የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት የ2024 አሸናፊዋ ከንቲባ
19/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ያስከተለው የሱዳን ግጭት
19/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የከፋ ሰብዓዊ ቀውስ ያስከተለው የሱዳን ግጭት
ከጎርጎሪያኑ ሚያዚያ 2023 ዓ/ም ጀምሮ በሱዳን ጦር እና በፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ መካከል የሚካሄደው የእርስ በርስ ጦርነት ሱዳንን ለከፋ የሰብአዊ ቀውስ ዳርጓታል። በአስር ሺ የሚቆጠሩ ሰዎች የተገደሉበት የሱዳን ጦርነት ሰሞኑን እንደገና ተባብሷል። ይህም የዕርዳታ ስራን በማስተጓጎል ከፍተኛ ሰብዓዊ ቀውስ አስከትሏል።
19/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የጀርመን አፍሪቃ ሽልማት አሸናፊዋ ከንቲባ
የፍሪታውን ከንቲባ ኢቮኔ አኪ ሳውየር ለአሥርተ ዓመታት በእርስ በርስ ጦርነት የደቀቀችውን የሴራሊዮን ዋና ከተማ ፍሪታወንን ለኑሮ ምቹ ወደሆነች ከተማነት ቀይረዋታል። የመኖሪያ ቤቶች፣ የውኃ አቅርቦትና ቆሻሻ አሰባሰብ በእጅጉ አሻሽለዋል።ለዚህ ቁርጠኝነታቸውም የጀርመኑ አፍሪካ ፋውንዴሽን የ2024 የአፍሪካ ሽልማትን ሰጥቷቸዋል።
19/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos በደቡብ አፍሪካ የአንድነት መንግሥት ድምጽ ሰጪዎች ደስተኛ ናቸው?
ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ የሚመሩት የደቡብ አፍሪካ የአንድነ ት መንግሥት በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ለሀገሬው ሰዎች የተወሰነ ተስፋ ፈንጥቋል። ይሁንና በበርካታ ሽኩቻዎች ውስጥ የሚገኘው መንግሥት ደቡብ አፍሪካ ከተዘፈቀችበት የኤኮኖሚ ቀውስ የሚያወጣ የተቀናጀ የፖሊሲ ዕቅድ የለውም።
12/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos “አፍሪካ የበለጠ በፍትኃዊነት መወከል አለባት” የአይኤምኤፍ ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጂዮርጂየቫ
ከሰሐራ በርሐ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የሚኖራቸው ሦስተኛ ተወካይ ጥቅምት 22 ይፋ እንደሚሆን የአበዳሪው ተቋም ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጂዮርጂየቫ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በተቋሙ ለአፍሪካ አንድ ውክልና ሲጨመር የአይኤምኤፍ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የመቀመጫዎች ቁጥር ወደ 25 ከፍ ይላል።
12/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos ትኩረት በአፍሪካ የጥቅምት 2 ቀን 2017 መሰናዶ
ፕሬዝደንት ሲሪል ራማፎሳ የሚመሩት የደቡብ አፍሪካ የአንድነት መንግሥት በመጀመሪያዎቹ 100 ቀናት ለሀገሬው ሰዎች የተወሰነ ተስፋ ፈንጥቋል። ይሁንና በበርካታ ሽኩቻዎች ውስጥ የሚገኘው መንግሥት ደቡብ አፍሪካ ከተዘፈቀችበት የኤኮኖሚ ቀውስ የሚያወጣ የተቀናጀ የፖሊሲ ዕቅድ የለውም። ከሰሐራ በርሐ በታች የሚገኙ የአፍሪካ ሀገራት በዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የሚኖራቸው ሦስተኛ ተወካይ ጥቅምት 22 ይፋ እንደሚሆን የአበዳሪው ተቋም ዋና ዳይሬክተር ክሪስታሊና ጂዮርጂየቫ ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። በተቋሙ ለአፍሪካ አንድ ውክልና ሲጨመር የአይኤምኤፍ ሥራ አስፈጻሚ ቦርድ የመቀመጫዎች ቁጥር ወደ 25 ከፍ ይላል።
12/10/2024 • 0 minutos, 0 segundos የፍሪታው ን ከንቲባ ኢቮን አኪ ሶየር የጀርመን አፍሪካ ሽልማታቸውን መስከረም 26 ይቀበላሉ
የሴራ ሊዮን ዋና ከተማ ፍሪታውን ከንቲባ ኢቮን አኪ ሶየር የጀርመን አፍሪካ ሽልማታቸውን መስከረም 26 ይቀበላሉ። የፍሪታውን ከተማን የቆሻሻ አወጋገድ በማዘመን፣ የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦትን በማሻሻል እና ዛፎች እንዲተከሉ በማበረታታት ኢቮን አኪ ሶየር ስኬታማ ሆነዋል።
28/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የአውሮፓ ኅብረት ከአፍሪካ ስደት ለመቀነስ የመደበው የ5 ቢሊዮን ዩሮ ፈንድ ብርቱ ትችት ተሰነዘረበት
የአውሮፓ ኅብረት ከአፍሪካ ስደት ለመቀነስ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ይፋ ያደረገው የ5 ቢሊዮን ዩሮ ፈንድ በኦዲተሮች ብርቱ ትችት ተሰንዝሮበታል። ከተመደበው ገንዘብ ኢትዮጵያ የምትገኝበት የአፍሪካ ቀንድን ጨምሮ በሦስት ቀጠናዎች በ27 ሀገራት በ248 መርሐ-ግብሮች 933 የኮንትራት ውሎች ተፈርመዋል።
28/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos ትኩረት በአፍሪካ የመስከረም 18 ቀን 2017 መሰናዶ
የአውሮፓ ኅብረት ከአፍሪካ ስደት ለመቀነስ ከዘጠኝ ዓመታት በፊት ይፋ ያደረገው የ5 ቢሊዮን ዩሮ ፈንድ በኦዲተሮች ብርቱ ትችት ተሰንዝሮበታል። ከተመደበው ገንዘብ ኢትዮጵያ የምትገኝበት የአፍሪካ ቀንድን ጨምሮ በሦስት ቀጠናዎች በ27 ሀገራት በ248 መርሐ-ግብሮች 933 የኮንትራት ውሎች ተፈርመዋል። የሴራ ሊዮን ዋና ከተማ ፍሪታውን ከንቲባ ኢቮን አኪ ሶየር የጀርመን አፍሪካ ሽልማታቸውን መስከረም 26 ይቀበላሉ። የፍሪታውን ከተማን የቆሻሻ አወጋገድ በማዘመን፣ የንጹህ መጠጥ ውኃ አቅርቦትን በማሻሻል እና ዛፎች እንዲተከሉ በማበረታታት ኢቮን አኪ ሶየር ስኬታማ ሆነዋል።
28/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos በናይጀሪያ የተስፋፉት የሀሰት የዩኒቨርስቲ ዲግሪዎች
14/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos ሀንጋሪ ወታደሮቿን ወደ ቻድ ለመላክ ተዘጋጅታለች
14/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos በናይጀሪያ የተስፋፉት የሀሰት የዩኒቨርስቲ ዲግሪዎች
የፌደራሉ መንግሥት ፕሬዝዳንት ቦላ አህመድ ቲኑቡ የሀገሪቱ የሲቪል ሰርቪስ ፌደሬሽን ሃላፊ ማናቸውንም የሀሰት ሰርተፊኬት የያዘ ሰው እንዲያባርሩ ትዕዛዝ ሰጥተዋል ። ፕሬዝዳንቱ በዚህ እርምጃ የናይጄሪያን ቀጣሪዎች ከዚህ ዓይነቱ የሀሰት የትምህርት መረጃ መጠበቅና በአገሪቱ ውስጥ የብቃት ማረጋገጫዎች ትክክለኛነትን ማረጋገጥ ይገባል ብለዋል።
14/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos ሀንጋሪ ወታደሮቿን ቻድ ለመላክ ተዘጋጅታለች
ከክፍለ ዓለሙ ውጭ በሚገኙ ታዛቢዎች እምነት ኦርባን 200 ወታደሮችን በመላክ በምዕራብ አፍሪቃ እያደገ የመጣውን የሩስያ ተጽእኖ እየኮረጁ ነው። አንዳንዶቹ የወታደሮቹ መስፈር በሳህል አካባቢ የጸጥታ ሁኔታ ላይ ከባድ ተጽእኖ ሊያሳርፍ ይችላል ይላሉ።ተንታኙ አውሱ እንደሚሉት ግን በትልቂቱ ቻድ 200 ወታደሮች ምንም ዓይነት ተጽእኖ ሊያደርጉ አይችሉም።
14/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos ግብጽን ያንደረደረው ውጥረት በሶማሊያና ኢትዮጵያ መካከል
ግብጽ ከሰሞኑ የጦር መሣሪያዎችን በወታደራዊ አውሮፕላን ጭና ሞቃዲሾ ማስገባቷ ይፋ ከሆነ በኋላ በኢትዮጵያ እና ሶማሊያ መካከል ወታደራዊ ፍጥጫው እጅግ አይሏል ። ሁኔታዎች ወደየት እያመሩ ይሆን?
7/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos የቻይና እና የአፍሪቃ ትብብር (FOCAC) የላቀ እመርታ በማሳየት ላይ ነው ። የቻይና እና አፍሪቃ የትብብር ጉባኤ ትናንት ሲጠናቀቅ ቻይና ለአፍሪቃ 51 ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ መመደቧ ተሰምቷል ። ቻይና ከኢትዮጵያ ጋ በመተባበር ፖለቲካዊ የእርስ በርስ መተማመንን ለማጠናከር፣ ሁለንተናዊ ወዳጅነትን ለማጎልበት እንደምትሠራ ገልጣለች ።
7/9/2024 • 0 minutos, 0 segundos ትኩረት በአፍሪቃ፣ የጋቦን መፈንቅለ መንግሥት አንደኛ ዓመት።አፍሪቃ በፀጥታዉ ምክር ቤት
31/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos ሞሮኮ ምዕራብ ሰሐራን ለመቆጣጠር ለረዥም ዓመታት የተከተለችው ስልት እየሰራ ነው
ሞሮኮ በምዕራብ ሰሐራ ግዛት ላይ የምታነሳውን የይገባኛል ጥያቄ በመደገፍ ፈረንሳይ ለንጉሥ መሐመድ 5ኛ መንግሥት ከፍ ያለ ውለታ ውላለች። በምላሹ ፈረንሳይ ወደ አውሮፓ መጓዝ የሚፈልጉ ስደተኞችን ሞሮኮ እንድትቆጣጠር ትሻለች። የፈረንሳይ የአቋም ለውጥ ለሰሐራ ሰዎች የነጻነት ጥያቄ ብቻ ሳይሆን በሞሮኮ እና አልጄሪያ ውዝግብ ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል
24/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos ዩጋንዳ የዜጎቿን ሕይወት ከቀጠፈ የቆሻሻ ክምር መደርመስ አደጋ በኋላ ኃይለኛ ጥያቄ ተጋፍጣለች
ዩጋንዳ እንደ ኢትዮጵያ ኃይለኛ የቆሻሻ ክምር ተንዶ የ35 ዜጎቿን ሕይወት ተነጥቃለች። ከአደጋው በኋላ የሀገሪቱ የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት ጥያቄ ተነስቶበታል። የፕሬዝደንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ መንግሥት ከአራት ዓመታት በፊት ብሔራዊ የቆሻሻ አወጋገድ ዕቅድ ይፋ ቢያደርግም በገንዘብ እጥረት ምክንያት ተግባራዊነቱ እጅግ ዘግይቷል።
24/8/2024 • 0 minutos, 0 segundos ትኩረት በአፍሪካ የነሐሴ 18 ቀን 2016 መሰናዶ