10/20/2024 • 38 minutes, 16 seconds የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአማራ ክልል ይካሄዳል ያሉት «የዘፈቀደ የጅምላ እሥር»
ኢሰመኮና አምነስቲ ኢንተርናሽናል በአማራ ክልል በመካሄድ ላይ ያሉት «የዘፈቀደና የጅምላ» ያሏቸው እስሮች እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል። የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት እና የአማራ ክልል የህዝብ ግንኙነት ሃላፊዎች በክልሉ ጽንፈኛ ባሏቸው ኃይላት ላይ የተ ወሰደው «ሕግ የማስከበር ተግባር ነው» ሲሉ እርምጃው እንደሚቀጥልም ተናግረዋል።
10/13/2024 • 40 minutes, 53 seconds የሰብዓ ዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች በአማራ ክልል ይካሄዳል ያሉት «የዘፈቀደ የጅምላ እሥር»
10/13/2024 • 40 minutes, 53 seconds እንወያይ፤ ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት ዛሬ በኢትዮጵያ እንዴት ይገመገማል?
ኢትዮጵያ ውስጥ ከስድስት ዓመታት በፊት የመናገር ነጻነት ከፍተኛ መሻሻል የታየበት ዓመት ለመሆን በቅቶ ነበር። ይሁንና ሀገራዊ ፖለቲካዊና በኢኮኖሚያዊ ጉዳዮች ላይ መረጃ የሚያቀርቡ ጋዜጠኞ፤ ትንታኔ የሚሰጡ የፖለቲካ ተንታኞች፤ ብሎም የኪነጥበብ ባለሞያዎች ጫና ላይ እየደረሰ መሆኑን የሰብዓዊ መብት ተከራካሪዎች በየጊዜዉ መግለጫ ያወጣሉ።
10/6/2024 • 40 minutes, 55 seconds ለመንግስት ሰራተኞች የታሰበው የደሞዝ ጭማሪ ምን ያህል ይደጉማል ?
9/29/2024 • 41 minutes, 42 seconds የደሞዝ ጭማሪው «ሳይመጣ የሄደ ተስፋ» ወይስ ደጓሚ ?
ገና ለገና የደሞዝ ጭማሪ ሊደረግ ነው በሚል በተለይ በመሰረታዊ የፍጆታ ቁሳቁሶች ላይ ተከታታይነት ያለው ጭማሪ እየታየ መሆኑን ሸማቾች ይናገራሉ ። ይህ ደግሞ የሰራተኛውን የኑሮ ውድነት ለመቋቋም ይደግፋል ተብሎ ተስፋ የተጣለበት የደሞዝ ጭማሪ ተስፋ እንዳያመነምን ያሰጋል ።
9/29/2024 • 41 minutes, 42 seconds ውይይት፤እያሽቆለቆለ ለመጣው የተማሪዎች ውጤት እና የትምህርት ጥራት መፍትሄ ይኖረው ይሆን?
9/22/2024 • 35 minutes, 51 seconds ውይይት፤እያሽቆለቆለ ለመጣው የተማሪዎች ውጤት እና የትምህርት ጥራት መፍትሄ ይኖረው ይሆን?
በኢትዮጵያ ባለፉት ተከታታይ ሶስት ዓመታት በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ላይ እየተመዘገበ ያለው ውጤት ብዙዎችን እያሳሰበ ነው። በስርዓተ ትምህርቱ ፣በትምህርት ጥራት እና አሰጣጥ ላይም ጥያቄ እንዲነሳ እያደረገ ነው። ታዲያ የችግሩ መንስኤ ምንድነው? ተማሪዎች መምህራን ወይስ ስርዓተ ትምህርቱ?መፍትሄውስ?
9/22/2024 • 35 minutes, 51 seconds ዉይይት፣ የኢትዮጵያ፣ የሶማሊያና የግብፅ መዛዛት እንደቀጠለ ነዉ።ከእንግዲሕስ?
9/15/2024 • 41 minutes, 23 seconds የኢትዮጵያን ሴቶች እና ሕጻናት ከአሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃት ማን ይታደጋቸዋል?
በኢትዮጵያ ወሲባዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሕጻናት እና ሴቶች ፍትኅ እንዲያገኙ ሲደረግ የነበረው ውትወታ ምን አሳካ? የሀገሪቱ ተቋማት ተገደው ለተደፈሩ፣ ሕይወታቸውን ለተነጠቁ እና አሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃቶች ለ ተፈጸመባቸው ፍትኅ ለማረጋገጥ ለምን ተሳናቸው? ጾታዊ ጥቃትን ለማስቆም ወንዶች፣ ቤተሰብ፣ ማኅበራዊ ተቋማት? በውይይቱ በኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን የሴቶች፣ የሕፃናት፣ የአካል ጉዳተኞች እና የአረጋውያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሐዋርያ፣ በጾታ ዕኩልነት ላይ በአማካሪነት የሚሠሩት ወይዘሮ አሻም አሳዝነው፤ የጾታ ዕኩልነት አዶቮኬት የሆኑት ርብቃ ዳዊት እና ረዳት ፕሮፌሰር ሱራፌል ወንድሙ ተሳትፈዋል።
9/8/2024 • 42 minutes, 13 seconds የኢትዮጵያን ሴቶች እና ሕጻናት ከአሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃት ማን ይታደጋቸዋል?
በኢትዮጵያ ወሲባዊ ጥቃት የተፈጸመባቸው ሕጻናት እና ሴቶች ፍትኅ እንዲያገኙ ሲደረግ የነበረው ውትወታ ምን አሳካ? የሀገሪቱ ተቋማት ተገደው ለተደፈሩ፣ ሕይወታቸውን ለተነጠቁ እና አሰቃቂ ወሲባዊ ጥቃቶች ለተፈጸመባቸው ፍትኅ ለማረጋገጥ ለምን ተሳናቸው? ጾታዊ ጥቃትን ለማስቆም ወንዶች፣ ቤተሰብ፣ ማኅበራዊ ተቋማት እና መንግሥት ምን ሊያደርጉ ይገባል?
9/8/2024 • 42 minutes, 13 seconds የሰሞኑ ተደጋጋሚ የተፈጥሮ አደጋዎች የበርካቶችን ሕይወት ቀጥፏል
ተደጋጋሚ የተፈጥሮ አደጋዎች ያስከተሉት ጉዳት እና የመከላከል ሥራዎች በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ከሰሞኑ የተከሰቱ ተደጋጋሚ የተፈጥሮ አደጋዎች ለበርካቶች ሞት እና መፈናቀል ሰበብ ሆነዋል ። በጎፋ የመሬት መንሸራተት ከሁለት መቶ አምሳ በላይ ሰዎች መቀጠፋቸው ያጫረው የሐዘን ጠባሳ ገና አልጠገገም ። ሦስት ምሑራን እና ባለሞያዎች የተሳተፉበትን ሙሉውን ውይይት በድምፅ ማዕቀፉ መከታተል ይቻላል ።
"ህወሓት ፈረሰ ማለት የፕሪቶሪያ ስምምነት ፈረሰ ማለት ነው የሚል አባባል በውሉ የተካተቱ የትግራይ ባለድርሻ አካላትንና ከፍተኛ መስዋዕትነት የከፈሉትን የትግራይ የጸጥታ ኃይሎች መስዋዕትነት መናቅ ነው ብዬ አስባለሁ"
8/25/2024 • 41 minutes, 54 seconds ሁለተኛ ዓመቱን የያዘው የአማራ ክልል ጦርነት ማብቂያው የት ነው?
አንድ ዓመት ባለፈው የአማራ ክልል ጦርነት ከሁለቱም ወገን ፣ቁጥሩ በውል ያልታወቀ የሰዎች ሕይወት እንደጠፋ በርካታ ንብረትም እንደወደመ በሰላማዊ ሰዎች ላይም የተለያዩ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች መፈጸማቸውን ሴቶችንም የወሲብ ጥቃቶች ሰለባ ማድረጉን የሀገር ውስጥም ሆነ የውጭ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችባወጧቸው ዘገባዎች አስታውቀዋል።
8/18/2024 • 41 minutes, 38 seconds ሁለተኛ ዓመቱን የያዘው የአማራ ክልል ጦርነት ማብቂያው የት ነው?
8/17/2024 • 41 minutes, 38 seconds «የኤኮኖሚ ማሻሻያው» የብር አቅም መዳከም ለብዙኀኑ ሕዝብ ምን ማለት ይሆን?
8/11/2024 • 40 minutes, 58 seconds እንወያይ፤ የጠቅላይ ሚኒስትሩና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዉይይት ፋይዳዉ ምን ይሆን?
ጠ/ሚኒስትሩና ተቃዋሚዎች ለዉይይት መቀመጣቸዉ በይሁንታ ቢታይም፤ ለሃገሪቱ መፍትሄ ሊያስገኝ ይገባል። በቅድምያ በሃገሪቱ የሚሰማዉን የጥይት ድምፅ ፀጥ ሊያሰኝ፤ ነፍጥ ያነገቡትን ጨምሮ በሃገሪቱ ሁሉን አካታች ዉይይት እንዲጀመር ሊያደርግ ይገባል። የፖለቲካ ምህዳሩ ሊሰፋ እና የታሰሩ ፖለቲከኞች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊፈቱ ይገባል።
8/4/2024 • 42 minutes, 16 seconds የጠቅላይ ሚኒስትሩና የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዉይይት ምን ፋይዳ ይኖረዉ ይሆን?
8/4/2024 • 42 minutes, 16 seconds ውይይት፦ የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ላይ ይበረታል?
የኢትዮጵያ መንግሥት ተግባራዊ የሚያደርገው የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር አካል የሆኑ የተለያዩ አዋጆች ባለፉት ወራት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ጸድቀዋል። ለመሆኑ የኤኮኖሚ ማሻሻያው የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ጫንቃ ላይ ይወድቃል? በኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሚና ምንድነው? በዚህ ውይይት የገንዘብ አስተተዳደር ባለሙያው ዶክተር አብዱልመናን መሐመድ፣ በዓለም አቀፍ ተቋም ውስጥ ከፍተኛ ተመራማሪ ሆነው በመ ሥራት ላይ የሚገኙት ዶክተር ቀልቤሳ መገርሳ እና በዩናይትድ ኪንግደም ብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ ሥር በሚገኘው ፔሪቮሊ አፍሪካ ጥናት ማዕከል ተመራማሪው ዶክተር ኢዮብ ባልቻ ተሳትፈዋል።
7/28/2024 • 41 minutes, 26 seconds የኢትዮጵያ የኤኮኖሚ ማሻሻያ መርሐ-ግብር የሚያስከፍለው ዋጋ በማን ላይ ይበረታል?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ “በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሪ ተመን ሥርዓት” ተግባራዊ ልታደርግ እንደሆነ ገልጸዋል። የኤኮኖሚ ማሻሻያ አካል የሆነው ውሳኔ የብርን የመግዛት አቅም በከፍተኛ መጠን ያዳክማል። ይኸ ውይይት የኤኮኖሚ ማሻሻያው የሚያስከፍለው ዋጋ ማን ላይ ይበረታል? ሲል ያጠይቃል
7/28/2024 • 41 minutes, 26 seconds «ዕገታ» ከመንግስት ቁጥጥር ውጭ ሆኖ ወይስ በቸልተኝነት እዚህ ደረሰ?
አሁን አሁን ግጭት ጦርነት በሚደረግባቸውም ይሁን አንጻራዊ ሰላም ባለባቸው አካባቢዎች ለዜጎች የየዕለት ስጋት ሆኖ የቀጠለው እና ምናልባትም ችግሩ በዚህ ከቀጠለ በሀገር ህልውና ላይ የሚያስከትለው መዘዝ አሳሳቢ እየሆነ የመጣው የሰላማዊ ሰዎች ዕገታ ጉዳይ ነው ።
7/21/2024 • 45 minutes, 8 seconds እንወያይ፤ ሰብዓዊ መብት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቶች ተግዳሮቶች በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መሆኑን በተለያዩ ተቋማት የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ። በሌላ በኩል ለሰብዓዊ መብት የሚታገሉ እና ችግሩ መፍትሄ እንዲያገኝ የሚወተውቱ በሰብዓዊ መብት ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችም በስራቸው ሳቢያ ከመንግስት ጫና እና እንግልት እየጠነከረባቸው መምጣቱን እየገለፁ ነው።
7/14/2024 • 40 minutes, 52 seconds እንወያይ፤ የሰብዓዊ መብት እና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ተግዳሮቶች በኢትዮጵያ
7/14/2024 • 40 minutes, 52 seconds 7/7/2024 • 40 minutes, 39 seconds እንወያይ፣ የኢትዮጵያዉን ተፈናቃዮች ፈተና፣ የለጋሾች ዳተኝነት
7/1/2024 • 40 minutes, 51 seconds እንወያይ፤ በሴቶች ላይ እየደረሰ ያለ ጥቃትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ
በኢትዮጵያ ዉስጥ ግጭትና ጦርነት ሴቶች ይበልጥ ግፍ ደርሶባቸዋል፤ እየደረሰባቸዉም ነዉ። ጾታዊ ጥቃትና ማዋከቦችን ለመግታት ከመንግሥትም ሆነ ከሴቶች ማህበራት በቂ ድጋፍ አልታየም ይባላል። እንደሚታወቀዉ ሴት እናት፤ እህት፤ ሚስት፤ ልጅ ናት። ለኢትዮጵያዉያን ደግሞ አገርም ናት። ግን ሴቶች ላይ እየደረሰ ያለዉ ሰቆቃ ለምን ትኩረት አልተሰጠዉም?
6/23/2024 • 41 minutes, 31 seconds እንወያይ፤ አሳሳቢዉ በሴቶች ላይ የሚሰነዘር ጥቃትና የሰብዓዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ
6/23/2024 • 41 minutes, 31 seconds የኢትዮጵያ የምርጫ ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ማሻሻያ አዋጅና ፋይዳው
ማሻሻያውን የደገፉ እርምጃው በኢትዮጵያ የትጥቅ ትግል የሚያካሂዱ ቡድኖች ወደ ሰላማዊ ትግል እንዲገቡ የሚያበረታታ ሲሉ የማሻሻያው ተቃዋሚዎች ደግሞ ወደ አማራና አፋር ክልሎች ተስፋፍቶ በነበረው በትግራዩ ጦርነት የተፈጸሙ ወንጀሎች ፍትህ ሳያገኙ ተድበስብሰበው እንዲቀሩ የሚያደርግ ሲሉ ይቃወማሉ።
6/16/2024 • 36 minutes, 53 seconds የኢትዮጵያ የምርጫ ፣የፖለቲካ ፓርቲዎች ምዝገባና የምርጫ ስነ ምግባር ማሻሻያ አዋጅና ፋይዳው
6/14/2024 • 36 minutes, 53 seconds ግጭት ጦርነት ያጠላበት ሀገራዊ ምክክር በኢትዮጵያ
6/9/2024 • 39 minutes, 31 seconds ውይይት፦ የመንግሥት 47 ዩኒቨርሲቲዎች ሚና ከኢትዮጵያ ፍላጎት ምን ያህል የተጣጣመ ነው?
የኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያስተዳድራቸው ዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ባለፉት ሦስት አስር ዓመታት ገደማ ከሁለት ወደ አርባ ሰባት አድጓል። ባለሙያዎች በተማሪዎች ቁጥር እና በመሠረተ ልማት ግንባታ ረገድ ዕድገት ቢኖርም ውጤቱ ለመንግሥትም ሆነ ለዜጎች አመርቂ አይደለም ሲሉ ይሞግታሉ። በዚህ ውይይት በኢትዮጵያ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት ልማት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ኮራ ጡሹኔ፣ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ የምርምር እና የኅትመት ዳይሬክተር ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ እና በደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ሰይፈ ታደለ ኪዳኔ ተሳትፈዋል።
6/2/2024 • 40 minutes, 59 seconds የመንግሥት 47 ዩኒቨርሲቲዎች ሚና ከኢትዮጵያ ፍላጎት ምን ያህል የተጣጣመ ነው?
አየር መንገድ፣ መከላከያ ሠራዊት እና ፌድራል ፖሊስ ያቋቋሟቸውን ሳይጨምር ኢትዮጵያ 47 የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች አሏት። የዩኒቨርሲቲዎች ቁጥር ሲጨምር ሀገሪቱ ምን አተረፈች? የትምህርት ተቋማቱ ከገዢው ፓርቲ ምን ያክል ነጻ ናቸው? በዚህ ውይይት አቶ ኮራ ጡሹኔ፣ ዶክተር ኤፍሬም ተክሌ እና ዶክተር ሰይፈ ታደለ ተሳትፈዋል።
6/2/2024 • 40 minutes, 59 seconds ከ33 ዓመታት በኋላ የዩናይትድ ስቴትስ ሚና በኢትዮጵያ ፖለቲካ
5/26/2024 • 39 minutes, 25 seconds የኢትዮጵያ የግጭት አዙሪትና የአሜሪካ የፖሊሲ ንግግር
ዩናይትድ ስቴትስ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ግጭት በተመለከተ ከሦስት ዐሥርተ ዓመታት ወዲህ ለየት ያለ የፖሊሲ አቋሙዋን ባለፈው ሳምንት ረቡዕ ከአዲስ አበባ ዐሳውቃለች ። ጉዳዩ 33 ዓመት ወደ ኋላ ወደ ለንደኑ ስብሰባም ይወስደናል ። እንዴት? መልሱን ከሳምንታዊው የውይይት መድረክ ያድምጡ ።
5/26/2024 • 39 minutes, 25 seconds የጠቅላይ ሚንስትሩ «የሰላም ጥሪ » ምን አይነት ምላሽ ያግኝ ?
5/19/2024 • 40 minutes, 58 seconds የጠቅላይ ሚንስትሩ የሰላም ጥሪ ፤ ሰላማዊ ምላሽ እንዴት ያግኝ?
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ ባለፈው ሳምንታት መንግስታቸው ከታጣቂዎች ጋር ብርቱ ፍልሚያ እያደረገ ወደ ሚገኝባቸው የኦሮሚያ እና አማራ ክልል አካባቢዎች አቅንተዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ በሁለቱም አካባቢዎች በጥቅሉ ጦርነት እንዲቆም ብሎም «በወንድማማቾች መካከል የሚደረግ መገዳደልም እንዲያበቃ » ጥሪ አስተላልፈዋል።
5/19/2024 • 40 minutes, 58 seconds የሁለቱ ወገኖች የስልጣን ሽኩቻ ወዴት ያመራ ይሁን?
በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደርና በህወሐት መካከል ያለው የስላጣን ሽኩቻ ተካሮ አንዱ በአንዱ ላይ የስም ማጥፋት ዘመቻው በግላጭ እየተካሄደ ከመሆኑም አልፎ ጎራ ለይተው እስከመገዳደል እንዳይደረስና የተገኘው አንጻራዊ ሰላም እንዳይደፈርስ ብዙዎቹ የክልሉ ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
5/12/2024 • 40 minutes, 51 seconds እንወያይ፤ ኢትዮጵያ ሌላ ዙር ግጭትን ለመሸከም ጫንቃዉ አላት?
ትግራይና አማራ ክልል በሚወዛገቡባቸዉ አካባቢዎች የተቀ ሰቀሰዉን ዉጥረት እንዴት አያችሁት? ምንስ ተሰማችሁ? ከየትኛዉም ወገን ይሁን ያ ሁሉ ህዝብ ካለቀ እና ንብረት ከወደመ በኋላ በፕሪቶርያዉ ስምምነት ሰላም ይሰፍናል ተብሎ ሲጠነቅ ዳግም ወደ ሌላ ዉጥረት እየተገባ ነዉ? ይህን ዉጥረት ህዝቡና ሃገሪቱ መሸከም ይችላሉ? ምንድን ነዉ መደረግ ያለበት?
4/28/2024 • 45 minutes, 49 seconds አደገኛው የኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰት
ወደ ሳዑዲ አረብያ ለመሄድ ጉዞ የጀመሩ 38 ኢትዮጵያውያን ጅቡቲ ድንበር አቅራቢያ የተጫኑበት ጀልባ ሰጥሞ ባለፈው ሳምንት ሞተዋል። በዚሁ ሳምንት ነበር ሳዑዲ አረብያ ውስጥ ችግር ላይ የወደቁ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ጥረት የቀጠለው።በአሁኑ ጊዜ በአደገኛ ጉዞ መላልሰው ወደ መካከለኛው ምሥራቅና ወደ ደቡብ አፍሪቃ የሚሄዱ ጥቂት አይባሉም።
4/21/2024 • 42 minutes, 10 seconds አደገኛው የኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ፍልሰት
4/21/2024 • 42 minutes, 10 seconds በኢትዮጵያ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ዕጣ ፈንታ
4/14/2024 • 39 minutes, 29 seconds ኢትዮጵያ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስድስት የሥልጣን ዓመታት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን የያዙበት ስድስተኛ ዓመት ደጋፊዎቻቸው በሰልፍ ተቃዋሚዎቻቸው በትችት አስበውታል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ጆን አሕመድ፣ ከሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ሙከርም ሚፍታህ፣ ከጁሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ዶክተር ሰይፈ ታደለ የተሳተፉበት ውይይት ለመሆኑ ዐቢይ ምን አሳክተው ምን አጎደሉ? ሲል ያጠይቃል
4/7/2024 • 43 minutes, 21 seconds እንወያይ፦ ኢትዮጵያ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስድስት የሥልጣን ዓመታት
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን የያዙበት ስድስተኛ ዓመት ደጋፊዎቻቸው በሰልፍ ተቃዋሚዎቻቸው በትችት አስበውታል። የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ጆን አሕመድ፣ በሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊሲ ጥናት ረዳት ፕሮፌሰር ሙከርም ሚፍታህ በደቡብ አፍሪካ ጁሐንስበርግ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ ዶክተር ሰይፈ ታደለ የተሳተፉበት ውይይት በስድስት ዓመታት ዐቢይ ምን አሳክተው ምን አጎደሉ? ሲል ያጠይቃል።
4/6/2024 • 43 minutes, 21 seconds የፊት ለፊቱ ንግግር አንድምታ እና የኢትዮጵያ መሻት
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ የትግራዩ ጦርነት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ከተለያዩ ክልሎች የህዝብ ተወካዮች ጋር በተከታታይ ውይይት እያደረጉ ነው። በየውይይቱ ክልሎቹም ሆኑ የኃይማኖት ተቋማቱ በተናጥል እና የጋራ ወቅታዊ የሃገራዊ ጉዳዮች ላይ ሃሳብ ፣ አስተያየት እና ጥቆማ ሰጥተዋል፤ አፋጣኝ ምላሽ ይሻሉ ያሏቸውንም ጥያቄዎች አንስተዋል።
3/24/2024 • 41 minutes, 31 seconds ግጭት ጦርነት እንዲቆም ፤ ፖለቲካዊ ንግግር በአፋጣኝ እንዲጀመር ከተወያዮች ጥያቄ ቀርቧል
3/24/2024 • 41 minutes, 31 seconds ከፕሪሪቶሪያ ስምምነት አፈጻጸም ምን እንማር?
አፈራራሚዎቹ በግጭቱ የተጎዱትን መልሶ ማቋቋምን ጨምሮ ተጎጂዎችን ያማከለ የሽግግር የፍትሕ ሂደት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን የስምምነቱ ፈራሚዎች መገናኘታቸውን እንዲቀጥሉ ጥሪ አድርገዋል።እነዚህ የበለፀጉ እንዲሁም በአማራ፣ በኦሮሚያ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ክልሎች የተከሰቱት ቀውሶች በተመሳሳይ ቁርጠኝነት ችግሩ እንዲፈታ ጥሪ አቅርበዋል።
3/17/2024 • 40 minutes, 53 seconds ዉይይት፣ የኦሮሚያና የአማራ ክልል ግጭቶች ለምን አይቆሙም?
የተለያዩ መገናኛ ዘዴ ዎች፣የመብት ተሟጋቾች፣የርዳታ ድርጅት ሠራተኞች ከሁሉም በላይ የየአካባቢዉ ነዋሪዎች እንደሚሉት በየግጭት፣ ዉጊያ ጥቃቶቹ የሚያልቅ፣ የሚቆስል፣የሚፈናቀለዉ ሕዝብና የምትደፈረዉ ሴት ቁጥር እየጨመረ ነዉ።
3/10/2024 • 40 minutes, 24 seconds ዉይይት፣ በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች የሚደረጉት ግጭቶች ለምን አይቆሙም?
3/10/2024 • 40 minutes, 24 seconds አሳሳቢው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ በአማራ ክልል
ኢሰመኮ በቅርቡ በመርዓዊ ከተማ በሲቭሎች ላይ በመከላከያ ሠራዊት ከሕግ ውጭ ግድያዎች መፈጸሙን ለማወቅ መቻሉን አስታውቋል። በመከላከያ ሠራዊት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ግጭት እንደነበር ያረጋገጠው መንግሥት የመከላከያ ኃይሉ የትኛውንም ዓይነት ሲቪል ዒላማ አላደረገም ሲል አስተባብሏል።
2/25/2024 • 39 minutes, 30 seconds አሳሳቢው የሰላማዊ ሰዎች ግድያ በአማራ ክልል
2/25/2024 • 39 minutes, 30 seconds 50 ዓመታት፦ የኢትዮጵያ አብዮት ውርስ ምንድነው?
የአጼ ኃይለሥላሴን ዘውዳዊ መንግሥት ከፍጻሜ ያደረሰው የኢትዮጵያ አብዮት 50 ዓመታት ሞላው። የካቲት 1966 “ፈነዳ” የሚባለው አብዮት “መሬት ላራሹ” የተፈከረበት፣ የብሔሮች እና የሐይማኖት ዕኩልነት የተጠየ ቀበት ነው። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ዶ/ር መላኩ ተገኝ እና ዶ/ር ኢዮብ ባልቻ የተሳተፉበት ውይይት የአብዮቱ ውርስ ምንድነው? ሲል ያጠይቃል።
2/18/2024 • 40 minutes, 45 seconds 50 ዓመታት፦ የኢትዮጵያ አብዮት ውርስ ምንድነው?
የአጼ ኃይለሥላሴ ዘውዳዊ መንግሥትን በማስወገድ የፊውዳላዊ ሥርዓትን ከፍጻሜ ያደረሰው የኢትዮጵያ አብዮት የተቀሰቀሰው ከ50 ዓመታት በፊት ነበር። በየካቲት ወር 1966 “ፈነዳ” የሚባለው አብዮት “መሬት ላራሹ” የተፈከረበት፣ የብሔሮች፣ የሐይማኖት ዕኩልነት የተጠየቀበት ነው። የታክሲ አሽከርካሪዎች፣ ሠራተኞች፣ መምህራን እና ወታደሮች የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንገብ በየፊናቸው በዘውዳዊው መንግሥት ላይ ጫና ያደርጉ ነበር። ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና፣ ዶክተር መላኩ ተገኝ እና ዶክተር ኢዮብ ባልቻ የተሳተፉበት ውይይት የኢትዮጵያ አብዮት ውርስ ምንድነው? ሲል ያጠይቃል።
2/17/2024 • 40 minutes, 45 seconds እንወያይ፤ በአንድ ላይ ቆመው ለኢትዮጵያ ይጮሁ የነበሩ ወገኖች ዛሬ የት ናቸዉ?
2/4/2024 • 43 minutes, 36 seconds እንወያይ፤ የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ሚና ከየት ወዴት?
በዉጭ የሚኖረዉ ኢትዮጵያዊና ትዉልደ ኢትዮጵያዊ (ዲያስፖራ) በኢትዮጵያ ፖለቲካ፤ ኢኮኖሚና ማኅበራዊ እንቅስቃሴ፤ ከፍተኛ ሚናን እንደሚጫወት ይታወቃል። አሁን አሁን ግን አብዛኛዉ ዲያስፖራ በዘላቂ የአገሪቱ ጥቅሞች ላይ አንድ ላይ መቆሙ ቀርቶ፤ ተጻራሪና ግዚያዊ የሆኑ የቡድን ፍላጎቶችን ይዞ በየፊናው ቆሞ መታየቱ የተለመደ ሁኗል። ችግሩ ምን ይሆን?
2/4/2024 • 43 minutes, 36 seconds ዉይይት፣ የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ ስምምነት፣ ድጋፍ፣ተቃዉሞና ዉግዘቱ
በዓባይ ወንዝ ዉኃ አጠቃቀም ሰበብ ከኢትዮጵያ ጋር የምትወዛገበዉ ግብፅ ደግሞ ለዉጊያም እየተጋበዘች ነዉ።የግብፅ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሳሚሕ ሽኩሪ ኢትዮጵያን «የአካባቢዉ ያለመረጋጋት ምንጭ» በማለት ወንጅለዋታል።የሐገሪቱ ፕሬዝደንት የቀድሞዉ ፊልድ ማርሻል አብዱልፈታሕ አልሲሲ በበኩላቸዉ ሶማሊያና ደሕንነቷ ላደጋ ከተጋለጠ ግብፅ ጣልቃ ለመግባት
1/28/2024 • 41 minutes, 2 seconds ዉይይት፣ የኢትዮጵያና የሶማሊላንድ ስምምነት፣ ድጋፍ፣ተቃዉሞና ዉግዘቱ
1/26/2024 • 41 minutes, 2 seconds የኢትዮጵያ የጸጥታ እና የደህንነት ተቋማት ወቅታዊ ሁኔታ
1/21/2024 • 43 minutes, 5 seconds ከውጭና ከሃገር ውስጥ በተሰበሰበ የአገሪቱ ሀብት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አነሳሽነት እየተገነቡ ያሉ የመናፈሻዎችና የቤተመንግስት ግንባታዎች፤ በቀጥታ ከመንግስት ካዝና በቢልዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ ወጪ ተደርጎ የሚካሄዱ የመንግስት መስሪያቤቶች እድሳት አነጋጋሪነታቸው እንደቀጠለ ነው።
1/7/2024 • 40 minutes, 18 seconds ውይይት፦ ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ማዳከም ወይስ…የኢትዮጵያ አጣብቂኝ
ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ባለፉት አራት ዓመታት በባንኮችም ይሁን በጎንዮሽ ገበያው ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። ብር ሲዳከም ለኢትዮጵያ ምን ፈየደ? ለሀገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ሁለተኛ ምዕራፍ ዳጎስ ያለ ማስፈጸሚያ የሚሻው የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ መንግሥት በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሚቀነቀነውን ብርን የማዳከም እርምጃ ሊቀበል ይችላል?
የኢትዮጵያ አጣብቂኝ፦ ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ማዳከም ወይስ…?
ብር ከዶላር አኳያ ያለው የምንዛሪ ተመን ባለፉት አራት ዓመታት በባንኮችም ይሁን በጎንዮሽ ገበያው ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷል። ብር ሲዳከም ለኢትዮጵያ ምን ፈየደ? ለሀገር በቀል የኤኮኖሚ ማሻሻያ ሁለተኛ ምዕራፍ ዳጎስ ያለ ማስፈጸሚያ የሚሻው መንግሥት በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት የሚቀነቀነውን ብርን የማዳከም እርምጃ ሊቀበል ይችላል?
12/17/2023 • 39 minutes, 33 seconds እንወያይ፤ በአማራ ክልል የቀጠለዉ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ማቆምያዉ የት ነዉ?
ለአማራ ክልሉ ሰብዓዊ ቀዉስ ተጠያቂዉ ማን ነዉ? በትግራይ ጦርነት በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተገድለዋል። አሁንም በአማራና በኦሮሚያ ክልል ጦርነቱ ቀጥሏል። መንግሥት ከቀዉስ ማትረፍ ፖሊሲዉን ማቆም አለበት፤ ጠ/ሚኒስትሩ ስልጣን መልቀቅ አለባቸዉ፤ በሃገሪቱ የተኩስ አቁም ታዉጆ ዉይይት መጀመር አለበት» ይላሉ ተወያዮች እርሶስ?። እርሶስ? ይጻፉልን!
12/10/2023 • 43 minutes, 15 seconds 11/26/2023 • 40 minutes, 22 seconds የሰላም ንግግሩ ተስፋ እና የሀገሪቱ መጻኢ ዕጣ ፈንታ
ከወራት ዝምታ በኋላ ተፋላሚ ወገኖች ለሌላ የሰላም ንግግር በታንዛንያዋ የንግድ ከ ተማ ዳሬ ሰላም ተቀምጠዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የሰላም ንግግር እየተደረገ መሆኑን ከሳምንት ዝምታ በኋላ ባለፈው ሐሙስ ነበር ይፋ ያደረገው ። የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ተደራዳሪዎቹ ከመንግስት ተወካዮች ጋር በመነጋገር ላይ መሆናቸውን ቀደም ብሎ ነበር ያስታወቀው።
11/19/2023 • 43 minutes, 41 seconds መንግስት ከኦሮሞ ነጻነት ጦር ጋር የሚያደርገው የሰላም ንግግር ዘላቂ ሰላም ያመጣ ይሆን ?
11/19/2023 • 43 minutes, 41 seconds ከምንም በላይ ሕጻናት፤ ሴቶችና አረጋውያን ተጎጂዎች ናቸው
በሀገር ውስጥ ተፈናቃዮች ላይ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች
11/5/2023 • 36 minutes, 28 seconds በተፈናቃዮች ላይ የሚደርሱ የሰብዓዊ መብቶችት ጥሰቶች
ድንገት ተፈናቅለው በወጡበት የቀሩ ፣በማያውቁትና መጠለያ ሊባሉ በማይችሉ ስፍራዎች ለብዙ ጊዜያት የቆዩ በርካቶች ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ችግሮቻቸው እየተባባሱ እንጂ እየቀነሱ አልሄዱም። በመጠለያ ጣቢያዎች ለከፋ ችግር ከተጋለጡት አብዛኛዎቹ ምርጫ በማጣታቸው ወደ ቀድሞው ቀያቸው ለመመለስ እንደሚፈልጉ ይናገራሉ። ሆኖም የጸጥታ ስጋት አላቸው።
11/5/2023 • 36 minutes, 28 seconds ዉይይት፣ የኢትዮጵያ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ትብብርና አሰራር
10/27/2023 • 39 minutes, 51 seconds እንወያይ፤ የ12 ኛ ክፍል ተማሪዎች ወደቁ የተባሉበት አሳሳቢዉ ዉጤትና አንደምታዉ
ከ 800 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች መዉደቃቸዉ ብቻ ሳይሆን፤ በችግር ያስተማሩ ወላጆች ብሎም በህብረተሰቡ ላይ የሚፈጥረዉ ጫና ቀላል አለመሆኑ ነዉ። የችግሩ መንስኤ ምንድነው? የትምህርት ስርዓት ዉድቀት? ጥቂት ተማሪዎች ብቻ ለከፍተኛ ተቋማት በቁ፤ ብዙኃኑ ግን ወድቋል፤ የተባለለበትን ፈተና የወደቀዉ ማነዉ? እንዴት ትገመግሙታላችሁ? ጻፉልን!
10/22/2023 • 39 minutes, 41 seconds በተስፋ የተሞሉ ተማሪዎች መዉደቃቸዉ የተሰማበት ዜና፤ በኑሮ ዉድነት በቀዉስ ብሎም ከጦርነት ወጥታ ወደ ሌላ ጦርነት ለገባችዉ ሃገር ኢትዮጵያ ሌላ እራስ ምታት ነዉ። ሃላፊነቱን ማን ይዉሰድ?
10/22/2023 • 39 minutes, 41 seconds ውይይት፦ በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ለመመርመር የተቋቋመው ኮሚሽን ሥራ መቋረጥ ምን ያጎድላል?
10/15/2023 • 40 minutes, 3 seconds ያለተጠያቂነት እየተባባሰ የመጣው የሰብአዊ መብት ጥሰት በኢትዮጵያ
10/9/2023 • 39 minutes, 48 seconds «በኢትዮጵያ የኢንተርኔት አገልግሎት ከሰብአዊ መብት አንጻር እንዴት ይታያል?»
በኢትዮጵያ ሚሊዮኖች የሚኖሩባቸው የተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ከኢንተርኔቱ ዓለም እንዳይገናኙ ከተዘጋባቸው ሰነባብተዋል ። ሌላው ቀርቶ የቀጥታ ስልክ መስመር አገልግሎት የማያገኙ አካባቢዎች እና ከተሞች ኢትዮጵያ ውስጥ ጥቂት የሚባሉ አይደሉም ። በኢትዮጵያ አንዳች ነገር ኮሽ ሲል የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት በተደጋጋሚ ሲቋረጥ ይስተዋላል ።
9/24/2023 • 40 minutes, 4 seconds አዲሱ ዓመት ለተቀጣሪው ሰራተኛ ተስፋ ወይስ ስጋት ?
በሀገሪቱ በተለይ የመሰረታዊ ፍጆታ ቁሶች እና የቤት ኪራይ በየጊዜው ያለከልካይ እጅግ በተጋነነ ሁኔታ ጭማሪ ሲያሳዩ ሰራተኛው በወር በሚያገኘው ደመወዝ ላይ ጭማሪ ስለመደረጉ ብዙም አይሰማም ወይም ቢኖርም ያለውን የገበያ እና የኑሮ ሁኔታ የሚመጥን ሆኖ አለመገኘቱ ነው የሚነገረው ።
9/17/2023 • 45 minutes, 28 seconds በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ የሚገኘው ተቀጣሪ የህብረተሰብ ክፍል ተስፋው ምን ይሆን?
9/17/2023 • 45 minutes, 28 seconds 2015 ግጭቶች የተካሄዱበት፣ የመንግሥት ተባባሪ የነበሩ ውጊያ የገጠሙበት ፣ጎሳ ላይ ያነጣጠረ ጥቃት የደረሰበት ፣ቤቶች የፈረሱበት ሰዎች የተፈናቀሉበት፣ የኑሮ ውድነት እጅግ የናረበት ጋዜጠኞች የታሰሩበት ኢንተርኔትም የተቋረጠበት ዓመት ነበር። እነዚህ ችግሮች ወደ 2016 ዓም እንዳይሻገሩ ለመከላከል ምን መደረግ አለበት?
9/10/2023 • 41 minutes, 41 seconds የአማራ ክልል ግጭት፤ የጅምላ እስር እና የመገናኛ አውታሮች ሽፋን
አዲስ አበባን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች የአማራ ተወላጆች በጅምላ ለእስር መዳረጋቸው ከብዙ አቅጣጫ ይሰማል ። ብሔር ተኮር እስሩ መባባሱ፤ ትምህርት ቤቶች ጭምር በታሰሩ ሰዎች መጨናነቃቸውን በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች ይጠቁማሉ ። ለመሆኑ ይህ ምን ያህል የመገናኛ አውታሮች ሽፋን አገኘ?
8/27/2023 • 39 minutes, 54 seconds እንወያይ፤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ሰላምን ያመጣ ይሆን?
ተወያዮች፤የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በተፈጥሮዉ መብት ገዳቢ ነዉ፤ኢትዮጵያም ተሞክሮ ይህንኑ ያሳያል። መንግሥትን ጨምሮ ባለድርሻ አካላት እንዲሁም ዝም ያለዉ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ሁሉ ለሰላም ወደ ድርድር እንዲመጡ፤ጦርነትም ይቁም ሲሉ ጥሪ አሰምተዋል።መንግሥት የጅምላ እስሩን ያቁም፤የአማራ ክልልን ጥያቄዎች ይመልስ ብለዋል። እ ርሶስ? አስተያየት አሎት?
8/20/2023 • 42 minutes, 47 seconds የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ በአማራ ክልል ሰላምን ያሰፍን ይሆን? የክል ሉን ጥያቄዎችስ ይፈታ ይሆን?
8/20/2023 • 42 minutes, 47 seconds ውይይት፦ የአማራ ክልል ቀውስ ገፊ ምክንያቶች፣ ዳፋው እና በውይይት የመቋጨት ተስፋ
8/15/2023 • 39 minutes, 58 seconds የአማራ ክልል ቀውስ፦ ገፊ ምክንያቶች፣ ዳፋው እና በውይይት የመቋጨት ተስፋ
በአማራ ክልል ሲብላላ የቆየው ቅራኔ በሣምንቱ መጀመሪያ ወደ ውጊያ ቢያመራም የመረጋጋት ዝንባሌ አሳይቷል። የቀውሱ ገፊ ምክንያቶች ምንድናቸው? በውይይት ካልተቋጨ በአማራ ክልል እና በኢትዮጵያ ላይ የሚያስከትለው ዳፋ ምን ሊሆን ይችላል? ዶክተር ታደሰ ጥሩነህ፣ ዶክተር ብዙነህ ጌታቸው እና ዶክተር ሰማኸኝ ጋሹ በዚህ ውይይት ተሳትፈዋል።
8/14/2023 • 39 minutes, 58 seconds የኢትዮጵያ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመውጫ ፈተና ውጤት ተስፋ እና ስጋት
7/30/2023 • 40 minutes, 9 seconds 7/2/2023 • 40 minutes, 40 seconds ውይይት፦ የዎላይታ ሕዝበ-ውሳኔ እና ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄ
6/25/2023 • 38 minutes, 32 seconds 6/4/2023 • 39 minutes, 59 seconds 5/28/2023 • 41 minutes, 55 seconds እንወያይ፤ ኢትዮጵያ ከግጭትና ቀዉስ አዙሪት እንዴት ትዉጣ?
በተለያዩ የግጭት ምዕራፍ ውስጥ ገብታ እየተናጠች ያለችው ኢትዮጵያ መውጫዋ ወዴት ይሆን? ምንድን ነዉ ከአንዱ ችግር ወጥተን ወደሌላ ችግር የምንገባበት ምክንያት? መንግሥትን ለመጣል የሚደረግ ትጥቅ ትግል ጊዜዉ ነዉ ወይ? መንግሥትም ሆነ ታጣቂዎች ጦርነት ዉስጥ መግባት ህዝብን ጦርነት ዉስጥ ማስገባት መቼ ነዉ የሚቆመዉ? ከየት ይምጣ ዘላቂው መፍትሄ?
5/28/2023 • 41 minutes, 55 seconds አሳሳቢ እየሆነ የሄደው የፕረስ ነጻነት ይዞታ በኢትዮጵያ
5/14/2023 • 40 minutes, 20 seconds እንወያይ፦ የሸገር ከተማ አስተዳደር ቤት ፈረሳ እና ውዝግቡ
4/23/2023 • 40 minutes, 42 seconds የክልል ልዩ ኃይሎች መፍረስ እና አንድምታው
4/16/2023 • 42 minutes, 47 seconds የጉራጌ የክልልነት ሕገ መንግሥታዊ ጥያቄ እና ምላሹ
በኢትዮጵያ ሕገ መንግሥት አንቀፅ 47 መሰረት ማንኛውም ብሔር ብሔረሰብ በማንኛውም ጊዜ የክልልነት ጥያቄ ማንሳት ሕገ መንግሥታዊ መብቱ እንደሆነ ይደነግጋል ። ለመሆኑ የጉራጌ ሕዝብ ክልል ልሁን፤ ራሴን በራሴም ላስተዳድር ብሎ ያቀረበው ጥያቄ ምን ደረጃ ላይ ይገኛል? ከመንግሥት የተገኘው ምላሽስ ምንድን ነው? ሳምንታዊ እንወያይ መሰናዶ።
4/9/2023 • 40 minutes, 36 seconds ኢትዮጵያ ለሽግግር ፍትህ ዝግጁ ነች? የፍትህ ሚኒስቴር ካቋቋመው ከፍተኛ የባለሙያዎች ቡድን አቶ ምስጋናው ሙሉጌታ እና ዶ/ር ማርሸት ታደሰ፤ በሐርቫርድ ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት የሰብዓዊ መብቶች መርሐ-ግብር ተባባሪ ዳይሬክተር ዶክተር አባድር ኢብራሒም እና ዘ-ሔግ በሚገኝ ፍርድ ቤት በአማካሪነት የሚሰሩት አቶ ካሳሁን ሞላ በውይይቱ ተሳትፈዋል
3/26/2023 • 43 minutes, 38 seconds