ጠባሳን ጥሎ ነዉ ያለፈዉ። በህብረተሰቡ ውስጥ እውነተኛ እርቅና ይቅርታ እንዲመጣ ምን መደረግ አለበት?
1/15/202340 minutes, 44 seconds
Episode Artwork

ወጣቶቹን የሚያረግፈው ስደት፦ ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አፍሪካ

በጥቅምት እና ሕዳር ወራት ከ50 በላይ የኢትዮጵያውያን አስከሬኖች በማላዊ እና በዛምቢያ ተገኝተዋል። በየአገራቱ የተካሔዱ ምርመራዎች በመንገድ ላይ ሞተው የተገኙት ኢትዮጵያውያን ወደ ደቡብ አፍሪካ በማምራት ላይ እንደነበሩ የሚጠቁሙ ናቸው። ይኸ ውይይት የጉዞ መስመሩን ጠባይ፣ የስደቱን ገፊ ምክንያቶች እና የኢትዮጵያውያኑን መከራ የሚመረምር ነው።
1/3/202341 minutes, 44 seconds
Episode Artwork

ውይይት፤ ወጣቶቹን የሚያረግፈው ስደት፦ ከደቡብ ኢትዮጵያ ወደ ደቡብ አፍሪካ

1/1/202341 minutes, 44 seconds
Episode Artwork

የመገናኛ አውታሮች ሁለት ገጽታ በኢትዮጵያ

በኢትዮጵያ አንዳንድ የመገናኛ አውታሮች በጥቃት አድራሾች ሊድበሰበሱና ሊዳፈኑ ይችሉ የነበሩ የግፍ ተግባራትን፣ ግድያዎችን፤ አላግባብ እስሮችንና ሌሎች በደሎችን በማጋለጥ በተለይ የማኅበራዊ የመገናኛ አውታሮች ከፍተኛ አስተዋጽዖ ሲያበረክቱ ይታያል። ግድያ፤ ጭፍጨፋና ማፈናቀሎችን የሚያስፋፉ አደገኛ መረጃዎችን በማሰራጨት በብርቱ የሚተቹም አሉ። ውይይት
12/25/202240 minutes
Episode Artwork

ተወያዮች «በመንግሥት በኩል ያለዉ ዝምታ ምን እንደሆነ ለማወቅ ተቸግረናል።»

12/11/202242 minutes, 10 seconds
Episode Artwork

ዉይይት፤ ስንቱ ሲሞት ነዉ በኢትዮጵያ መግደልና መገዳደል የሚቆመዉ?

ሰሜን ኢትዮጵያ ይካሄድ የነበረዉ ጦርነት በሰላም ስምምነት መቆሙ የፈጠረዉ ስሜት ሳይቀዘቅዝ፤ ምዕራብ ኢትዮጵያ ዉስጥ ብሔርን መሰረት ያደረገዉ ግጭትና ጥቃት አስከፊ ደረጃ ላይ ደርሷል። በተለያዩ የወለጋ ዘኖች አካባቢ በሚኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ ባነጣጠረዉ ጥቃት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለው፤ በሺዎች የሚቆጠሩ በየአካባቢዉ እየተሰቃዩ ነዉ።
12/11/202242 minutes, 10 seconds
Episode Artwork

ውይይት፦ የኢትዮጵያ "ደህንነት ተግዳሮት" የተባለው "የተደራጀ ሌብነት" በኮሚቴ ሥራ ይቆማል?

12/4/202240 minutes, 28 seconds
Episode Artwork

የኢትዮጵያ "ደህንነት ተግዳሮት" የተባለው "የተደራጀ ሌብነት" በኮሚቴ ሥራ ይቆማል?

የኢትዮጵያ መንግሥት የፋይናንስ ደህንነት አገልግሎት ኃላፊ እና የብሔራዊ መረጃና ደሕንነት አገልግሎት ባልደረቦችን ጨምሮ በሙስና የተጠረጠሩ ሹማምንት በቁጥጥር ሥር ማዋሉን አስታውቋል። በጸረ-ሙስና ዘመቻው የጸጥታ፣ የፍትኅና የመሬት አስተዳደር ቅድሚያ ተሰጥቷቸዋል። የጸረ ሙስና ብሔራዊ ኮሚቴ የአገር ደህንነት ሥጋት የተባለውን ሙስና ማቆም ይችላል?
12/4/202240 minutes, 28 seconds
Episode Artwork

የህዳር 11 ቀን 2015 ዓ/ም የእንወያይ ዝግጅት

11/20/202240 minutes, 50 seconds
Episode Artwork

የትጥቅ መፍታት እና የመከላከያ ያልሆኑ ኃይሎች ከክልሉ መውጣት አንድምታ

ግጭት ጦርነቱ ቆሞ ሰላም እንዲወርድ ችግሮች በንግግር ይፈቱ ዘንድ ይወተውቱ የነበሩቱ አሁን ስምምነቱን በደስታ ከመቀበል ባሻገር አሁን ጥያቄው ስምምነቱ በእርግጥ ተግባራዊ ይሆን የሚለው ሆኗል።
11/20/202240 minutes, 50 seconds
Episode Artwork

ቃለ መጠይቅ ከፕሮፌሰር መስፍን አርአያ ጋር

11/15/202224 minutes, 56 seconds
Episode Artwork

ዘላቂ መፍትኄ የሚሻው የፀጥታ ስጋት በኦሮሚያ ክልል

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ የፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል የሰላም ስምምነት መደረጉን በርካቶች በበጎ ጎኑ ቢቀበሉትም በመላ ሀገሪቱ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ግን ሌሎች ግጭቶች ባሉባቸው አካባቢዎችም ሰላማዊ መፍትኄ እንዲፈለግ ተደጋጋሚ ጥሪ ይሰማል። በተለይ በኦሮሚያ ክልል ያለው የፀጥታ ችግር እጅግ መባባሱ መነጋገሪያ ኾኗል።
11/13/202238 minutes, 7 seconds
Episode Artwork

በኦሮሚያ ክልል የፀጥታው ችግር ከሰሞኑ ተባብሶ ቀጥሏል

11/13/202238 minutes, 7 seconds
Episode Artwork

የሰላም ስምምነቱ

11/6/202236 minutes, 28 seconds
Episode Artwork

ዉይይት፤ በጦርነት ዛቻና ፕሮፖጋንዳ የታጀበዉ የሰላም ድርድር

„የሰላም ንግግሩ ጠረቤዛ ጠባብ ነዉ። ችግሩ በጦርነት ላይፈታ ለምን ሰዉ ያልቃል፤ አገር ይወድማል? ህብረተሰቡ መራብ፤ መገደል፤ ተስፋ መቁረጥ ይብቃን ብሎ መንቃት አለበት ። እነዚህ ቡድኖች የሚወዛገቡበት ችግር የጎበዝ አለቃ አይነት ክርክር ነዉ። ከዉይይቱ በፊት ተኩስ ማቆም ግዳጅ መሆን ነበረበት። የኤርትራ ሰራዊት በቀላሉ ይወጣልስ?“
10/30/202240 minutes, 43 seconds
Episode Artwork

ዉይይት፤ በጦርነት ዛቻና ፕሮፖጋንዳ የታጀበዉ የሰላም ድርድር

10/30/202240 minutes, 43 seconds
Episode Artwork

የ12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሂደት ችግሮችና አስተምህሮቱ

10/23/202239 minutes, 33 seconds
Episode Artwork

የ2014 ዓ.ም. 12ተኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ሂደት ችግሮችና አስተምህሮቱ

ባለፈው ሳምንት ፣በአራት የአማራ ክልል ዩኒቨርስቲዎች ለመፈተን ከሄዱ ተማሪዎች ፈተናውን ጥለው ወጡ የተባሉ ከ12 ሺህ በላይ ተማሪዎች፣ዳግም ፈተና እንዳይወስዱ ትምሕርት ሚኒስቴር መወሰኑ ሲያነጋግር ከርሟል። የፈተናው ሂደት ያጋጠሙ ችግሮችና አስተምህሮቱ የዚህ ውይይት ትኩረት ነው።
10/23/202239 minutes, 33 seconds
Episode Artwork

ድርድሩ መክሸፍ፣ ዉጊያዉና የድርድር ባሕል

10/16/202241 minutes, 59 seconds
Episode Artwork

የዋጋ ንረት፦ ገፊ ምክንያቶች፣ የብሔራዊ ባንክ እርምጃ እና የወደፊት ሥጋቶች

10/9/202239 minutes, 21 seconds
Episode Artwork

የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት እና የጎረቤት ሃገራት ሚና

ሰላማዊ መፍትሔ ያጣው የሰሜን ኢትዮጵያውን ጦርነት ጨምሮ ሀገሪቱን ለሚያብጠው አለመረጋጋት በጦርነቱ በቀጥታ በመሳተፍም ሆነ ግጭቶች እንዲባባሱ የጎረቤት ሃገራት ሚና እንዳላቸው በስም እየተጠቀሰ ሲነገር ይሰማል። ድርድን በመደገፍ ለሰላም ንግግሩ ቁርጠኛ አቋም እንዳላቸው የገለጹ የጎረቤት ሃገራት እንዳሉ ስማቸው ይጠቀሳል።
10/2/202238 minutes, 37 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፦ ያለመተማመን፤ የሰላም ውይይት እንቅፋት

9/25/202239 minutes, 17 seconds
Episode Artwork

«ማጠንጠኛው ተጠያቂነት ነው» የእንወያይ መሰናዶ

9/11/202239 minutes, 41 seconds
Episode Artwork

ኢትዮጵያ፦ በግጭት ጦርነቱ የሰላማዊ ዜጎች መብት ጥሰት

ኢትዮጵያ ውስጥ በግጭት ጦርነቱ የተነሳ ሰላማዊ ዜጎች በተለያዩ ቦታዎች በተደጋጋሚ አሰቃቂ በሆነ መልኩ ሲገደሉ፤ ጥቃት ሲደርስባቸው እና በገፍ ሲፈናቀሉ ይታያል። በግጭት ጦርነቶች ወቅት የሰላማዊ ዜጎች የሰብአዊ መብት አጠባበቅ» ምን ይመስላል? የሰብአዊ መብት ተሟጋች ባለሞያዎችን ለውይይት ጋብዘናል። ሙሉው ውይይት ከታች በድምፅ ይገኛል።
9/11/202239 minutes, 41 seconds
Episode Artwork

የኢትዮጵያ ፖለቲካ ክሽፈትና ዳግም ያገረሸዉ ጦርነት

9/4/202239 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፦ ኢትዮጵያ ሌላ ዙር ጦርነት የሚሸከም ጫንቃ ይኖራታል?

8/28/202241 minutes, 45 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፤ የክልልና የክላስተር አደረጃጀት ተግዳሮት ወይስ መፍትሄ?

«የደቡብ ክልል በፊትም የተዋቀረበት መንገድ ችግር ያለበት ነዉ። ህዝብ ተወያይቶበት እና አምኖበት የተቀበለዉ ሳይሆን የተጫነበት ነዉ። የፖለቲካ ባህላችን መቀየር አለበት። አሁን በደቡብ ክልል ይደረግ የተባለዉ አደረጃጀት እና ህዝቡ የሚፈልገዉ አደረጃጀት ለየቅል ነዉ። ግጭትና ዉዝግብን አስከትሏል።ህዝብ ሕገ መንግሥታዊ መብቱ ሊከበርለት ይገባል።»
8/21/202241 minutes, 1 second
Episode Artwork

ተወያዮች «የችግሮቹ ሁሉ ምንጭ ሕገ መንግሥቱ ነዉ። ልንከልሰዉ ይገባል»

8/21/202241 minutes, 1 second
Episode Artwork

እንወያይ፦ የጉራጌ ዞን ምክር ቤት ውሳኔ እና የሚጠበቁት አዳዲስ ክልሎች ጉዳይ

8/14/202241 minutes, 3 seconds
Episode Artwork

እንወያይ

7/31/202240 minutes, 14 seconds
Episode Artwork

«የሙስናዉ ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሻቀበ ነዉ...»

7/24/202237 minutes, 50 seconds
Episode Artwork

የነዳጅ ድጎማ ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብት ምን ይዞ ይመጣል?

የነዳጅ ድጎማ ብቻውን ኢትዮጵያን ከ146.6 ቢሊዮን ብር በላይ ለሆነ የበጀት ጉድለት እንደዳረጋት መንግሥት አስታውቋል። የነዳጅ ድጎማውን በሒደት የሚያነሳ ማሻሻያ መንግሥት ገቢራዊ እያደረገ ነው። ማሻሻያው ጦርነት፣ ድርቅና የዋጋ ግሽበት ለተጫነው ምጣኔ ሐብት ምን ይዞ ይመጣል? ደሐውን የማኅበረሰብ ክፍል ከዳፋው እንዴት መታደግ ይቻላል?
7/17/202239 minutes, 48 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፦ የነዳጅ ድጎማ ማሻሻያ ለኢትዮጵያ ምጣኔ ሐብት ምን ይዞ ይመጣል?

7/17/202239 minutes, 48 seconds
Episode Artwork

መንግሥት ጭፍጨፋውን ማስቆም ለምን ተሳነው?

በኢትዮጵያ በተለይ ባለፉት አራት ዓመታት እዚህም እዚያም ኼድ መለስ ይል የነበረው ብሔርን መሰረት ያደረገ ግድያ እና ጭፍጨፋ ከሰሞኑ ከፍተኛ ደረጃ መድረሱ ብርቱ ቁጣ ቀስቅሷል። ባለፉት ቀናት ኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ውስጥ በአብዛኛው የአማራ ብሔር ተወላጆች በተከታታይ ከፍተኛ ጭፍጨፋ ተፈጽሞባቸዋል። ሙሉ ውይይቱ በድምፅ ከታች ይገኛል።
7/10/202239 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

ዳግም ሞት፤ ዳግም ሐዘን እንዳይከሰትስ ምን ይደረግ?

7/10/202239 minutes, 47 seconds
Episode Artwork

«በብሔር ተኮሩ ግድያ እንድንፈራና እና እንድንባንን እየተደረግን ነዉ»

7/3/202241 minutes, 20 seconds
Episode Artwork

እንወያይ

6/19/202239 minutes, 58 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፦ የኢትዮጵያ መንግሥትንና ህወሓትን የማሸማገል ጥረት

6/12/202231 minutes, 15 seconds
Episode Artwork

እንወያይ፦ የጋዜጠኞች እና የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች እስር በኢትዮጵያ

6/5/202230 minutes, 56 seconds